ክፍል ፸፰
በመጋቢት ፩፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዮ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። በዚያ ቀን ነቢዩ እና ሌሎች መሪዎች የቤተክርስቲያኗን ጉዳይ ለመወያየት ተሰብስበው ነበር። ይህም ራዕይ ነቢዩ፣ ስድኒ ሪግደን፣ እና ኒዌክ ኬ. ውትኒ ወደ ምዙሪ በመጓዝ እና ፅዮንን ለመመስረት እና ድሆችን ለመርዳት ገንዘብ የሚያስገኝ፣ የቤተክርስቲያኗን የንግድ እና የማተም ጥረቶችን የሚረዳ “ድርጅት” እንዲመሰርቱ መመሪያ የሚሰጥ ነበር። ይህም ድርጅት፣ የትብብር ድርጅት ተብሎ የሚታወቀው፣ የተመሰረተው በሚያዝያ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) እና የፈረሰው በ፲፰፻፴፬ (እ.አ.አ.) ነበር (ክፍል ፹፪ን ተመልከቱ)። ከፈረሰ በኋላ፣ በጆሴፍ ስሚዝ አመራር፣ “የድሀውን ህዝቤ የጎተራ ስራዎችን” የሚለው “የንግድ እና የማተሚያ ድርጅት” የሚለውን በራዕይ ውስጥ ቀይሯል፣ እናም “ስርዓት” የሚለው ቃል “ድርጅት” የሚለውን ቃል ተክቷል።
፩–፬፣ ቅዱሳን ጎተራ ማዘጋጀት እና መመስረት ይገባቸዋል፤ ፭–፲፪፣ ንብረቶቻቸውን በጥበብ መጠቀም ወደ ደህንነት ይመራል፤ ፲፫–፲፬፣ ቤተክርስቲያኗ ከምድራዊ ሀይላት ጥገኝነት ነጻ መሆን ይገባታል፤ ፲፭–፲፮፣ ሚካኤል (አዳም) በቅዱሱ (ክርስቶስ) አመራር ያገለግላል፤ ፲፯–፳፪፣ ታማኞች ብጹአን ናቸው፣ ሁሉንም ነገሮች ይወርሳሉና።
፩ ጌታ ለጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ እንዲህ ሲል ተናገረው፥ ራሳችሁን የሰበሰባችሁት፣ በቤተክርስቲያኔ ሀታላቅ ክህነት የተሾማችሁት አድምጡኝ፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ፤
፪ እናም በፊቴ ባቀረባችሁት ነገር ደህንነት ለእናንተ ይሆንላችሁ ዘንድ፣ ከበላይ ሀየሾማችሁን፣ በጆሮአችሁ የጥበብ ቃላትን የሚናገራችሁን የእርሱን ለምክር ስሙ፣ ይላል ጌታ አምላክ።
፫ በእውነትም እንዲህ እላችኋለሁ፣ ጊዜው መጥቷል፣ እና አሁንም ተቃርቧል፤ እናም እነሆ፣ እናም ተመልከቱ፣ በዚህ ስፍራ እና ሀበፅዮን ምድርም፣ ለየድሀውን ህዝቤ ሐየጎተራ ስራዎችን የሚቆጣጠር እና የሚመሰረት የህዝቤ መድርጅት መኖር አለበት—
፬ ይህም ለቤተክርስቲያኔ ቋሚ እና ዘለአለማዊ አመሰራረት እና ስርዓት፣ ራሳችሁ የተቀበላችሁትን ምክንያት ወደፊት ለመግፋት፣ ለሰው ደህንነት እና በሰማይ ላለው ለአባታችሁ ክብር፤
፭ ሰማያዊ ነገሮችን ለማግኘትም፣ እናንተም በሰማያዊ ነገሮች፣ አዎን፣ እናም በምድራዊ ነገሮችም ሀበእኩል እንድትተሳሰሩ ዘንድ ነው።
፮ በምድራዊ ነገሮች እኩል ካልሆናችሁ ሰማያዊ ነገሮችን ለማግኘት እኩል አትሆኑምና፤
፯ ሀበሰለስቲያል አለም ውስጥ ስፍራን እንድሰጣችሁ ከፈለጋችሁ፣ ያዘዝኳችሁን እና የምጠብቅባችሁን ነገሮች ለበማድረግ ራሳችሁን ሐማዘጋጀት አለባችሁና።
፰ እናም አሁን፣ ጌታ በእውነት እንዲህ ይላል፣ ሁሉም ነገሮች፣ በእናንተ በዚህ ሀስርዓት አብራችሁ በተጣመራችሁበት፣ ለእኔ ለክብር መደረጋቸው አስፈላጊ ነው፤
፱ ወይም፣ በሌላ ቃላትም፣ አገልጋዬ ኒወል ኬ ውትኒ እና አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ፣ እና አገልጋዬ ስድኒ ሪግደን በፅዮን ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ጋር ይማከሩ፤
፲ አለበለዚያም፣ የተዘጋጁላቸውን ነገሮች ይሰወርባቸውም ዘንድ እና እንዳይገባቸው፣ ሀሰይጣን ልቦቻቸውን ከእውነቱ ሊያርቀው ይሻልና።
፲፩ ስለዚህ፣ በስምምነት ወይም ሊሰበር በማይችል በዘለአለማዊ ሀቃል ኪዳን ራሳችሁን እንድታዘጋጁ እና እንድታደራጁ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።
፲፪ እናም ይህን የሚሰብረውም ሹመቱን እና የቤተክርስቲያን ደረጃውን ያጣል፣ እና እስከቤዛ ቀንም በሰይጣን ሀእንዲንገላታ ይሰጣል።
፲፫ እነሆ፣ ይህም እናንተን የማዘጋጅበት ዝግጅት፣ እናም የተሰጣችሁን ትእዛዝ ለማከናወን ትችሉ ዘንድ የምሰጣችሁ መሰረት እና ምሳሌ ነው፤
፲፬ ሀመከራም የሚመጣባችሁ ቢሆን እንኳ፣ በእኔ አሳብ ቤተክርስቲያኗ ከሰለስቲያል አለም በታች ካሉት ሌሎች ፍጥረቶች ሁሉ በላይ ነጻ ሆና ትቆም ዘንድ፤
፲፭ ለተዘጋጀላችሁ ሀአክሊል ትመጡ፣ እና በብዙ መንግስታት ላይ ለገዢዎች ትሆኑ ዘንድ የማዘጋጅበት ዝግጅት፣ የምሰጣችሁ መሰረት እና ምሳሌ ነው፣ ሐአዳም-ኦንዳይ-አማንን የመሰረተው ጌታ አምላክ፣ የፅዮን ቅዱስ፤
፲፮ ሀሚካኤልን እንደ ልኡል የሾመው፣ እናም እግሮቹን ያጸና፣ እናም በከፍታም ላይ ያስቀመጠው፣ እናም የደህንነትን ቁልፎች፣ የቀናት መጀመሪያ እና የህይወት መጨረሻ በሌለው፣ በቅዱሱ ምክር እና አመራር አማካይነት የደህንነትን ቁልፎች የሰጠው ጌታ አምላክም እንዲህ ይላል።
፲፯ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እናንት ትንሽ ልጆች ናችሁ፣ እናም አብ በእጆቹ ምን አይነት ታላቅ በረከቶች እንዳለው እና ለእናንተም እንዳዘጋጀ ገና አልገባችሁም፤
፲፰ እናም ሁሉንም ነገሮች አሁን ሀመሸከም አትችሉም፤ ይህም ቢሆን፣ ተደሰቱ፣ እንደሚገባችሁ ለእመራችኋለሁና። መንግስት የእናንተ ናት እናም በእዚያም ያሉ በረከቶች የእናንተ ናቸው፣ እናም ሐየዘለአለም ባለጠግነትም የእናንተ ናቸውና።
፲፱ እናም ሁሉንም ነገሮች ሀበምስጋና የሚቀበል እርሱ የከበረ ይሆናል፤ እናም የምድር ነገሮችም፣ እንዲሁም ለበመቶ እጥፍ፣ አዎን በብዙ፣ ለእርሱ ይጨመሩለታልና።
፳ ስለዚህ፣ ያዘዝኳችሁን ነገሮች እንዲሁ አድርጉ፣ ይላል ቤዛችሁ፣ እንዲሁም እናንተን ሀከመውሰዱ አስቀድሞ ሁሉንም ነገሮች የሚያዘጋጀው ለየአህመን ልጅ፤
፳፩ የበኩር ሀቤተክርስቲያን ናችሁና፣ እናም በደመናው ወደላይ ለይወስዳችኋል፣ እናም ለእያንዳንዱም የድርሻውን ይሰጠዋልና።