ክፍል ፹፪
በሚያዝያ ፳፮፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.)፣ በኢንድፐንደንስ፣ በጃክሰን የግዛት ክፍል ሚዙሪ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። ጊዜው በቤተክርስቲያኗ ሊቀ ካህናት እና ሽማግሌዎች የምክር ስብሰባ ላይ ነበር። በምክር ስብሰባው ላይ፣ ከዚህ በፊት በጥር ፳፭፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) በአምኸርስት ኦሀዮ ውስጥ በሊቀ ካህናት፣ በሽማግሌዎች፣ እና በአባላት ጉባኤ ላይ ለዚህ ሀላፊነት የተሾመው ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንደ ታላቅ ክህነት ፕሬዘደንት ተደግፎ ነበር (የክፍል ፸፭ ርዕስን ተመልከቱ)። ይህ ራዕይ ከዚህ በፊት (ክፍል ፸፰) የቤተክርስቲያኗን ንግድ እና የማተም ጥረቶችን የሚቆጣጠር የትብብር ድርጅት ተብሎ ይታወቅ የነበረውን ድርጅት (በኋላም፣ በጆሴፍ ስሚዝ አመራር፣ “ስርዓት” የሚለው ቃል “ድርጅት” የሚለውን ተካ) እንዲመሰረት ተደጋጋሚ መመሪያ ሰጠ።
፩–፬፣ ብዙ ለተሰጠው፣ ከእርሱ ብዙ ይጠበቃል፤ ፭–፯፣ ጭለማ በአለም ላይ ነግሷል፤ ፰–፲፫፣ እሱ ያለውን ስናደርግ ጌታ በቃሊ ይታሰራል፤ ፲፬–፲፰፣ ፅዮን በውበት እና በቅድስና መጨመር አለባት፤ ፲፱–፳፬፣ እያንዳንዱ ሰው ለባልንጀራው መልካም ሊሻ ይገባዋል።
፩ አገልጋዮቼ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እርስ በርስ መተላለፋችሁን ሀይቅር ብትባባሉ፣ እኔ ጌታ እንዲሁ ይቅር እላችኋለሁ።
፪ ይህም ቢሆን፣ በመካከላችሁ ታላቅ ኃጢአት የሰሩ አሉ፤ አዎን፣ ሀሁላችሁም ኃጢአት ሰርታችኋል፤ ነገር ግን፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ተጠንቀቁ፣ እናም ከኃጢአት ተቆጠቡ፣ አለበለዚያ የበለጠ ፍርድ በራሳችሁ ላይ ይወድቅባችኋል።
፫ ሀብዙ ለተሰጠው ከእርሱ ብዙ ለይጠበቅበታልና፤ እናም በታላቅ ሐብርሀን ላይ መኃጢአት የሚሰራ የባሰውን ፍርድ ይቀበላል።
፬ ሀለራዕዮች ስሜን ትጠራላችሁ፣ እናም እኔ እሰጣችኋለሁ፤ እናም የምሰጣችሁን፣ የምለውን ባትጠብቁ፣ ህግ ተላላፊዎች ትሆናላችሁ፤ እናም ለፍትህና ፍርድ በህጌ ላይ የተመደቡ ቅጣት ናቸው።
፭ ስለዚህ፣ ለአንዱ የምናገረው ለሁሉም የተናገርሁት ነው፥ ነቅታችሁ ሀጠብቁ፣ ለጠላትም ተፅዕኖውን እያስፋፋ ነው፣ እናም ሐጭለማም ነግሷል፤
፮ እናም የእግዚአብሔር ቁጣ በምድር ኗሪዎች ላይ ተቀጣጥሏል፣ እናም ማንም መልካምን አያደርግም፣ ሁሉም መንገዳቸውን ሀስተዋል።
፯ እናም አሁን፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እኔ ጌታ እናንተን በምንም ሀኃጢአት ሀላፊ አላደርጋችሁም፤ መንገዳችሁን ሂዱ ዳግመኛም ኃጢአትን አትስሩ፤ ነገር ግን ኃጢአት ለሚሰራው ነፍስ ለየቀድሞው ኃጢአት ይመለስበታል፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ።
፰ እና ደግሜም፣ እላችኋለሁ፣ ለእናንተ ያለኝ ፈቃዴን ትረዱ ዘንድ ሀአዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤
፱ ወይም፣ በሌላ አባባል፣ ለደህንነታችሁ ይሆንላችሁ ዘንድ፣ በፊቴ ምን ሀማድረግ እንዳለባችሁ መመሪያ እሰጣችኋለሁ።
፲ እኔ ጌታ የምለውን ስታደርጉ በቃሌ ሀእታሰራለሁ፤ ነገር ግን የምለውን ባታደርጉ፣ የተስፋ ቃል የላችሁም።
፲፩ ስለዚህ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ፍርድ ወዲያውኑ ሊመጣ ካልሆነ በቀር፣ በተለያዩ ሀላፊነታችሁ አገልጋዮቼ ኤድዋርድ ፓርትሪጅ እና ኒወል ኬ ውትኒ፣ ኤ ስድኒ ጊልበርት እና ስድኒ ሪግደን፣ እና አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ፣ እና ጆን ዊትመር እና ኦሊቨር ካውድሪ፣ እና ደብሊው ደብሊው ፌልፕስ እና ማርቲን ሀሪስ በመተላለፍ ሊሰበር በማይቻል ሀስምምነት እና ቃል ኪዳን ይስማሙ—
፲፪ የድሆችን ጉዳዮች፣ በፅዮን ምድር እና በከርትላንድ ምድር ውስጥ ከኤጲስ ቆጶስ አመራር ጋር ግንኙነት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ ለማስተዳደር በቃል ኪዳን ይስማሙ፤
፲፫ የከርትላንድን ምድር በራሴ ጊዜ ለልዑል እግዚአብሔር ቅዱሳን ጥቅም፣ እና ለፅዮን ሀካስማ፣ ቀድሼዋለሁና።
፲፬ ሀፅዮን በውበት፣ እና በቅድስና፣ ልትልቅ ይገባል፤ ድንበሮችዋም ሊሰፉ፣ ካስማዎቿም ሊጠናከሩ፣ አዎን፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ፅዮን ልትነሳ እና ለየውበት ልብሷን ልትለብስ ይገባል።
፲፭ ስለዚህ፣ በዚህ ቃል ኪዳን ራሳችሁን እንድታስተሳስሩ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፣ እናም ይህም በጌታ ህግጋት መሰረት መደረግ አለበት።
፲፮ እነሆ፣ ይህም በእኔ ዘንድ መልካም የሚሆንላችሁ ጥበብም ነው።
፲፯ እናም እናንተም ሀእኩል ትሆኑ ዘንድ ይገባል፣ ወይም በሌላ አባባል፣ የሀላፊነታችሁን ጉዳዮች የማስተዳደር ጥቅም፣ እያንዳንዱ ሰው፣ ፍላጎቱ ትክክለኛ እስከሆነ ድረስ፣ በፍላጎቱ እና በሚያስፈልገው፣ በንብረቶች ላይ እኩል መብት ይኖረዋል—
፲፰ እናም ይህ ሁሉ ለህያው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ጥቅም፣ እያንዳንዱ ሰው ሀችሎታውን ያሻሽል ዘንድ፣ እያንዳንዱም ሰው ሌሎች ችሎታዎችን ያገኝ ዘንድ፣ አዎን፣ ከአንድ መቶ እጥፍ፣ የቤተክርስቲያኗ ሁሉ የጋራ ንብረት እንዲሆን ወደ ጌታ ለጎተራ ያገባ ዘንድ—
፲፱ እያንዳንዱ ሰው የባልንጀራውን ፍላጎት እንዲሻ፣ እናም ለሁሉም ነገሮች ሙሉ ሀአይኑን ወደ እግዚአብሔር ክብር ያደርግ ዘንድ ነው።
፳ ይህ ስርዓት፣ ኃጢአት ካልሰራችሁ በስተቀር፣ እንደ ዘለአለም ሀስርዓት ለእናንተ፣ እና ለእናንተ ተተኪዎቻችሁ መድቤአለሁ።
፳፩ እናም በዚህ ቃል ኪዳን ላይ ኃጢአት የሚፈፅም ነፍስ፣ እና ልቡን በዚህ ላይ የሚያደነድን፣ በቤተክርስቲያኔ ህግጋት መሰረት ይደረግባቸዋል፣ እናም እስከቤዛ ቀን በሰይጣን ሀእንዲጎሰሙ ይሰጣሉ።
፳፪ እና አሁን፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እና ይህ ጥበብ ነው፣ በዓመፃ ገንዘብ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ፣ እናም እነዚህም አያጠፏችሁም።
፳፫ ፍርድን ለእኔ ብቻ ተዉት፣ የእኔ ነውና እናም ሀእከፍለዋለሁ። ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን፣ በረከቶቼ ከእናንተ ዘንድ ይኑሩ።
፳፬ ከፅናታችሁ ካልወደቃችሁ፣ ሀመንግስትም የእናንተ ናትና፣ እናም ለዘለአለምም ትሆናለች። እንዲሁም ይሁን። አሜን።