ክፍል ፹፰
በታህሳስ ፳፯ እና ፳፰፣ ፲፰፻፴፪፣ እና በጥር ፫፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ይህም በነቢዩ “‘የወይራ ቅጠል’…ከገነት ዛፍ የተቀጠፈች፣ ለእኛ የተሰጠ የጌታ የሰላም መልእክት” ተብሎ ተጠቁሞ ነበር። ይህም ራዕይ የተሰጠው ሊቀ ካህናት በጉባኤ “አንድ በአንድ እና በድምጽ ጌታ ለእኛ ስለፅዮን መገንባት ፍላጎቱን እንዲገልጽልን” ከጸለዩ በኋላ ነበር።
፩–፭፣ ታማኝ ቅዱሳን የዘለአለም ህይወት ተስፋ የሆነውን ያንን አፅናኝ ተቀበሉ፤ ፮–፲፫፣ ሁሉም ነገሮች በክርስቶስ ብርሀን ቁጥጥር ስር ያሉ እና የሚገዙ ናቸው፤ ፲፬–፲፮፣ ትንሳኤ የሚመጣው በቤዛነት በኩል ነው፤ ፲፯–፴፩፣ ለሰለስቲያል፣ ለተረስትሪያል፣ ወይም፤ ለቲለስቲያል ህግ ታዛዥ መሆን ሰዎችን ለእነዚህ መንግስታት እና ክብሮች ያዘጋጃል፤ ፴፪–፴፭፣ በኃጢአት የሚኖሩትም በመርከስ ይቀራሉ፣ ፴፮–፵፩፣ ሁሉም መንግስታት በህግ የሚገዙ ናቸው፤ ፵፪–፵፭፣ እግዚአብሔር ለሁሉም ነገሮች ህግ ሰጥቷል፤ ፵፮–፶፣ ሰው እግዚአብሔርንም እንኳ ይረዳዋል፤ ፶፩–፷፩፣ አገልጋዮቹን ወደ መስክ ልኮ እናም በየተራ ስለሚጎበኛቸው ሰው ምሳሌ፤ ፷፪–፸፫፣ ወደጌታ ቅረቡ፣ እናም ፊቱንም ታያላችሁ፤ ፸፬–፹፣ ራሳችሁን ቀድሱ እናም የመንግስትን ትምህርት እርስ በርስ ተማማሩ፤ ፹፩–፹፭፣ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው እያንዳንዱ ሰው ጎረቤቱን ሊያስጠነቅቅ ይገባዋል፤ ፹፮–፺፬፣ ምልክቶች፣ የፍጥረታት መናወጥ፣ እና መላዕክት የጌታን መምጫ መንገድ ያዘጋጃሉ፤ ፺፭–፻፪፣ መላዕክታዊ መለከቶች ሙታንን በየተራቸው እንዲነሱ ይጠሯቸዋል፤ ፻፫–፻፲፮፣ መላእክታዊ መለከቶች የወንጌሉን በዳግም መመለስ፣ የባቢሎንን መውደቅ፣ እና የታላቁን የእግዚአብሔር ጦርነት ያውጃሉ፤ ፻፲፯–፻፳፮፣ ትምህርትን ፈልጉ፣ የእግዚአብሔርን ቤት (ቤተመቅደስን) መስርቱ፣ እናም የልግስና ማሰሪያንም ልበሱ፤ ፻፳፯–፻፵፩፣ የነቢያት ትምህርት ቤት ስርዓት፣ እግሮችን የማጠብ ስርዓት በመጨመር፣ ተመድቧል።
፩ በእውነት፣ እናንተን በመመልከት ያለውን ፈቃዱን ለመቀበል ለተሰበሰባችሁት ጌታ እንዲህ ይላል፥
፪ እነሆ፣ ይህ ጌታን የሚያስደስት ነው፣ እናም መላእክትም በእናንተ ሀተደስተዋል፤ የጸሎታችሁ ለምፅዋትም ሐበፀባኦት ጌታ ጆሮዎች ውስጥ መጥተዋል፣ እናም በተቀደሱት ስሞች፣ እንዲሁም የሰለስቲያል አለም በሆኑት፣ መመፅሀፍ ውስጥ ተመዝግበዋል።
፫ ስለዚህ፣ ለእናንተ፣ እንዲሁም ወደ እናንት ባልንጀሮቼ፣ በልባችሁ ውስጥ እንዲኖር፣ ሌላ ሀአፅናኝ፣ እንዲሁም ለቅዱስ የተስፋ መንፈስን እልክላችኋለሁ፤ ያም አፅናኝ፣ በዮሐንስ ምስክር ውስጥ እንደተመዘገበው፣ ለደቀመዛሙርቴ ቃል የገባሁላቸው ነው።
፬ ይህም አፅናኝ ሀለዘለአለም ህይወት፣ እንዲሁም የሰለስቲያል መንግስት ለክብርን፣ እንደምሰጣችሁ የገባሁላችሁ ቃል ኪዳን ነው፤
፭ ይህም ሀየበኩሩ ቤተክርስቲያን፣ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሆነ፣ እንዲሁም ከሁሉም በላይ ቅዱስ የሆነው የእግዚአብሔር ክብር ነው—
፮ ሀእርሱም በሁሉም ነገሮች ውስጥና በሁሉም ነገሮች በኩል በመሆን የእውነት ለብርሀን ይሆን ዘንድ፣ በዚህም ሁሉን ነገሮች ሐእንዲረዳ ዘንድ፣ ወደላይ ያረገው፣ ደግሞም ከሁሉም ነገሮች በታች መየወረደው ነው።
፯ ይህም እውነት ያበራል። ይህም ሀየክርስቶስ ብርሀን ነው። እርሱም በጸሀይ ውስጥ፣ እናም የጸሀይ ብርሀን፣ እናም ያም ለየተሰራበት ሀይል ነው።
፰ እርሱም በጨረቃ ውስጥ፣ እናም የጨረቃ ብርሀን፣ እና ያም የተሰራበት ሀይል ነው፤
፱ የከዋክብትም ብርሀን፣ እናም እነዚህም የተሰሩበት ሀይል፤
፲ እናም ምድርንም፣ እናም ይህም ሀይል፣ እንዲሁም ሀየቆማችሁበት ምድር ነው።
፲፩ እናም ብርሀን የሚሰጣችሁም፣ የሚበራው ብርሀንም፣ በእርሱ አይኖቻችሁን የሚያበራው በኩል ነው፣ ያ ብርሀንም ሀየምትረዱበትን የሚያነሳሳው ነው፤
፲፪ ያም ከእግዚአብሔር ፊት ጠፈርን ሀለመሙላት የሚሄድ ለብርሀን ነው—
፲፫ ሀበሁሉም ነገሮች ውስጥ ነው፣ ለሁሉም ነገሮች ለህይወት ይሰጣል፣ ሁሉም ነገሮች የሚገዙበት ሐህግ፣ እንዲሁም፣ በዘለአለም እቅፍ ውስጥ ያለው፣ በሁሉም ነገሮች መካከል ውስጥ ያለው፣ በዙፉኑ ላይ የሚቀመጠው የእግዚአብሔር ሀይል የሆነው ብርሀን ነው።
፲፬ አሁን፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ለእናንተ በተደረገላችሁ ሀቤዛነት በኩል የሙታን ትንሳኤ ይመጣል።
፲፭ እናም ሀመንፈስና ለአካል የሰው ሐነፍስ ናቸው።
፲፮ እናም የሙታን ሀትንሳኤ የነፍስ ቤዛነት ነው።
፲፯ እናም የነፍስ ቤዛነትም ሁሉንም ነገሮች ህይወት በሚሰጠው፣ በልቡ ሀድሀውና ለየዋሁ ሐምድርን ይወርሳሉ ተብሎ በታወጀበት በእርሱ በኩል ነው።
፲፰ ስለዚህ፣ ሀለሰለስቲያል ክብር ያዘጋጅ ዘንድ፣ ጽድቅ ካልሆነው ሁሉ መንጻት አለበት፤
፲፱ የተፈጠረበትን አላማ ካሟላ በኋላ፣ ሀበክብር፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር አብም ፊት፣ ይነግሳል፤
፳ የሰለስቲያል መንግስት የሆኑት አካላት ለዘለአለም ሀየራሳቸው ያደርጉት ዘንድ ነው፤ ለዚህም ለምክንያት ተሰርቷል እና ተፈጥሯል፣ እናም ለዚህም ምክንያት ሐተቀድሷል።
፳፩ እናም በምሰጣችሁ ህግ፣ እንዲሁም በክርስቶስ ህግ፣ በኩል የማይቀደሱት፣ ሌላ መንግስትን፣ እንዲሁም የተረስትሪያል መንግስትን ወይም የቲለስቲያል መንግስትን፣ መውረስ አለባቸው።
፳፪ በሰለስቲያል መንግስት ሀህግ መፅናት የማይችለው በሰለስቲያል ክብር መፅናት አይችልምና።
፳፫ እና በተረስትሪያል መንግስት ህግ መፅናት የማይችለውም ሀበተረስትሪያል ክብር መፅናት አይችልም።
፳፬ እና በቲለስቲያል መንግስት ህግ መፅናት የማይችለውም ሀበቲለስቲያል ክብር መፅናት አይችልም፤ ስለዚህ ለመንግስት ክብር ብቁ አይደለም። ስለዚህ የክብር መንግስት ባልሆነ መንግስት ውስጥ መፅናት አለበት።
፳፭ ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ሀምድር በሰለስቲያል መንግስት ህግ ትጸናለች፣ የፍጥረቷን አላማ ታሟላለችና፣ እናም ህግጋትን አትተላለፍምና—
፳፮ ስለዚህ፣ ሀትቀደሳለች፤ አዎን፣ ምንም እንኳን ለየምትሞትም ቢሆን፣ ዳግም ህይወት ይሰጣታል፣ እናም ህይወት በተሰጠባት ሀይልም ትጸናለች፣ እናም ሐጻድቃንም መይወርሷታል።
፳፯ ምንም እንኳን ቢሞቱም፣ ዳግም እንደ ሀመንፈሳዊ ሰውነት ለይነሳሉ።
፳፰ ሰለስቲያል መንፈስ የሆኑትም ፍጥረታዊ ሰውነት የሆነውን አንድ አይነት ሰውነት ይቀበላሉ፤ እንዲሁም ሰውነታችሁን ትቀበላላችሁ፣ እናም ሀክብራችሁም ሰውነታችሁ ለህይወት የተሰጠበት ያ ክብር ይሆናል።
፳፱ ሀበሰለስቲያል ክብር ህይወት ከፊሉ የተሰጣችሁም፣ እንዲሁም ደግሞ ሙሉነትን፣ ትቀበላላችሁ።
፴ እናም ሀበተረስትሪያል ክብር ክፍል ህይወት የተሰጣቸውም አንድ አይነት፣ እንዲሁም ሙሉነትን፣ ይቀበላሉ።
፴፩ እናም ሀበቲለስቲያል ክብር ክፍል ህይወት የተሰጣቸውም አንድ አይነት፣ እንዲሁም ሙሉነትን፣ ይቀበላሉ።
፴፪ እናም የቀሩ ሰዎችም ሀህይወት ይሰጣቸዋል፤ ይህም ቢሆን፣ ሊያገኟቸው የሚችሉትን ለመቀበል ለፈቃደኛ ስላልነበሩ፣ ለመቀበል ፈቃደኛ በሆኑት ለመደሰት ወደስፍራቸው ዳግም ይመለሳሉ።
፴፫ ለሰው ስጦታ ቢሰጠው እና ስጦታውን ባይቀበለው ምን ይጠቅመዋል? እነሆ፣ በተሰጠው አይደሰትም፣ ወይም በስጦታ ሰጪውም አይደሰትም።
፴፬ ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በህግ የሚመራው በህግ ይጠበቃል እና በዚህ ፍጹም ይሆናልም ሀይቀደሳልም።
፴፭ ሀህግን የሚሰብርና በህግ የማይጸናው፣ በራሱ ህግ ለመሆን የሚፈልገው፣ እና በኃጢአት ለመፅናት ፈቃደኛ የሆነው፣ እና ሁሉ በኃጢአት የሚጸናው ግን በህግ ወይም ለበምህረት፣ ሐበፍትህ፣ ወይም በፍርድ ሊቀደስ አይችልም። ስለዚህ፣ መረክሰው መቅረት አለባቸው።
፴፮ ሁሉም መንግስታት የተሰጣቸው ህግ አላቸው፤
፴፯ እናም ብዙ ሀመንግስታት አሉ፤ መንግስት የሌለበት ምንም ስፍራ የለም፤ እና፣ ታላቁ ወይም ታናሹ መንግስት፣ ስፍራ የሌለው ምንም መንግስት የለም።
፴፰ እናም ለእያንዳንዱም መንግስት ሀህግ ተሰጥቷል፤ እና ለእያንዳንዱም ህግ ልዩ ገደብና አካሄድ አላቸው።
፴፱ በእነዚህ ሀአካሄዶች ለየማይጸኑትም ከጥፋት ነጻ አይሉም።
፵ ሀየመረዳት ችሎታ ከመረዳት ችሎታ ጋር ይጣበቃል፤ ለጥበብም ጥበብን ይቀበላል፤ ሐእውነት እውነትን ያቅፋል፣ መበጎነት በጎነትን ያፈቅራል፤ ሠብርሀን ከብርሀን ጋር ይጣበቃል፤ ምህረት በምህረት ላይ ረርህራሄ አላት እና የራሷንም ታደርገዋለች፤ ፍትህ መንገዱን ይቀጥላል እናም የራሱንም ይወስዳል፤ ፍርድም በዙፋን ላይ በሚቀመጠውና ሁሉንም ነገሮች በሚመራውና በሚያከናውነው ፊት ይሄዳል።
፵፩ ሁሉንም ነገሮች ሀይረዳል፣ እና ሁሉም ነገሮች በፊቱ ናቸው፣ እና ሁሉም ነገሮች በዙሪያው ናቸው፤ እና በሁሉም ነገሮች ላይ፣ በሁሉም ነገሮች ውስጥ ነው፣ እና በሁሉም ነገሮች ከዳር እስከ ዳር ነው፤ እና ሁሉም ነገሮች በእርሱ፣ እና በእርሱ በኩል፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር፣ ለዘለአለም ናቸው።
፵፪ እና ዳግም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ለሁሉም ነገሮች ሀበጊዜአቸው እና በወቅታቸው የሚሄዱበት ህግ ሰጥቷል፤
፵፫ እናም መንገዶቻቸውም፣ እንዲሁም ምድርን እና ፕላኔቶችን የሚያካትቱት የሰማያት እና የምድር መንገዶች፣ የተወሰኑ ናቸው።
፵፬ እናም በጊዜአቸው እና በወቅታቸውም፣ በደቂቃዎቻቸው፣ በሰአቶቻቸው፣ በቀናቶቻቸው፣ በሳምንቶቻቸው፣ በወራቶቻቸው፣ በአመቶቻቸው እርስ በራስ ሀብርሀን ይሰጣሉ—እነዚህም ሁሉ ለእግዚአብሔር ለአንድ አመት ናቸው፣ ነገር ግን ለሰው አይደሉም።
፵፭ ምድር በክንፎቿ ትሽከረከራለች፣ እናም ሀጸሀይ ብርሀኑን በቀን ይሰጣል፣ እና ጨረቃም ብርሀኗን በማታ ትሰጣለች፣ እና ከዋክብትም፣ በእግዚአብሔር ለሀይል መካከል በክብር በክንፎቻቸው ሲሽከረከሩ፣ ብርሀናቸውን ይሰጣሉ።
፵፮ እንዲገባችሁ፣ እነዚህን መንግስታት ከምን ጋር ላመሳስል?
፵፯ እነሆ፣ እነዚህ ሁሉ መንግስታት ናቸው፣ እናም ማንኛውን ወይም ከእነዚህ ታናሾችን ያየ ማንም ሰው እግዚአብሔር በሞገሱ እና በክብሩ ሲሄድ ሀአይቶታል።
፵፰ እላችኋለሁ፣ እርሱ አይቶታል፤ ይህም ቢሆን፣ ሀየራሱ ወደ ሆኑት የመጣውንም አልተቀበሉትም።
፵፱ ሀብርሀንም በጭለማ ያበራል፣ እና በጨለማም ያሉት አይረዱትም፤ ይህም ቢሆን፣ በእርሱ ውስጥ እና በእርሱ ህይወት ተሰጥቷችሁ እግዚአብሔርን ለየምትረዱበት ቀን ይመጣል።
፶ ከዚያም እንዳያችሁኝ፣ እንደሆንኩኝ፣ እና በውስጣችሁ ያለሁት የእውነት ብርሀን እንደሆንኩኝ፣ እና እናንተም በእኔ ውስጥ እንዳላችሁ ታውቃላችሁ፤ አለበለዚያም ውጤታማ አትሆኑም።
፶፩ እነሆ፣ እነዚህን መንግስታት እርሻ ባለው ሰው አመሳስላቸዋለሁ፣ እናም አገልጋዮቹ እርሻውን ይቆፍሩ ዘንድ ወደ እርሻው ላካቸው።
፶፪ እና ለመጀመሪያው እንዲህ ይላል፥ ሂድ እና በእርሻው ስራ፣ እና በመጀመሪያው ሰዓት ወደአንተ እመጣለሁ፣ እና የፊቴ ደስታን ታያለህ።
፶፫ እና ለሁለተኛውም እንዲህ ይላል፥ አንተ ደግመህ ወደ እርሻው ሂድ፣ እና በሁለተኛው ሰዓት በፊቴ ደስታ እጎበኝሀለሁ።
፶፬ እና ደግሞም ለሶስተኛውም አለ፥ እጎበኝሀለሁ።
፶፭ እና ለአራተኛውም፣ እና ቀጥሎም ለአስራ ሁለቱ።
፶፮ በመጀመሪያው ሰዓት የእርሻው ጌታ ወደ መጀመሪያው ሄደ፣ እና በዚያ ሰዓት ሁሉ ከእርሱ ጋር ቆየ፣ እና እርሱም በጌታው ፊት ብርሀን ተደሰተ።
፶፯ እና ከዚያም ሁለተኛውን፣ እና ሶስተኛውን፣ እና አራተኛውን፣ እና እስከ አስራሁለተኛው ድረስ ደግሞ ለመጎብኘት ከመጀመሪያው ተለይቶ ሄደ።
፶፰ እንደዚሁ ሁሉም፣ እያንዳንዱ በሰዓቱ፣ እና በጊዜው፣ እና በወቅቱ፣ የጌታቸውን ፊት ብርሀን ተቀበሉ—
፶፱ ከመጀመሪያው ጀምሮ፣ እና ሀእስከመጨረሻው በመቀጠል፣ እና ከመጨረሻው እስከመጀመሪያው፣ እና ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው እንዲህ ተቀበሉ፤
፷ ጌታው በእርሱ እና እርሱም በጌታው፣ ይከብር ዘንድ፣ ሁሉም ይከብሩ ዘንድ፣ እያንዳንዱም ሰው ሰዓቱ እስኪያልቅ ድረስ፣ እንዲሁም ጌታው እንዳዘዘው እንዲሁ ተቀበለ።
፷፩ ስለዚህ፣ በዚህ ምሳሌ እነዚህን መንግስታት፣ እና ሀየሚኖሩባቸውን፣ እንዲሁም በሰአቱ፣ እና በጊዜው፣ እና በወቅቱ፣ እንዲሁም እግዚአብሔር ባወጀው ያሉትን እያንዳንዱ መንግስት እመስላለሁ።
፷፪ እና ዳግም፣ ሀባልንጀሮቼ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በቅርብ እያለሁ ለእንድትጠሩኝ ዘንድ፣ ከምሰጣችሁ ከዚህ ትእዛዝ ጋር፣ እነዚህን አባባሎች በልባችሁ ሐእንድታሰላስሏቸው እተውላችኋለሁ—
፷፫ ወደ እኔ ሀቅረቡ እና እኔም ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ ተግታችሁም ለፈልጉኝ እናም ሐታገኙኝማላችሁ፤ ለምኑ፣ እናም ይሰጣችኋል፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችሁማል።
፷፬ ለእናንተ ሀአስፈላጊ የሆነውን ማንኛውንም ነገር በስሜ አብን ለብትለምኑ፣ ይሰጣችኋል።
፷፭ እናም ለእናንተ ሀአስፈላጊ ያልሆነውን ብትጠይቁ፣ ወደ ለኩነኔም ይቀየርባችኋል።
፷፮ እነሆ፣ የምትሰሙት በምድረበዳ እንደሚጮኽ ሰው ሀድምፅ ነው—በምድረበዳ፣ ምክንያቱም ልታዩት አትችሉምና—ድምጼ፣ ምክንያቱም ድምጼ ለመንፈስ ነውና፤ መንፈሴም እውነት ነው፤ ሐእውነትም ይጸናልና መጨረሻም የለውም፤ እና በእናንተ ቢሆንም ይበዛል።
፷፯ እና ወደ ሀክብሬ ዐይኖቻችሁ ለቢያተኩሩ፣ ሰውነታችሁ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፣ እና በእናንተም ምንም ጭለማ አይኖርም፤ እና ብሩህ የሆነ ሰውነትም ሁሉንም ነገሮች ሐይረዳል።
፷፰ ስለዚህ፣ ሀአዕምሮዎቻችሁ ለእግዚአብሔር የቀኑ እንዲሆኑ ራሳችሁን ለቀድሱ፣ እናም እርሱን ሐየምታዩበት ቀን ይመጣል፤ ፊቱን ለእናንተ ይገልጣልና፣ እና ይህም በራሱ ጊዜና፣ በራሱ መንገድ፣ እናም እንደ ፈቃዱ ይሆናል።
፷፱ የሰጠኋችሁን ታላቅ እና የመጨረሻ ቃል ኪዳን አስታውሱ፤ ሀከንቱ ሀሳቦቻችሁንና ከልክ በላይ የሆኑ ለሳቆችን ከእናንተ አስወግዱ።
፸ ቆዩ፣ በዚህም ስፍራ ቆዩ፣ እና የክብር ስብሰባን፣ እንዲሁም በእዚህ በመጨረሻው መንግስት የመጀመሪያ አገልጋዮች የሆኑትን፣ ጥሩ።
፸፩ እናም ያስጠነቀቋቸውም በጉዞአቸው ጌታን ይጥሩ፣ እና ለጥቂት ወቅትም የተቀበሉትን ሀማስጠንቀቂያ በልቦቻቸው ያሰላስሉ።
፸፪ እነሆ፣ እናም አስተውሉ፣ መንጋዎቻችሁን እንከባከባለሁ፣ እና ሽማግሌዎችን አስነሳለሁ እና ወደ እነርሱም እልካለሁ።
፸፫ እነሆ፣ ስራዬን በራሱ ጊዜ አፈጥናለሁ።
፸፬ እናም የዚህ የመጨረሻ መንግስት የመጀመሪያ ሀአገልጋዮች ለሆናችሁ፣ አብራችሁ እንድትሰበሰቡ፣ እና ራሳችሁን እንድታደራጁ፣ እና ራሳችሁን እንድታዘጋጁ፣ እና ራሳችሁን ለትቀድሱ ዘንድ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ አዎን፣ ሐአነጻችሁም ዘንድ ልባችሁን አንጹ፣ እጆቻችሁን እና እግሮቻችሁንም በፊቴ መየጸዱ ይሁኑ፤
፸፭ ከዚህ ክፉ ትውልድ ደም ንጹህ መሆናችሁን ወደ ሀአባታችሁ፣ አምላካችሁና፣ አምላኬ፣ እመሰክር ዘንድ፤ እንደ ፈቃዴም የገባሁላችሁ ቃል ኪዳን፣ ይህን ታላቅ እና የመጨረሻ ቃል ኪዳን፣ ላሟላ እችል ዘንድ ነው።
፸፮ ደግሞም፣ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሀበጸሎት እና ለበጾም ትበረቱም ዘንድ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።
፸፯ እናም የመንግስቱን ሀትምህርት እርስ በርስ ለትማማሩም ዘንድ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።
፸፰ በትጋት አስተምሩ እናም፣ ሀጸጋዬ ከእናንተ ጋር ይሆናል፣ ይህም በፅንሰ ሀሳብ፣ በመሰረታዊ መርሆች፣ በትምህርት፣ በወንጌሉ ህግ፣ ከእግዚአብሔር መንግስት ጋር ግኑኝነት ባላቸው ሁሉም ነገሮች፣ ለእውቀታችሁ አስፈላጊ የሆኑትን ፈጽማችሁ ለእንድትማሩ ዘንድ፤
፸፱ ሀበሰማይና ምድር፣ እናም ከምድር በታች፣ ስላሉትም ነገሮች፤ ስለነበሩት ነገሮች፣ ስለአሉ ነገሮች፣ እና በቅርብም ስለሚሆኑት ነገሮች፤ በቤት ስላሉም ነገሮች፣ በሌሎች ሀገሮች ስላሉትም ነገሮች፤ ስለህዝብ ለጦርነቶች እና አወዛጋቢ ጉዳዮች፣ እና በምድር ላይ ስላሉት ፍርዶች፤ እና የሀገራት እና የመንግስታትም እውቀቶች በፍጹም እንድትማሩ ዘንድ፣ ጸጋዬ ከእናንተ ጋር ይሆናል—
፹ በተጠራችሁበት ጥሪ፣ እና በልዩ ሀላፊነት በሰጠኋችሁ ተልዕኮ፣ ጥሪዎቻችሁን እንድታጎሉ በምልካችሁ ጊዜ በሁሉም ነገሮች ትዘጋጁ ዘንድ ጸጋዬ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
፹፩ እነሆ፣ የላኳችሁ ሀእንድትመሰክሩ እና ሰዎችን ለእንድታስጠነቅቁ ነው፣ እናም የተጠነቀቀው ሰው ባልንጀራውን ማስጠንቀቁ አስፈላጊ ነው።
፹፪ ስለዚህ፣ ምክንያትም አይኖራቸውም፣ እና ኃጢአቶቻቸውም በራሳቸው ላይ ናቸው።
፹፫ ከጊዜው ሀቀድሞ ለየሚፈልገኝም ያገኘኛል፣ እና አይተውም።
፹፬ ስለዚህ ለመጨረሻ ጊዜ ሀበአህዛብ መካከል በመሄድ በአገልግሎታችሁ ፍጹማን ትሆኑ ዘንድ፤ የጌታም አንደበት የጠራቸውን ሁሉ ለማምጣት፤ ህግን ለለማሰር እና ምስክርንም ለማተም እና ከሚመጣውም የፍርድ ሰአት ቅዱሳንን ታዘጋጁ ዘንድ ቆዩ እናም ተግታችሁም ስሩ።
፹፭ ነፍሳቸውም በዚህም ሆነ በሚመጣው አለም ክፉዎችን የሚጠብቀውን፣ ሀየርኩሰጥ ጥፋት የሆነውን፣ የእግዚአብሔር ቁጣ ያመልጥ ዘንድ ቅዱሳንን ታዘጋጁ ዘንድ ቆዩ እናም ተግታችሁም ስሩ። እውነት እላችኋለሁ የጌታ አንደበት ለእስኪጠራቸው ድረስ የመጀመሪያ ያልሆኑት ሽማግሌዎች በወይኑ ስፍራ መስራታቸውን ይቀጥሉ፤ ሰአታቸው ገና አልደረሰምና፤ ልብሶቻቸውም ከዚህ ትውልድ ደም ሐየነጹ አይደሉም።
፹፮ ሀነጻ ሆናችሁ በተፈጠራችሁበትም ለአርነት ጸንታችሁ ቁሙ፤ ሐበኃጢአትም ራሳችሁን መአትጥመዱ፣ ነገር ግን፣ ጌታ እስከሚመጣ ድረስ፣ እጆቻችሁን ሠእንዲጸዱ አድርጉ።
፹፯ ለብዙ ቀናት ሳይቆይ እና ሀምድርም እንደሰካራም ሰው ለትፍገመገማለች እና ወዲህና ወዲያ ትናወጣለች፣ እና ሐጸሀይም ፊቷን ትሰውራለች፣ ብርሀኗንም ትከለክላለች፤ እና ጨረቃም መበደም ትርሳለች፤ እና ሠከዋክብትም እጅግ ይቆጣሉ፣ እናም የበለስ ፍሬ ከበለስ እንደሚወድቅም ራሳቸውን ይጥላሉ።
፹፰ እና ከምስክርነታችሁ በኋላ በህዝብ ላይ ንዴት እና ቁጣ ይመጣል።
፹፱ ከምስክርነታችሁ በኋላ፣ በመካከሏ ሁከት የሚያመጣ የምድር ሀመናወጥ ምስክርነት ይመጣል፣ እና ሰዎችም ወደ ምድር ይወድቃሉ እናም ለመነሳትም ይሳናቸዋል።
፺ እና ደግሞም የነጎድጓድ፣ እና የመብረቅ ሀድምፅ፣ እና የማእበል ድምፅ፣ እና ከገደባቸው በላይ ራሳቸውን በሚወረውሩ የባህር ማዕበል ድምፅ ምስክርነት ይመጣል።
፺፩ እና ሁሉም ነገሮች ሀበሁከት ውስጥ ይሆናሉ፣ እና በእርግጥም፣ የሰዎች ልብ በፍርሀት ይደክማል፤ ፍርሀት በሁሉም ሰዎች ላይ ይመጣልና።
፺፪ እናም፣ ተዘጋጁ፣ ተዘጋጁ፣ በምድር የምትኖሩ ሆይ፤ የእግዚአብሔር ፍርድ መጥቷልና። እነሆ፣ እና አስተውሉ፣ ሀሙሽራው መጥቷል፤ ከእርሱ ጋር ለመገናኘትም ውጡ በማለት፣ በከፍተኛ ድምፅ በመጮህ፣ የእግዚአብሔርን መለከት በመንፋት፣ ለመላዕክትም በሰማይ መካከል ይበራሉ።
፺፫ እና ወዲያውም በሰማይ ሀታላቅ ምልክት ይታያል፣ እናም ሁሉም ሰዎች አብረው ያዩታል።
፺፬ እና ሌላም መልአክ መለከቱን እንዲህ በማለት ይነፋል፥ ህዝብን ሁሉ ሀየዝሙቷን ቁጣ ወይን ጠጅ እንዲጠጡ ያደረገችው፣ የእግዚአብሔን ቅዱሳን የምታሳድድ፣ ደማቸውን የምታፈስ—በብዙ ውሀዎች እና በባህር ደሴቶች ላይ የተቀመጠችው—ያቺ ለታላቅ ሐቤተክርስቲያን፣ የርኩሰት መእናት፣ እነሆ፣ የምድር ሠእንክርዳድ እርሷ ነች፤ አንድ ላይ ታስራለች፤ እስሯም ተጠናክሯል፣ እና ማንም ሰው ሊፈታው አይችልም፤ ስለዚህ፣ ረለመንደድ ተዘጋጅታለች። እና መለከቱም ረጅም እና ጉልህ ይሆናል፣ እና ሁሉም ህዝብ ይሰሙታል።
፺፭ እና በሰማይም ለግማሽ ሰአት ያህል ሀጸጥታ ይሆናል፤ እና ወዲያውም፣ መጽሐፍ ለጥቅልል ከተጠቀለለ በኋላ እንደሚዘረጋ፣ የሰማይ መጋረጃዎች ይዘረጋሉ፣ እናም የጌታ ሐፊትም ይገለጣል፤
፺፮ እና በህይወት በምድር ላይ ያሉት ቅዱሳን በቅፅበት ይለወጣሉ እና እርሱን ያገኑት ዘንድም ሀይነጠቃሉ።
፺፯ እና በየመቃብራቸው ያንቀላፉትም ሀይነሳሉ፣ መቃብሮቻቸውም ይከፈታሉና፤ እና እነርሱ ደግመውም በሰማይ አምድ መካከል እርሱን ለመቀበል ይነጠቃሉ—
፺፰ መጀመሪያ ከእርሱ ጋር የሚወርዱት፣ እና በምድርና በመቃብራቸው ያሉት፣ እርሱን ለመቀበል የተነጠቁት፣ እነርሱም የክርስቶስ፣ ሀየመጀመሪያ ፍሬዎች፣ ናቸው፤ እና ይህም ሁሉ የሚሆነው የእግዚአብሔር መልአክ መለከት ድምፅ ሲሰማ ነው።
፺፱ ከዚህ በኋላም ሌላ መልአክ፣ ሁለተኛው መለከት፣ ያሰማል፤ ከዚያም፣ ወንጌልን ለመቀበልና እንደሰዎች በሥጋ ሀይፈረድባቸው ዘንድ፣ ለበወህኒ ለእነርሱ የተዘጋጀውን ድርሻቸውን የተቀበሉት፣ በመምጫው ጊዜ የክርስቶስ የሆኑት ቤዛነትም ይመጣል።
፻ ደግሞም፣ ሶስተኛው መለከት የሆነው ሌላ መለከት ይነፋል፤ ከዚያም የሚፈረድባቸውና ሀበኩነኔ የሚገኙት ሰዎች ለነፍሳት ይመጣሉ፤
፻፩ እነዚህም የቀሩት ሀሙታን ናቸው፤ እና ይህ ለሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፣ ያም እስከምድር ፍጻሜም ድረስ፣ በሕይወት አይኖሩም።
፻፪ እና አራተኛው መለከት የሆነው ሌላ መለከትም እንዲህ በማለት ይነፋል፥ እስከታላቅ እና መጨረሻው ዘመን፣ እንዲሁም እስከፍጻሜው፣ ድረስ ከሚቀሩት መካከል ሀቆሽሸው የሚቀሩ አሉ።
፻፫ እና አምስተኛው መለከት የሆነው፣ ሀዘለአለማዊውን ወንጌል በሰማይ መካከል በመብረር ለሀገር ለነገድ ለቋንቋ ለህዝብ የሚሰብከው አምስተኛው መልአክ፣ ሌላውን መለከት ይነፋል፤
፻፬ ይህም፣ ለህዝብ ሁሉ በማለት፣ የመለከቱ ድምፅ ይሆናል፣ በሰማይና በምድር፣ እና ከምድር በታች ላሉት—ሀሁሉም ጆሮዎች ይሰሙታልና፣ እና የመለከቱንም ድምፅ እንዲህ ሲል ሲሰሙም፣ ጉልበት ሁሉ ለይንበረከካል ምላስም ሁሉ ይናዘዛል፥ እግዚአብሔርን ሐፍሩ፣ እና በዙፋኑ ላይ ከዘለአለም እስከ ዘለአለም ለሚቀመጠው ክብሩን ስጡ፤ የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና።
፻፭ እና ደግሞም፣ ስድስተኛው መልአክ የሆነው ሌላ መልአክም መለከቱን እንዲህ በማለት ይነፋል፥ ህዝብን ሁሉ የዝሙቷን ቁጣ ወይን ጠጅ እንዲጠጡ ያደረገችው ሀወድቃለች፤ ወድቃለች፣ ወድቃለች!
፻፮ እና ዳግም፣ ሰባተኛው መልአክ የሆነው ሌላ መልአክ መለከቱን እንዲህ በማለት ይነፋል፥ ተፈፅሟል፤ ተፈፅሟል! የእግዚአብሔር ሀበግ ለአሸንፎታል እናም መጥመቂያውን፣ እንዲሁም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያን፣ ብቻውን ሐረግጦታል።
፻፯ ከዚያም መላእክቱ የሀይሉን የክብር አክሊል ይደፋሉ፣ እና ሀቅዱሳንም ለበክብሩ ይሞላሉ፣ እና ሐውርሳቸውን ይቀበላሉ እና ከእርሱም ጋር መእኩል ይደረጋሉ።
፻፰ ከዚያም የመጀመሪያው መልአክ መለከቱን ዳግም በሚኖሩት ጆሮዎች ላይ ያሰማል፣ እና የሰዎችን የሚስጥር ስራዎችና ሀበመጀመሪያው ሺህ አመታት የእግዚአብሔርን ታላቅ ስራዎች ለይገልጣል።
፻፱ ከዚያም ሁለተኛው መልአክ መለከቱን ይነፋል፣ እና የሰዎችን የሚስጥር ስራዎች፣ እና የልባቸውን ሀሳብና ስሜታቸውን፣ እና በሁለተኛው ሺህ አመታት የእግዚአብሔርን ታላቅ ስራዎች ይገልጣል—
፻፲ እናም ሰባተኛው መልአክ መለከቱን እስከሚነፋ ድረስ ይቀጥላል፤ እና በምድር ላይ እና በባህር ላይ ይቆማል፣ እና ሀዘመንም እንደሚፈጸም በዙፋኑ ላይ በሚቀመጠው ስም ይምላል፤ እና የቀደመውንም እባብ፣ ዲያብሎስ የሚባለው፣ ለሰይጣንም ይያዛል፣ እና ሐለአንድ ሺህ ለሚሆን ዘመንም አይፈታም።
፻፲፩ ከዚያም ሰራዊቱን ለመሰብሰብ ይችል ዘንድ ለትንሽ ዘመን ሀይለቀቃል።
፻፲፪ እና ሰባተኛው መልአክ ሀሚካኤል፣ እንዲሁም የመላእክት አለቃው፣ ሰራዊቱን፣ እንዲሁም የሰማይ ሰራዊትን፣ ይሰበስባል።
፻፲፫ እና ዲያብሎስም ሰራዊቱን ይሰበስባል፤ እንዲሁም የሲኦል ሰራዊትን፣ እና ከሚካኤልና ከሰራዊቱ ጋር ለመዋጋት ይመጣል።
፻፲፬ ከዚያም የታላቁ እግዚአብሔር ሀጦርነት ይመጣል፤ እና በቅዱሳን ላይ ከዚህ በኋላ ሀይል እንዳይኖራቸው፣ ዲያብሎስና ሰራዊቱ ወደራሳቸው ስፍራም ይጣላሉ።
፻፲፭ ሚካኤል ጦርነታቸውን ይዋጋላቸዋልና፣ እና በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውን፣ እንዲሁም የበጉን፣ ዙፋን ሀየሚፈልገውን ያሸንፋል።
፻፲፮ ይህም የእግዚአብሔርና ሀየተቀደሱት ክብር ነው፤ እና ከዚህም በኋላ ለሞትን አይቀምሱም።
፻፲፯ ስለዚህ፣ ሀባልንጀሮቼ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እንዳዘዝኳችሁ የክብር ስብሰባችሁን ጥሩ።
፻፲፰ እና ሁሉም እምነት ስለሌላቸው፣ ተግታችሁ ፈልጉ እና እርስ በርሳችሁም ሀየጥበብ ቃላትን ለተማማሩ፤ አዎን፣ ከተመረጡት ሐመጽሀፍትም የጥበብን ቃላት ፈልጉ፤ እውቀትን፣ እንዲሁም በጥናትና ደግሞም በእምነት፣ እሹ።
፻፲፱ ራሳችሁን አደራጁ፤ አስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ አዘጋጁ፤ ሀቤትን፣ እንዲሁም የጸሎትን ቤት፣ የጾምን ቤት፣ የእምነትን ቤት፣ የእውቀትን ቤት፣ የክብርን ቤት፣ የስርዓትን ቤት፣ የእግዚአብሔርን ቤት መስርቱ፤
፻፳ በእዚህም መግባታችሁ በጌታ ስም ይሆን ዘንድ፤ መውጣታችሁም በጌታ ስም ይሆን ዘንድ፤ ሰላምታችሁም፣ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጆቻችሁን በማንሳት፣ በጌታ ስም ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔርን ቤት መስርቱ።
፻፳፩ ስለዚህ፣ ጥቅም የሌለውን ንግግራችሁን ሁሉ፣ ሀሳቆችን ሁሉ፣ ለከፍተኛ ፍላጎታችሁን ሁሉ፣ ሐኩራታችሁን እና ተራ አስተሳሰባችሁን ሁሉ፣ እና ክፉ ድርጊታችሁን ሁሉ መአቁሙ።
፻፳፪ ከመካከላችሁም መምህር መድቡ፣ እና ሁሉም ታናጋሪ እንዲሆኑ አታድርጉ፤ ነገር ግን፣ ሁሉም ሲናገሩ ሁሉም ይታነጹ ዘንድ፣ እና እያንዳንዱም ሰው እኩል ባለመብት ይሆን ዘንድ፣ አንድ በአንድ በተራ እንዲናገር አድርጉ እና ሁሉም የሚነገረውን እንዲሰሙ አድርጉ።
፻፳፫ እርስ በርሳችሁ ሀመዋደዳችሁን አረጋግጡ፤ ለትምክህተኞች አትሁኑ፤ በወንጌሉ አስፈላጊ እንደሆነም እርስ በርስ መካፈልን ተማሩ።
፻፳፬ ሀስራ ፈት መሆንን አቁሙ፤ እርኩስ መሆንንም አቁሙ፤ እርስ በራስ ለስህተት መፈለግን አቁሙ፤ አስፈላጊ ከሆነው በላይ መተኛትንም አቁሙ፤ እንዳትደክሙ፣ ወደመኝታችሁ በጊዜ ሂዱ፤ ሰውነቶቻችሁ እና አዕምሮዎቻችሁ ይነቃቁ ዘንድም በማለዳ ተነሱ።
፻፳፭ እና ከሁሉም በላይ፣ የፍጹምነትና ሀየሰላም ማሰሪያ የሆነውን ለልግስና፣ እንደ ካባ፣ ልበሱት።
፻፳፮ ሀእስከምመጣም ድረስ ሳትታክቱ ዘንድ፣ ዘወትር ለጸልዩ። እነሆ እናም አስተውሉ፣ በቶሎ እመጣለሁ፣ እናም እናንተንም ወደራሴ እወስዳችኋለሁ። አሜን።
፻፳፯ ደግሞም፣ ለነብያቱ ሀትምህርት ቤት አመራር፣ እንዲሁም ለቤተክርስቲያን ለሹማምንቶች ሁሉ፣ ወይም በሌላ ቃል፣ ከሊቀ ካህናት ጀምሮ እስከ ዲያቆን ድረስ በቤተክርስቲያኑ እንዲያገለግሉ ለተጠሩት ተዘጋጅቶ፣ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ እንዲማሩበት የተመሰረተውን ቤት ስርዓት በሚመለከት—
፻፳፰ እናም ይህም የትምህርት ቤቱ አመራር ቤት ስርዓት ይሆናል፥ ፕሬዘደንት ወይም መምህር እንዲሆን የተሾመው በሚዘጋጅለት ቤት ውስጥ በስፍራው ቆሞ ይገኝ።
፻፳፱ ስለዚህ፣ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በጎላ ንግግር ሳይሆን፣ በቤቱ ውስጥ ያሉት ተሰብሳቢዎች ቃላቶቹን በጥንቃቄና በግልፅ በሚሰሙበት ስፍራ መጀመሪያ ይሁን።
፻፴ እና ወደ እግዚአብሔር ቤት ውስጥ ሲመጣም፣ በቤቱ ውስጥ የመጀመሪያ መሆን ይገባዋልና—እነሆ፣ ይህም ድንቅ ነው፣ ምሳሌም ይሆን ዘንድ—
፻፴፩ የዘለአለማዊ ቃል ኪዳን ምልክት ወይም ማስታወሻም ይሆን ዘንድ፣ በጸሎት በእግዚአብሔር ፊት በመንበርከክ እራሱን ሀያቅርብ።
፻፴፪ እናም ከእርሱ በኋላ ማንም ሲገባ፣ መምህሩ ይነሳ፣ እና ወደሰማይ በተዘረጉ እጆች፣ አዎን፣ እንዲሁም በቀጥታ፣ ወንድሙን ወይም ወንድሞችን በእነዚህ ቃላት ሰላም ይበላቸው፥
፻፴፫ እናንት ወንድም ወይም ወንድሞች ናችሁ? በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ በምልክት ወይም በዘለአለማዊ ቃል ኪዳን ማስታወሻ ሰላም እላችኋለሁ፣ በዚህም ቃል ኪዳን፣ በማይለወጥ፣ በማይነቃነቅ፣ እና በማይቀየር ቁርጥ ውሳኔ፣ በእግዚአብሔር ጸጋ በፍቅር እስር ውስጥ፣ በእግዚአብሔር ትእዛዛት ሁሉ ያለእንከን፣ በምስጋና መስጠት፣ ከዘለአለም እስከዘለአለም ጓደኛችሁና ሀወንድማችሁ ለመሆን ወደ ለማህበርተኛነት እቀበላችኋለሁ። አሜን።
፻፴፬ እናም ለዚህ ሰላምታ ብቁ ሆኖ የማይገኘውም ከመካከላችሁ ምንም ስፍራ አይኑረው፤ ቤቴ በእርሱ ሀእንዲረከስ አትፈቅዱምና።
፻፴፭ እና የሚገባውና በፊቴ ታማኝ የሚሆነው፣ እና ወንድም የሆነው፣ ወይም ወንድሞችም ከሆኑ፣ ወደሰማይ በተዘረጉ እጆች፣ በአንድ አይነት ጸሎት እና ቃል ኪዳን፣ ወይም በአንድ አይነት ምልክት አሜን በማለት ለፕሬዘደንት ወይም ለመምህሩ ሰላምታ ይሰጣሉ።
፻፴፮ እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ይህም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ፣ በነቢያትም ትምህርት ቤት ውስጥ፣ እርስ በርስ ሰላምታ የምትሰጣጡበት ምሳሌ ነው።
፻፴፯ እናም መሸሸጊያ፣ ለምትታነጹበት የመንፈስ ቅዱስ ሀድንኳን ይሆን ዘንድ፣ በጌታ ቤት፣ እንዲሁም በነቢያት ትምህርት ቤት ውስጥ፣ መንፈስ በሚናገረው በምታደርጉት ሁሉ ጸሎት እና ምስጋና በመስጠት እንድታደርጉ ተጠርታችኋል።
፻፴፰ እና ከዚህ ትውልድ ሀደም ንጹህ ያልሆነን በመካከላችሁ ማንንም ወደ እዚህ ትምህርት ቤት አትቀበሉ።
፻፴፱ እና እርሱም እግርን ሀማጠብ በሆነ ስርዓት ተቀበሉት፣ ለዚህም ምክንያት ነበር የእግር ማጠብ ስነስርዓት የተመሰረተው።
፻፵ ደግሞም፣ የእግር ማጠብ ስርዓት የሚከናወነው በፕሬዘደንቱ፣ ወይም በቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎች አመራር ነው።
፻፵፩ ይህም የሚጀምረው በጸሎት ነው፤ እና ዳቦው እና ወይኑ ሀከተሰጠ በኋላ፣ እኔን በሚመለከት በዮሐንስ ምስክር ምዕራፍ አስራ ሶስት ውስጥ በምስክርነት በሰጠው ለምሳሌ ራሱን ያልብስ። አሜን።