ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፷


ክፍል ፷

በነሀሴ ፰፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በጃክሰን አውራጃ ሚዙሪ ውስጥ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። በዚህ ጊዜ ወደ ጃክሰን አውራጃ የተጓዙ እና በመሬቱና በቤተመቅደስ መገንቢያ ቦታ መቀደስ የተሳተፉ ሽማግሌዎች ምን ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው ለማወቅ ፈልገው ነበር።

፩–፱፣ ሽማግሌዎች በኃጢአተኞቹ ጉባኤ መካከል ወንጌልን ይስበኩ፤ ፲–፲፬፣ ጊዜአቸውን አያጠፉም እናም ችሎታቸውንም አይደብቁም፤ ፲፭–፲፯፣ ወንጌሉን ባልተቀበሉት ላይ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ እግራቸውን ይጠቡ።

፩ እነሆ፣ ወደመጡበት አገር ፈጥነው ለሚመለሱት ለቤተክርስቲያኑ ሽማግሌዎች ጌታ እንዲህ ይላል፥ እነሆ፣ ወደዚህ ስፍራ መምጣታችሁ አስደስቶኛል፤

፪ ነገር ግን በአንዳንዶች አልተደሰትኩም፣ አንደበቶቻቸውን አልከፈቱምና፣ ነገር ግን ሰውን በመፍራት የሰጠኋቸውን ችሎታ ደብቀዋል። ለእነዚህ አይነቶችም ወዮላቸው፣ ቁጣዬ በእነርሱ ላይ ነዳለችና።

፫ እናም እንዲህ ይሆናል፣ ለእኔ ይበልጥ ታማኝ ካልሆኑ ይህም፣ እንዲሁም ያላቸውም፣ ይወሰድባቸዋል።

፬ እኔ ጌታ ከላይ በሰማያት፣ እናም በምድር ሰራዊት መካከልም እገዛለሁና፤ እናም እንቁዎቼን በምሰበስብበት ጊዜ፣ ሁሉም ሰዎች የእግዚአብሔር ሀይልን የሚያውጀው ምን እንደሆነም ያውቃሉ።

፭ ነገር ግን፣ ወደ መጣችሁበት አገር ስለምትጓዙበትም እነግራችኋለሁ። ለእኔ ምንም ልዩነት ስለሌለው፣ እንደሚመስላችሁ መዘውር ይሰራ ወይም ይገዛ፣ እናም ሴንት ሉዊስ ወደሚባለው ከተማም ፈጥናችሁ ተጓዙ።

፮ ከዚያም ቦታ አገልጋዮቼ ስድኒ ሪግደን፣ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ፣ እና ኦሊቨር ካውድሪ ም ወደ ስንሰናቲ ይጓዙ፤

፯ እናም በዚህ ስፍራም ድምጻቸውን አንስተው፣ ያለ ቍጣና አለ ጥርጥር፣ ቅዱስ እጆችን በማንሳት፣ በጎላ ድምፅ ቃላቴን ይግለጹ። ቅዱሳን አደርጋችሁ ዘንድ ይቻለኛልና፣ እናም ኃጢአቶቻችሁም ተሰርየዋል።

፰ እና የሚቀሩትም፣ ከመጡባቸው ቤተክርስቲያኖች እስከሚመለሱ ድረስ፣ ሁለት በሁለት በመሆን፣ እናም በችኮላ ሳይሆን፣ ቃሉን በኃጢአተኞቹ ጉባኤ መካከል በመስበክ፣ ከሴንት ልዊስ ጎዞአቸውን ይጀምሩ።

፱ እናም ይህም ሁሉ ለቤተክርስቲያኖቹ ጥቅም ነው፤ ለዚህም ምክንያት ልኬአቸዋለሁና።

፲ እናም አገልጋዬ ኤድዋርድ ፓርትሪጅ የሰጠሁትን ገንዘብ፣ እንዲመለሱ ለታዘዙት ለእኔ ሽማግሌዎች ክፈሉን ይስጥ፤

፲፩ እና የሚችለውም፣ በወኪሉ በኩልም ይህን ይመልስ፤ እናም ከማይችለውም፣ ከእርሱ ይህ አይጠበቅበትም።

፲፪ እናም አሁን ወደዚህ ምድር እየመጡ ስላሉትም ቅሪቶች እናገራለሁ።

፲፫ እነሆ፣ በኃጢአተኞቹ ጉባኤ መካከል ወንጌሌን እንዲሰብኩ ተልከው ነበር፤ ስለዚህ፣ እንዲህም ትእዛዝ እሰጣቸዋለሁ፥ ጊዜአችሁን አታጥፉ፣ ችሎታችሁንም እንዳይታወቁ አትቅበሩ።

፲፬ እናም ወደ ፅዮን ምድር ከመጣችሁም እናም ቃሌን ካወጃችሁ በኋላ፣ በችኮላ፣ ወይም በቁጣ ወይም በጥላቻ ሳይሆን፣ በኃጢአተኞቹ ጉባኤ መካከል ወንጌሌን በማወጅ ፈጥናችሁ ተመለሱ።

፲፭ እናም እንዳታስቆጧቸው በፊት ለፊታቸው ሳይሆን በሚስጥር፣ በማይቀበሏችሁም ላይ ከእግራችሁ በታች ያለውን ትቢያ አራግፉ፤ ይህም በፍርድ ቀን ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ እግራችሁን እጠቡ።

፲፮ እነሆ፣ ይህም ለእናንተ በቂ እናም የእርሱ የላካችሁም ፈቃድ ነው።

፲፯ እናም በአገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ አንደበት በኩልም ስለስድኒ ሪግደን እና ኦሊቨር ካውድሪ ይገለጣል። የሚቀረውም ከዚህ በኋላ ይገለጣል። እንዲህም ይሁን። አሜን።