ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፵፭


ክፍል ፵፭

በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ በመጋቢት ፯፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ለቤተክርስቲያኗ የተሰጠ ራዕይ። ስለ ራዕይ ጽሁፍ ማስረጃን ሲያስተዋውቅ የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ እንዲህ ገልጿል፥ “በዚህ በቤተክርቲያኗ እድሜ፣ ሰዎች የጌታን ስራ እንዳይመረምሩና እምነቱንም እንዳያቅፉ ብዙ የሀሰት ዘገባዎችና ረብ የለሽ ታሪኮች ታትመውና ተሰራጭተው ነበር፤ ነገር ግን ለቅዱሳኑ ደስታ … ይህንን የሚከተለውን ተቀበልኩ”።

፩–፭፣ ክርስቶስ ከአብ ዘንድ አማላጃችን ነው፤ ፮–፲፣ ወንጌል የጌታን መንገድ በፊቱ የሚያዘጋጅ መልእክተኛ ነው፤ ፲፩–፲፭፣ ሔኖክንና ወንድሞቹን ጌታ ወደ እራሱ ተቀብሏቸዋል፤ ፲፮–፳፫፣ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ እንደተሰጠው ክርስቶስ የመምጫውን ምልክቶች ገለጠ፤ ፳፬–፴፰፣ ወንጌሉ ደግሞ ይመለሳል፣ የአህዛብ ጊዜያት ይፈጸማሉ፣ እና ምድርም በአስከፊ በሽታ ትሸፈናለች፤ ፴፱–፵፯፣ ተአምራት፣ ድንቃ ድንቅ፣ እና ትንሳኤ ዳግም ምፅአትን ያስከትላሉ፤ ፵፰–፶፫፣ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ይቆማል፣ እና አይሁዶችም በእጆቹና እግሮቹ ላይ ያሉትን ቁስሎች ያያሉ፤ ፶፬–፶፱፣ ጌታም ለአንድ ሺ አመት ዘመንም ይነግሳል፤ ፷–፷፪፣ በጣም አስፈላጊ መረጃዎች እንዲታወቁ የሚደረግበትን አዲስ ኪዳንን ነቢዩ ለመተርጎም እንዲጀምር መመሪያ ተሰጥቶታል፤ ፷፫–፸፭፣ ቅዱሳን እንዲሰበሰቡ እና ከሁሉም አገሮች ተሰብስበው የሚመጡበትን አዲስቷን ኢየሩሳሌም እንዲገነቡ ታዝዘዋል።

መንግስቱ የተሰጣችሁ፣ አቤቱ እናንት የቤተክርስቲያኔ ህዝብ ሆይ፣ አድምጡ፤ ምድርን የመሰረተውን፣ ሰማያትንና ሠራዊቱን ሁሉ የሰራውን፣ እና ህያው የሆኑትን፣ የሚንቀሳቀሱትን፣ እና የሚኖሩትን ሁሉ የፈጠረውን አድምጡ እና ስሙ።

ደግሞም እንዲህ እላችኋለሁ፣ ሞት እንዳይመጣባችሁ ድምጼን አድምጡ፤ ባሰባችሁትም ሰዓት በጋ ያልፋል፣ እና መኸሩ ይፈጸማል፣ እና መንፈሳችሁም አይድኑም።

ከአብ ፊት አማላጅ የሆነውን፣ ፊቱም ስለእናንተ እንዲህ በማለት የሚማፀንላችሁን ስሙ—

አባት ሆይ፣ ኃጢአት ያልሰራውን በእርሱም የተደሰትከውን ስቃይና ሞት ተመልከት፤ የፈሰሰውን የልጅህን ደም ተመልከት፣ ስምህ ይከበር ዘንድ አንተ የሰጠኸውን የልጅህን ደም ተመልከት፤

ስለዚህ፣ አባት ሆይ፣ በስሜ የሚያምኑትን ወደ እኔም መጥተው ዘለአለማዊ ህይወት ይኖራቸው ዘንድ እነዚህ ወንድሞቼን አድናቸው።

የቤተክርቲያኔ ህዝብ ሆይ፣ አድምጡ፣ እና እናንት ሽማግሌዎችም አብራችሁ ስሙ፣ እና ዛሬ እየተባለ እስከሚጠራ ድረስ ድምጼን አዳምጡ፣ እና ልባችሁንም አታደንድኑ፤

እውነት እላችኋለሁ፣ እኔ አልፋና ዖሜጋ፣ የመጀመሪያውና የመጨረሻው፣ የአለም ብርሀንና ህይወት—በጭለማም የማበራ ብርሀን ነኝ፣ በጨለማም ያሉት አይረዱትም።

የእኔ ወደ ሆኑት መጣሁ እነርሱም አልተቀበሉኝም፤ ለተቀበሉኝ ሁሉ ግን፣ ለእነርሱ ብዙ ተዓምራት እንዲሰሩ፣ እናም የእግዚአብሔር ልጆችም ይሆኑ ዘንድ ስልጣንን እሰጣቸዋለሁ፤ እና በስሜ ለሚያምኑትም ዘለአለማዊ ህይወት የሚያገኙበትንም ሀይል እሰጣቸዋለሁ።

እና ይህም ቢሆንም በአለም ብርሀን እንዲሆን፣ እና ለህዝቤም መመሪያ እንዲሆን፣ እና አህዛብም እንዲፈልጉት፣ እናም በፊቴም መንገድን የሚያዘጋጅልኝ መልእክተኛ እንዲሆን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳኔን ወደ አለም ልኬአለሁ።

ስለዚህ፣ ወደ እርሱ ኑ፣ እናም ከመጡትም ጋር እንደ ቀደሙት ቀናት ከሰዎች ጋር እንዳደረግሁት አነጋግረዋለሁ፣ እና ጠንካራ ማስረጃዬንም እሳያችኋለሁ።

፲፩ ስለዚህ፣ በአንድነት አድምጡ እና ጥበቤን—የሔኖክና የወንድሞቹ አምላክ ነው ብላችሁ የምትሉትን የእርሱን ጥበብ ላሳያችሁ፣

፲፪ ከምድር ተለይተው የተወሰዱትን፣ እና በቅዱሳን ሰዎች ዘንድ ሁሉ ተፈልጋ የፅድቅ ቀን እስከሚመጣበት እስከ እዚያ ተጠብቃ ያለውን ከተማ በክፋት እና በርኩሰታቸው ምክንያት ለማግኘት ያልቻሉትን ቀን ነው፤

፲፫ እናም በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች ነን ብለው የተናዘዙትን፤

፲፬ ነገር ግን ይህን እንደሚያገኙት እና በስጋም እንደሚያዩት ቃል ኪዳን ያገኙትን የሔኖክና የወንድሞቹን አምላክ የእነርሱን ጥበብ ላሳያችሁ።

፲፭ ስለዚህ፣ አድምጡ እናም ምክንያቴን እሰጣችኋለሁ፣ እና እንደ ቀደሙት ቀናት ሰዎችም አነጋግራችኋለሁ እናም እተነብያለሁም።

፲፮ ለደቀ መዛሙርቴ በስጋዬ በፊት ለፊታቸው ቆሜ እንዳሳየኋቸው ለእናንተም በግልፅ አሳያችኋለሁ፣ እና እንዲህም በማለት ነገርኳቸው፥ ለአባቶቻችሁ የተሰጠውን የተስፋ ቃል ለሟሟላት፣ በክብር በሰማይ ደመና ስለምመጣበት ቀን፣ ስለመመለሴ ምልክቶችን እንደጠየቃችሁኝ፣

፲፯ መንፈሳችሁ ከስጋችሁ ስለመለያየቱን እንደ ምርኮ ስላያችሁት፣ የቤዛ ቀን እንዴት እንደሚመጣ እና ደግሞም የተበተኑትን እስራኤል መመለስንም አሳያችኋለሁ።

፲፰ አሁን የእግዚአብሔር ቤት ብላችሁ የምትጠሩትን በኢየሩሳሌም ውስጥ ያለውን ቤተመቅደስ ተመልከቱ፣ እና ጠላቶቻችሁም ይህ ቤት በምንም አይወድቅም ይላሉ።

፲፱ ነገር ግን እውነት እላችኋለሁ፣ በማታ እንደሚመጣው ሌባ በዚህ ትውልድ ላይ ጥፋት ይደርሳል፣ እና ይህ ህዝብም ይጠፋሉ በሁሉም ሀገሮች መካከልም ይበተናሉ።

እና ይህ አሁን የምታዩት ቤተመቅደስም ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም።

፳፩ እና እንዲህም ይሆናል፣ ይሆናሉ ያልኳችሁ ጥፋቶች ከመከሰታቸው በፊት ይህ የአይሁድ ትውልድም አያልፍም።

፳፪ የአለም መጨረሻ እየመጣ እንደሆነ እናውቃለን ትላላችሁ፤ ምድርና ሰማይ እንደሚያልፉም እናውቃለን ትላላችሁ፤

፳፫ ስለዚህም እናንት በእውነት ትናገራላችሁ፣ ይህም ነውና፤ ነገር ግን እነዚህ የነገርኳችሁ ሁሉም ነገሮች እስከሚፈጸሙ ድረስ አያልፉም።

፳፬ እና ይህ የነገርኳችሁ ስለ ኢየሩሳሌም ነው፤ እናም ያ ቀን ሲመጣም፣ የቀሩትም በሁሉም አገሮች መካከል ይበተናሉ

፳፭ ነገር ግን ደግሞም ይሰበሰባሉ፤ ነገር ግን የአህዛብ ጊዜ እስከሚፈጸም ድረስ እንዲሁ ይቆያሉ።

፳፮ በዚያ ቀንም ስለ ጦርነቶችና የጦር ወሬዎች ይሰማል፣ እና ምድር ሁሉም በሁከት ውስጥ ትሆናለች፣ እናም የሰዎች ልብ በፍርሀት ይደክማል፣ እና እስከ ምድር ጫፍም ድረስ ክርስቶስ መምጫውን አዘገየው ይላሉ።

፳፯ የስዎች ፍቅርም ይቀዘቅዛል፣ እና ኃጢአትም ይበዛል።

፳፰ የአህዛብ ጊዜ ሲመጣም፣ በጨለማ ውስጥ ለተቀመጡትም ብርሀን ይሆናል፣ እና ይህም ወንጌሌ ሙሉ ይሆናል፤

፳፱ ነገር ግን አይቀበሉትም፤ ብርሀኑን አይመለከቱትምና፣ እናም በሰዎች አስተያየት ምክንያትም ልባቸውን ከእኔ ያዞራሉ

በዚያ ትውልድም ውስጥም የአህዛብ ጊዜዎች ይፈጸማሉ።

፴፩ እናም ተከታታይ ቀሰፋዎችን ከማየታቸው በፊት የማያልፉ ሰዎች በዚያም ትውልድ ይኖራሉ፤ በሽታም ምድርም በአሰቃቂ በሽታ ትሸፈናለችና።

፴፪ ነገር ግን ደቀ መዛሙርቴ በተቀደሰ ስፍራዎች ላይ ይቆማሉ፣ እናም አይነቃነቁም፤ ነገር ግን ከክፉዎቹም መካከል፣ ሰዎች ድምጾቻቸውን አንስተው እግዚአብሔርን ይረግማሉ እናም ይሞታሉ።

፴፫ የምድርም መናወጥ እናም ብዙ በዳማም በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ ነገር ግን ሰዎች በእኔ ላይ ልባቸውን ያደነድናሉ፣ እናም እርስ በራሳቸው ሰይፋቸውን ይማዘዛሉ፣ እናም ይገዳደላሉ።

፴፬ እና አሁንም፣ እኔ ጌታ እነዚህን ቃላት ለደቀ መዛሙርቴ ስነግራቸው ተጨንቀው ነበር።

፴፭ እናም እኔ እንዲህ አልኳቸው፣ አትጨነቁ፣ ምክንያቱም እነዚህ ሁሉ ነገሮች ሊሆኑ ግድ ስለሚሆን፣ ቃል የገባሁላችሁ ነገሮች ሁሉ እንደሚፈጸሙ ታውቃላችሁ።

፴፮ ብርሀንም መፈንጠቅ ሲጀምር፣ በምሳሌም እንደማሳያችሁ ለእነርሱም እንዲሁ ይሆናል—

፴፯ ተመልከቱ እና የበለስ ዛፎችንም እዩ፣ እናም በአይኖቻችሁም ተመልከቷቸው፣ እና ሲያቈጠቍጡ፣ እናም ቅጠሎቻቸውም ሲለመልሙ፣ በጋ አሁን እየቀረበ ነው ትላላችሁ፤

፴፰ እነዚህን ነገሮች ሁሉ በሚያዩበት በዚያ ቀንም እንዲህም ይሆናል፣ ከዚያም ሰአቱ እንደደረሰ ያውቃሉ።

፴፱ እና እንዲህም ይሆናል፣ እኔን የሚፈራ የጌታን መምጫ ታላቅ ቀን፣ እንዲሁም የሰውን ልጅ መምጫ ምልክቶችንይጠብቃል

እናም ምልክቶችንና ተዓምራቶችን ያያሉ፣ ምክንያቱም በላይ ሰማይ እና በታች በምድርም ይታያሉና።

፵፩ እናም ደምን፣ እሳትን፣ እና የጢስ ጭጋግን ይመለከታሉ።

፵፪ እና የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊትም፣ ፀሀይ ትጨልማለች፣ እናም ጨረቃ ወደ ደምነት ትለወጣለች፣ እናም ክዋክብትም ከሰማይ ይረግፋሉ።

፵፫ እናም የቀሩትም በዚህ ስፍራ ይሰበሰባሉ፤

፵፬ ከዚያም እኔን ይሻሉ፣ እናም እነሆ፣ እኔም እመጣለሁ፤ እናም በሀይልና በሰማይ ደመና፣ በታላቅ ክብር ተሸፍኜ፣ ከሁሉም ቅዱሳን መላእክት ጋርም ያዩኛል፤ እናም እኔን የማይጠብቀውም እርሱ ተለይቶ ይጠፋል።

፵፭ የጌታ ክንድ ከመውረዱ በፊት ግን፣ አንድ መልአክ መለከቱን ይነፋል፣ እናም አንቀላፍተው የነበሩት ቅዱሳንም በደመናው እኔን ለመቀበል ይመጣሉ

፵፮ ስለዚህ፣ በሰላም ብታንቀላፉ የተባረካችሁ ናችሁ፤ ምክንያቱም አሁን አይታችሁኝ እንዳወቃችሁኝ፣ እንዲሁም እናንት ወደ እኔ መጥታችሁ ነፍሶቻችሁም ህያው ይሆናሉና፣ እና ደህንነታችሁም ፍጹም ይሆናል፤ እና ቅዱሳንም ከአራቱ የምድር ማዕዘናትም ይመጣሉ።

፵፯ ከዚያም የጌታ ክንድ በአህዛብ ላይ ይወርዳል።

፵፰ ከዚያም ጌታ እግሩን በዚህ ተራራ ላይ ያቆማል፣ እና ተራራውም ለሁለት ይሰነጠቃል፣ እና ምድርም ትንቀጠቀጣለችም፣ ወዲህና ወዲያም ትናወጣለች፣ እና ሰማያትም ይንቀጠቀጣሉ

፵፱ እና ጌታም ድምጹን ያሰማል፣ እናም የምድርም ዳርቻ ሁሉ ይሰሙታል፤ እና የምድር ነገስታት ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፣ እና የሳቁትም ሞኝነታቸውን ያያሉ።

አሽሟጣጩንም አደጋ ይሸፍነዋል፣ ፌዘኛውም ይጠፋል፤ እናም ለኃጢአትም ያደፈጡ ሁሉ ተቆርጠው ወደ እሳት ይጣላሉ።

፶፩ ከዚያም አይሁድም ወደ እኔ ተመልክተው እንዲህ ይላሉ፥ በእጆችህ እና በእግሮችህ ያሉት እነዚህ ቍስሎች ምንድን ናቸው?

፶፪ ከዚያም እኔ ጌታ እንደ ሆንኩም ያውቃሉ፤ ምክንያቱም እኔ እንዲህ እላቸዋለሁና፥ እነዚህ ቁስሎች በወዳጆቼ ቤት የቆሰልኳቸው ቍስሎች ናቸው። እኔም ከፍ የተደረግሁት ነኝ። እኔም የተሰቀለው ኢየሱስ ነኝ። እኔም የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ።

፶፫ እና ከዚያም በኃጢአቶቻቸው ምክንያትም ያለቅሳሉ፤ ከዚያም ንጉሳቸውን ስላሰቃዩ በሰቆቃም ያዝናሉ።

፶፬ እና ከዚያም የአህዛብ አገሮችም ይድናሉ፣ እና ህግን የማያውቁትም በፊተኛው ትንሳኤ ስፍራ ይኖራቸዋል፤ እና ለእነርሱም ይቀልላቸዋል

፶፭ በሰው ልጆች ልብ ውስጥ ምንም ስፍራ እንዳይኖረው ሰይጣንም ይታሰራል

፶፮ እናም በክብሬ በምመጣበት በዚያም ቀንም፣ ስለ አስሮቹ ደናግል የተናገርኩት ምሳሌም ይፈጸማል።

፶፯ እነርሱ ጥበበኛ ናቸው እናም እውነትን ተቀብለዋልና፣ እና እንደ መሪያቸውም መንፈስ ቅዱስን ተቀብለዋል፣ እና አልተታለሉም—በእውነት እንዲህ እላችኋላሁ፣ ቀኑን ይዋጃሉ እንጂ ተቆርጠው ወደ እሳቱ አይጣሉም።

፶፰ እና ምድርንም ይወርሱ ዘንድ ይሰጣቸዋል እናም ተባዝተውም ብርቱዎች ይሆናሉ፤ እናም ልጆቻቸውም ያለኃጢአት ወደ ደህንነት ያድጋሉ

፶፱ ጌታም ከእነርሱ መካከል ይገኛልና፣ እናም ክብሩም በእነርሱ ላይ ያርፋል፣ እናም እርሱም ንጉሳቸውና ህግ ሰጪአቸው ይሆናል።

እና አሁንም እነሆ እንዲህ እላችኋላሁ፣ አዲስ ኪዳን እስከሚተረጎም ድረስ ስለዚህ ምዕራፍ ከዚህ ሌላ ታውቁ ዘንድ ምንም አልሰጣችሁም፣ እና በውስጡም እነዚህ ሁሉ ነገሮች ይታወቃሉ፤

፷፩ ስለዚህ ወደፊት ለሚመጡት ነገሮች ትዘጋጅ ዘንድ፣ አሁን ይህን እንድትተረጉም ሰጥቼሀለሁ።

፷፪ በእውነት እንዲህ እላችኋላሁ፣ ታላላቅ ነገሮች ይጠብቋችኋልና፤

፷፫ በባዕድ ሀገሮችም ጦርነትን ትሰማላችሁ፣ ነገር ግን እነሆ እንዲህ እላችኋላሁ፣ እነዚህ ቅርብ ናቸው፣ እንዲሁም በበራችሁ ላይ ቀርበዋል፣ እና ብዙ አመታት ከማለፋቸው በፊትም ስለራሳችሁ ሀገርም ጦርነትን ትሰማላችሁ።

፷፬ ስለዚህ የቤተክርቲያኔ ሽማግሌዎች ሆይ፣ እኔ ጌታ ከምስራቅ ሀገሮች ተሰብስባችሁ ውጡ እና በአንድነትም ራሳችሁን ሰብስቡ እላችኋለሁ፤ ወደ ምእራብ ሀገሮችም ሂዱ፣ በዚያም የሚኖሩትንም ንስሀ እንዲገቡም ጥሯቸው፣ እና ንስሀ ቢገቡም ቤተክርቲያኖችን ለእኔ ስሩልኝ።

፷፭ እና በአንድ ልብና ሀሳብ፣ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ለእናንተ የሚመደብላችሁን ውርስ ለመግዛት ትችሉ ዘንድ ሀብቶቻችሁን ሰብስቡ።

፷፮ ይህም አዲሲቷ ኢየሩሳሌምየሰላም ምድርመሸሸጊያ ከተማ፣ የልዑሉ እግዚአብሔር ቅዱሳን ደህንነት ስፍራ ትባላለች፤

፷፯ እና የጌታ ክብርም በዚያ ይገኛል፣ እናም የጌታ ፍርሀትም በዚያ ይኖራል፣ በዚህ ምክንያትም ኃጢአተኞቹም ወደ እርሷ አይገቡም፣ እናም ፅዮንም ተብላ ትጠራልች።

፷፰ በኃጢአተኞቹም መካከል እንዲህም ይሆናል፣ ሰይፉን በጎረቤቱ ላይ የማያነሳው እያንዳንዱ ሰውም ለደህንነት ወደ ፅዮን መሸሽ ያስፈልገዋል።

፷፱ በዚያም ከሰማይ በታች ካሉ እያንዳንዱ ሀገርም ወደ እሷ ይሰበሰባሉ፤ እና እርስ በራሱ በጦርነት ላይ የማይሆን ህዝብም እርሱ ብቻ ይሆናል።

በኃጢአተኞቹ መካከልም እንዲህ ይባላል፣ ከፅዮን ጋር ለመዋጋት አንሂድ፣ ምክንያቱም የፅዮን ኗሪዎች አስፈሪዎች ናቸውና፤ ስለዚህ ልንቋቋማቸው አንችልም።

፸፩ እናም እንዲህ ይሆናል ጻድቃን ከእያንዳንዱ ሀገሮች ተሰብሰበው ይወጣሉ፣ እና የዘለአለማዊ ደስታ መዝሙርንም እየዘመሩ ወደ ፅዮን ይመጣሉ።

፸፪ እና አሁንም እንዲህ እላችኋላሁ፣ ይህን ስራ በህዝቡ አይኖች፣ እና በጠላቶቻችሁ አይኖች እንድታከናውኑ፣ እና ያዘዝኳችሁንም ነገሮች እስከምታከናውኑ ድረስ ስራችሁን እንዳያውቁ ለእኔ አስፈላጊ ነው እስከምላችሁ ድረስ እነዚህ ነገሮች ወደ አለም እንዳይወጡ ጠብቁ፤

፸፫ ይህንንም ሲያውቁ፣ እነዚህን ነገሮች ያስተውሉ ዘንድ ነው።

፸፬ ጌታ ሲመጣም ለእነርሱ አስፈሪ ይሆናል፣ ፍርሀትም ይይዛቸዋል፣ እና በሩቅ ቆመውም ይንቀጠቀጣሉ።

፸፭ እናም በጌታ ፍርሀት እና በሀይሉ ችሎት ምክንያት ሁሉም አገሮች ይፈራሉ። እንዲህም ይሁን። አሜን።