ክፍል ፳፱
መስከረም ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በፈየት ኒው ዮርክ በስድስት ሽማግሌዎች ፊት በነቢዩ ጆሴፍ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ይህ ራዕይ የተሰጠው ከጉባዔው ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ፣ ከመሰከረም ፳፮፣ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) ጀምሮ ነው።
፩–፰፣ ክርስቶስ የመረጣቸውን ይሰበስባል፤ ፱–፲፩፣ ምፅአቱ አንድ ሺህ ዘመን እንዲጀምር ያደርጋል፤ ፲፪–፲፫፣ አስራ ሁለቱ መላው እስራኤልን ይፈርዳሉ፤ ፲፬–፳፩፣ ምልክቶች፣ መቅሰፍቶች፣ እና ውድመቶች ዳግም መፅአትን ይቀድማሉ፣ ፳፪–፳፰፣ የመጨረሻው ትንሳዔ እና የመጨረሻው ፍርድ አንድ ሺህ ዘመንን ይከተላሉ፤ ፳፱–፴፭፣ ሁሉም ነገሮች ለጌታ መንፈሳዊ ናቸው፤ ፴፮–፴፱፣ ሰይጣን እና ተከታዮቹ የሰውን ልጅ እንዲፈትኑ ከሰማይ ተወርውረዋል፤ ፵–፵፭፣ ውድቀቱ እና የኃጢአት ክፍያው መዳንን ያመጣሉ፤ ፵፮–፶፣ ህፃናት ልጆች በሀጢይት ክፍያው ድነዋል።
፩ ታላቁ ሀእኔ ነኝ ያለውን፣ ለየምህረቱ ክንድ ሐለኃጢአታችሁ ክፍያ የሆንውን፣ የአዳኛችሁን የኢየሱስ ክርስቶስን ድምጽ አድምጡ፤
፪ ድምጼን የሚያደምጡ እና ራሳቸውን በፊቴ ሀዝቅ የሚያደርጉ፣ እና ወደ እኔም በታላቅ ጸሎት የሚጣሩትን ህዝቦቹንም ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ለየሚሰበስበውን የእነርሱን ድምጽ አድምጡ።
፫ እነሆ እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ በዚህ ጊዜ ለኃጢአታችሁ ሀይቅርታን አግኝታችኋል፣ ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ትቀበላላችሁ፤ ነገር ግን ከዚህ የሚብስ ነገር እንዳይመጣባችሁ ዳግመኛ ኃጢአት እንዳትሰሩ አስታውሱ።
፬ እውነት እላችኋለሁ፣ ልክ እንደ ሀመለከትም ድምጽ፣ በደስታ ድምጽ ወንጌሌን ለማወጅ ከአለም ውስጥ ተመርጣችኋልና።
፭ እኔ ሀበመካከላችሁ ስላለሁ እና በአብም ዘንድ ለስለማማልዳችሁ፣ ልባችሁን አንሱ እናም ተደሰቱ፤ እናም ሐመንግስቱን ሊሰጣችሁ መልካም ፈቃዱ ነው።
፮ እናም፣ እንደተጻፈው—እንደ ትእዛዜ በጸሎት ሀአንድ ሆናችሁ ለበእምነት ሐየምትጠይቁትን ማንኛውንም ነገር ትቀበላላችሁ።
፯ እናም በእኔ የተመረጡትን ሀለመሰብሰብ ለተጠርታችኋል፣ ምክንያቱም በእኔ የተመረጡት ሐድምጼን ይሰማሉ እና መልባቸውንም አያደነድኑም፤
፰ ስለዚህ ልባቸውን ሀለማዘጋጀት እና በክፉዎች ላይ በሚላክበትን ለመከራ እና ጭንቀት ቀን ለመቃወም እንዲዘጋጁ፣ በዚህ ምድር ላይ በአንድ ስፍራ ሐእንዲሰበሰቡ አዋጁ ከአብ ዘንድ ወጥቷል።
፱ እነሆ ሰዓቱ ተቃርቧል፣ ምድርም የምትጠፋበትም ዳርሷል፤ እናም ሀትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሰሩ ሁሉ ለገለባ የሚሆኑበት ይሆናሉ፤ በምድር ላይ ኃጢአት እንዳይኖር ሐአቃጥላቸዋለሁ ይላል የሰራዊት ጌታ፤
፲ ሰዓቱ ተቃርቧል፣ እናም በኃዋሪያቴ የተነገረው መፈጸም አለበት፤ ሀእንደተናገሩት እንዲሁ ይፈጸማልና፤
፲፩ ራሴን ከሰማይ በኃይል እና በታላቅ ክብር፣ በሰማይ ሀሰራዊት ጋር እገልጣለሁ፣ እና ለበጽድቅም ከሰዎች ጋር በምድር ላይ ለአንድ ሐሺህ አመታት እኖራለሁ፣ እናም ኃጢአተኞችም መቆም አይችሉም።
፲፪ እናም ዳግም፣ እውነት፣ እውነት፣ እላችኋለሁ፣ በኢየሩሳሌም በአገልግሎቴ ከእኔ ጋር የነበሩት አስራ ሁለቱ ሀሐዋሪያቴ፣ ለበእሳት አምድ በምመጣበት ቀን የጽድቅን ልብስ ለብሰው፣ አክሊልን በራሳቸው ላይ ደፍተው፣ ልክ እንደ እኔው ሐበክብር፣ መላው እስራኤልን መለመፍረድ፣ እንዲሁም የወደዱኝ እና ትእዛዛቴን የጠበቁትን ብቻ ለመፍረድ፣ ከእኔ ጋር በቀኝ በኩል ይቆሙ ዘንድ በአብ ፈቃድ የጸና አዋጅ ወጥቷል።
፲፫ እነሆ ልክ እንደ ሲና ተራራ ሀመለከትም በረጅም እና በጉልህ ይሰማል፣ እናም መላው ምድርም ይናወጣል፣ እናም አዎን በእኔ ለየሞቱትም ሙታን የጽድቅን ሐአክሊል ሊቀበሉ እናም ልክ መእንደ እኔ ሊለብሱ፣ አንድ እንሆን ዘንድ ከእኔ ጋር እንዲሆኑ ወደፊትም ሠይመጣሉ።
፲፬ ነገር ግን፣ እነሆ እውነት እልሀለሁ ይህ ታላቅ ሀቀን ከመምጣቱ በፊት ለፀሀይ ትጨልማለች፣ እናም ጨረቃም ወደ ደምነት ትለወጣለች፣ እናም ከዋክብትም ከሰማይ ይረግፋሉ፣ እናም በላይ በሰማይና በታች በምድርም ታላቅ ሐምልክቶችም ይሆናሉ፤
፲፭ እናም በስዎች መካካልም ሀለቅሶ እና ሐዘን ይሆናል፤
፲፮ እናም ታላቅ ሀየበረዶ አውሎነፋስም የምድርን ሰብል ለማጥፋት ይላካል።
፲፯ እንዲህም ይሆናል፣ በአለም ኃጢአት የተነሳ፣ ንስሀም ስለማይገቡ፣ ሀበኃጢአተኞች ላይ ለበቀልን አደርጋለሁ፣ የቁጣ ጽዋዬም ሞልቷልና፤ ስለሆነም እነሆ፣ ካልሰሙኝ ሐደሜ አያነጻቸውም።
፲፰ ሰለዚህ፣ እኔ ጌታ አምላክ በውስጧ የሚኖሩትን ይይዙ ዘንድ በምድር ላይ ዝንቦችን እልካለሁ፣ እናም ስጋቸውንም ይበላሉ፣ በውስጣቸውም እጭ እንዲያዝ አደርጋለሁ፤
፲፱ እናም እኔን በመቃወም እንዳይናገሩ ሀምላሳቸው እንዳይንቀሳቀስ አደርገዋለሁ፤ ስጋቸው ከአጥንታቸው እናም አይኖቻቸው ከአይን ጉድጓዶቻቸው ላይ ይረግፋሉ።
፳ እናም የጫካ ሀአውሬዎች እናም የሰማይ አዕዋፋት ይበሏቸዋል።
፳፩ እናም ታላቋና ሀየርኩሰት ቤተክርስቲያን፣ እነዚህ ገና ያልተፈጸሙትን ነገሮች ግን መፈጸም ለየሚገባቸውን ነገሮች ነቢዩ ሕዝቅኤል እንደተናገረው፣ እና እኔ ህያው እንደሆንኩ፣ የምድር ሁሉ ሐጋለሞታ የሆነችው መወደምትበላ እሳት ትጣላለች፣ ምክንያቱም የረከሰ አይነግስምና።
፳፪ እናም ዳግም፣ እውነት፣ እውነት፣ እላችኋለሁ አንድ ሀሺህ አመት ሲጠናቀቅ፣ እናም ሰዎች ዳግም አምላካቸውን መካድ ሲጀምሩ፣ ምድርንና የምተዋት ለለጥቂት ጊዜ ይሆናል።
፳፫ እናም ሀመጨረሻው ይመጣል፣ እናም ሰማይ እና ምድር ይጠፋሉ እናም ለያልፋሉ፣ እንዲሁም አዲስ ሰማይ እና ሐአዲስ ምድርም ይሆናል።
፳፬ እነሆ ሁሉም አሮጌ ነገሮች ሀያልፋሉ፣ ሁሉም ነገሮች፣ እንዲሁም ሰማይ እና ምድር እናም በውስጣቸው ያሉት ሁሉ፣ ሰዎች እና አራዊት፣ የሰማይ አዕዋፋት፣ እናም የባህር አሳዎች ሁሉ አዲስ ይሆናሉ፤
፳፭ እናም አንድ ሀጸጉርም ሆነ ጉድፍ ከፊታችሁ እንኳን አይጠፋም፣ የእጄ ስራ ነውና።
፳፮ ነገር ግን እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ምድር ከማለፏ በፊት፣ ሀየመላእክቴ አለቃ ለሚካኤል ሐመለከቱን ይነፋል፣ ከዚያም በኋላ መየሞቱት ሁሉ ይነሳሉ፣ መቃብራቸው ይከፈታልና፣ እናም ወደፊትም ሠይመጣሉ—አዎን ሁሉም ወደፊት ይመጣሉ።
፳፯ እናም ሀጻድቃን ለዘለአለም ህይወት ለበቀኜ ይሰበሰባሉ፤ እናም በግራዬ የሚገኙትን ኃጢአተኞችም በአባቴ ፊት የእኔ እንደሆኑ ለመናገር ያሳፍረኛል፤
፳፰ ስለዚህ እንዲህም እላችኋለሁ—እናንት የተረገማችሁ ሀለዲያብሎስ እና ለመላእክቱ ወደተዘጋጀው ዘለአለማዊ ለእሳት ከፊቴ ሐሂዱ።
፳፱ እናም አሁን፣ እነሆ፣ እላችኋለሁ፣ በፍጹም በማንኛው ጊዜ እንዲመለሱ በአፌ ተናግሬ አላውቅም፣ እኔ ሀወዳለሁበት መምጣት አይችሉም፣ ሀይል የላቸውምና።
፴ ነገር ግን አስታውሱ ሁሉም ፍርዶቼ ለሰዎች አልተሰጡም፤ ከአፌ ቃላት እንደወጡ እንዲሁ ይፈጸማሉ፣ የመንፈሴ ኃይል በሆነው በቃሌ ኃይል ከፈጠርኳቸው ነገሮች ሀፊተኞችም ኋለኞች፣ ኋለኞቸም ፊተኞች ይሆናሉ።
፴፩ በመንፈሴ ሀይል ሀፈጥሬአቸዋለሁና፤ አዎን፣ ለመንፈሳዊ እንዲሁም ስጋዊ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ—
፴፪ የስራዬ ጅማሬ የሆነው በቅድሚያ ሀመንፈሳዊ፣ ሁለተኛ ጊዜአዊዊ፤ እናም ደግሞ የስራዬ ማብቂያ የሆነውን፣ በቅድሚያ ጊዜአዊው፣ እና ሁለተኛም መንፈሳዊው—
፴፫ ለእናንተ ስናገር በተፈጥሮ ትረዱ ዘንድ ነው፤ ነገር ግን ለእኔ ለስራዬ ሀመጨረሻም ሆነ መጀመሪያ የለውም፤ ነገር ግን ለእናንተ ተረዱት ዘንድ ተሰጥቷችኋል፣ ምክንያቱም እኔን ጠይቃችኋል እናም ተስማምታችኋልና።
፴፬ ስለዚህ፣ እውነት እላችኋለሁ ሁሉም ነገሮች ለእኔ መንፈሳዊ ናቸው፣ እናም በማንኛውም ጊዜ ቢሆን፣ ለሰው ወይም ለሰው ልጆች፣ ወይም እኔ ለፈጠርኩት ለአባታችሁ አዳምም፣ ጊዜያዊ የሆነ ህግ አልሰጠኋቸውም።
፴፭ እነሆ፣ ለእርሱ ራሱን ሀእንዲወክል ሰጥቸዋለሁ፣ እናም ለትእዛዛትን ሰጠሁት ነገር ግን ጊዜአዊ ትእዛዝን አልሰጠሁትም፣ ትእዛዛቴ መንፍሳዊ ናቸውና፤ ተፍጥሯዊ ሆነ ጊዜያዊ፣ እንዲሁም ስጋዊ ወይም ስሜታዊ አይደሉም።
፴፮ እናም እንዲህም ሆነ፣ አዳም በዲያብሎስ በመፈተን—እነሆ፣ ሀዲያብሎስም በአዳም ፊት ነበርና፣ ምክንያቱም ለኃይሌ የሆነውን ሐክብርህን ስጠኝ በማለት በእኔ ላይ መአምጿልና፤ እንዲሁም ሠአንድ ሶስተኛውን የሰማይ ረሰራዊት ሰበነጻ ምርጫቸው እኔን እንዲተው አደረገ፤
፴፯ እናም ወደታች ተጥለዋል፣ በዚህም የተነሳ ሀዲያብሎስ እና ለመላእክቱ መጥተዋል፤
፴፰ እናም፣ እነሆ፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ ለእነርሱ ስፍራ ተዘጋጅቶላቸዋል፣ ይህም ስፍራ ሀሲኦል ነው።
፴፱ እናም ሰይጣን የሰዎችን ልጆች ሀይፈትን ዘንድ ግድ ነው፣ ይህ ካልሆነ በራሳቸው መምረጥ አይችሉምና፤ ምክንያቱም ለመራራውን ካላወቁ ጣፋጩን ማወቅ አይችሉም ነበር—
፵ ስለዚህ፣ እንዲህም ሆነ ዲያብሎስ አዳምን ፈተነው፣ እናም የተከለከለውን ሀፍሬ በላ እናም ትእዛዙን ተላለፈ፣ በዚህም ለፈተና ራሱን አሳልፎ በመስጠቱ ምክንያት በሰይጣን ፈቃድ ለተገዢ ሆነ።
፵፩ ስለዚህ፣ እኔ፣ ጌታ አምላክ በመተላለፉ ምክንያት ከፊቴ ሀከዔደን ገነት ለእንዲወጣ አደረግሁ፣ በዚህም የተነሳ የመጀመርያ ሞት በሆነው እንዲሁም የመጨረሻ ሐሞት በሚሆነው መንፈሳዊ በሆነው በኃጢአተኞችም ላይ እናንት መየተረገማችሁ ወደዚያ ሂዱ በምልበት ጊዜ በሚከሰተው ሠየመንፈስ ሞት ሞተ።
፵፪ ነገር ግን፣ እነሆ፣ እንዲህ እላችኋለሁ እኔ፣ ጌታ አምላክ፣ ሀንስሀ እና ለበአንድያ ልጄ ስም በእምነት ሐመዳንን እንዲያውጁላቸው እኔ ጌታ አምላክ መመላእክትን እስከምልክላቸው ድረስ ሠበጊዜያው ሞት አዳም እና ዘሮቹ እዳይሞቱ አደረግሁኝ።
፵፫ እናም በዚህም የተነሳ እኔ ጌታ እግዚአብሔር የሰው ልጅ ሀየሚሞከርበት ቀናቱን መደብኩኝ፣ በዚህም የሚያምኑትም ሁሉ፣ በስጋዊ ሞቱ ወደ ለአለሟችነት እና ሐበዘለአለማዊ ህይወት መለመነሳት እንዲችል እኔ ጌታ እግዚአብሔር ይህን አደረግሁ።
፵፬ እናም የማያምኑት ወደ ዘለአለማዊ ሀጥፋት፣ ንስሀ ባለመግባታቸው ከመንፈሳዊ ውድቀታቸው አይድኑምና፤
፵፭ እነሆ ከብርሀን ይልቅ ጭለማን ይወዳሉ፣ እናም ሀስራቸውም እርኩስ ነው፣ እናም ለሚታዘዙለት ለዚያ ለደሞዛቸውን ይቀበላሉ።
፵፮ ነገር ግን፣ እላችኋለሁ፣ ህጻናት ሀልጆች ከአለም መጀመሪያ ጀምሮ በአንድያ ልጄ ለድነዋል፤
፵፯ ስለዚህ፣ ኃጢአትን ሊሰሩ አይችሉም፣ በእኔ ፊት ሀተጠያቂ እስኪሆኑ ድረስ ህጻናት ልጆችን ለለመፈተን ሰይጣን ሀይል አልተሰጠውምና፤
፵፰ ስለዚህ እንደ ፈቃዴ፣ እንደወደድሁ ሀከአባቶቻቸው እጅ ታላላቅ ነገሮችን እጠብቅባቸው ዘንድ ይህ ተሰጥቷቸዋል።
፵፱ እናም፣ ዳግም፣ እላችኋለሁ፣ እውቀት ያለው ሁሉ ንስሀ ይገባ ዘንድ አላዘዝሁምን?
፶ እናም ሀመረዳት ለሌለው እርሱ፣ እንደተጻፈው ያደርግ ዘንድ ሀላፊነቱ የእኔ ነው። እናም አሁን በዚህ ጊዜ ለእናንተ ተጨማሪ ነገርን አላውጅም። አሜን።