ከፍል ፹፯
በታህሳስ ፳፭፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል በከርትላንድ ኦሀዮ ወይም በአካባቢው የተሰጠ የጦርነት ራዕይ እና ትንቢት። በዚህ ጊዜ በዮናይትድ ስቴትስ ውስጥ ስለ ባርነት እና ሳውዝ ኬሮላይና የመንግስት ቀረጥ ስለመሰረዟ ክርክር በብዛት ይገኝ ነበር። የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ እንደሚገልጸው፣ “በሀገሮች መካከል ያለው ችግር ቤተክርስቲያኗ ከዱር የመውጣት ጉዞዋን ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ ከነበረው በላይ” ለነቢዩ “በግልፅ ይታይ” ነበር።
፩–፬፣ በሰሜን እና በደቡብ ስቴቶች መካከል ጦርነት ተተነበየ፤ ፭–፰፣ ታላቅ መቅሰፍት በምድር ኗሪዎች ላይ ይደርሳል።
፩ እውነትም፣ ጌታ፣ ሀበደቡብ ኬሮላይና ማመፅ በሚጀምረው፣ የብዙ ነፍሳት ሞት እና ስቃይ ውጤት ስለሆነው፣ በአጭር ጊዜ ስለሚመጣው ጦርነት እንዲህ ይላል፤
፪ እናም፣ ከዚህ ስፍራ አንስቶ፣ በሁሉም ህዝብ ላይ ሀጦርነት የሚፈስበት ጊዜ ይመጣል።
፫ እነሆ፣ የደቡብ ስቴቶቹ ከሰሜን ስቴቶቹ ጋር ይከፋፈላሉ፣ እናም የደቡብ ስቴቶች ሌሎች ሀገሮችን፣ እንዲሁም እንግሊዝ ተብለው የሚጠሩትንም ይጠራሉ፣ እናም እነርሱም፣ ከሌሎች አገሮች ራሳቸውን ለመጠበቅ፣ ሌሎች አገሮችን ይጠራሉ፤ እና ከዚያም ሀጦርነት በሁሉም ሕዝቦች ላይ ይፈሳል።
፬ እናም እንዲህ ይሆናል፣ ከብዙ ቀናት በኋላ፣ ለጦርነት የተዘጋጁት እና የሰለጠኑት ሀባሪያዎች በጌታቸው ላይ ይነሳሉ።
፭ እናም እንዲህ ይሆናል በምድሩ የሚቀሩትም ራሳቸውን ያዘጋጃሉ፣ እናም በጣም ይቆጣሉ፣ እናም አህዛብን በታላቅ ስቃይ ያሰቃዩአቸዋል።
፮ በመሆኑም፣ በጎራዴ እና ደም በማፍሰስ የምድር ኗሪዎች ሀያዝናሉ፤ እናም፣ የክፉ ጥፋት ሕዝብን ሁሉ በፍጹም እንዲጠፉ እስከሚያደርጋቸው ድረስ፣ ለበረሀብ፣ እና ወረርሽኝ፣ እና በምድር መንቀጥቀጥ፣ እና በሰማይ ነጎድጓድ፣ እና በአስፈሪ እና በግልፅ መብረቅም ሐየምድር ኗሪዎች ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔርን እጅ ንዴት፣ እና ቁጣ፣ እና መግሰጻ እንዲሰማቸው ይደረጋሉ።
፯ በጠላቶቻቸው ላይ እንዲበቀሉ የቅዱሳን እና የቅዱሳን ሀደም ወደሚጮኹበት ወደ ለፀባኦት ጌታ ጆሮዎች መምጣትን ያቆማሉ።
፰ ስለዚህ፣ የጌታ ቀን እስከሚመጣ ድረስ፣ በተቀደሱ ስፍራዎች ሀቁሙ፣ እናም አትነቃነቁ፤ እነሆ፣ ለበቶሎ ይመጣልና፣ ይላል ጌታ። አሜን።