ክፍል ፶፮
በሰኔ ፲፭፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) ከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ፣ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። ይህም ራዕይ በሚኖርበት በፍሪድሪክ ጂ ዊልያምስ እርሻ ላይ ስላለው ሀላፊነት በተመለከተ ጆሴፍ ስሚዝ ለእርሱ የተቀበለለትን የቀድሞውን ራዕይ (በቁጥር ፰ “ትእዛዝ” ተብሎ የተጠቀሰው) ባለማክበሩ እዝራ ቴይርን ይገስጻል። የሚቀጥለው ራዕይ ደግሞም ከቶማስ ቢ ማርሽ ጋር ወደ ሚዙሪ እንዲጓዝ የተጠራበትን ይሰርዛል (ክፍል ፶፪፥፳፪ ተመልከቱ)።
፩–፪፣ ደህንነትን ለማግኘት ቅዱሳን መስቀሉን መሸከም እና ጌታን መከተል አለባቸው፤ ፫–፲፫፣ ጌታ ያዛል እናም ይሽራል፣ እና የማይታዘዙትም ይጣላሉ፤ ፲፬–፲፯፣ ድሀውን ለማይረዳው ባለጠጋም ወዮለት፣ እና ልባቸው ላልተሰበሩ ድሆችም ወዮላቸው፤ ፲፰–፳፣ በልባቸው ንጹሀን የሆኑ ድሆች ብፁዓን ናቸው፣ ምድርን ይወርሳሉና።
፩ በስሜ ሀየምትታወቁ ህዝቤ ሆይ፣ አድምጡ ይላል ጌታ አምላካችሁ፤ እነሆ ቁጣዬ በአማጸኞች ላይ ነዷል፣ እናም በአህዛብ ላይ በሚመጣው ለየጉብኝት እና የመዓት ቀን፣ ክንዴን እና ቁጣዬን ያውቃሉ።
፪ ሀመስቀሉን አንስቶ ለየማይከተለኝ፣ እና ትእዛዛቴን የማያከብረው፣ እርሱ አይድንም።
፫ እነሆ፣ እኔ ጌታ አዛለሁ፤ እና ትእዛዝን ሰጥቼ እና ትእዛዜም ሀከተሰበረ በኋላም የማይታዘዘውም በራሴ ጊዜ ለይቆረጣል።
፬ ስለዚህ፣ እኔ ጌታ መልካምም እንደመሰለኝ አዝዛለሁ ሀእሽራለሁም፤ እናም፣ ጌታ እንዲህ ይላል፣ ይህም ሁሉ ለበሚያምጹት ራስ ላይ ይመለስላቸዋል።
፭ ስለዚህ፣ ለአገልጋዮቼ ሀቶማስ ቢ ማርሽ እና እዝራ ቴይር የሰጠሁትን ትእዛዝ እሽራለሁ፣ እና ለአገልጋዬ ቶማስ ወደ ሚዙሪ አገር ፈጥኖ እንዲጓዝም አዲስ ትእዛዝን ሰጥቼዋለሁ፣ እና አገልጋዬ ሴላ ጄ ግርፍን አብሮት ይሄዳል።
፮ ምክንያቱም እነሆ፣ ቶምሰን ውስጥ ባሉት ህዝቤ አንገተ ደንዳናነት እና በእነርሱ አመጽ ምክንያት ለአገልጋዮቼ ሴላ ጄ ግርፍን እና ኒውል ናይት የሰጠኋቸውን ትእዛዝ እሽራለሁ።
፯ ስለዚህ፣ አገልጋዬ ኒውል ናይት ከእነርሱ ጋር ይቆይ፤ እና በፊቴ የሚጸጸቱ እና ወደ መረጥኩት ምድር በእርሱ ተመርተው የሚሄዱት ሁሉም ይሂዱ።
፰ እና ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ እዝራ ቴይር ሀለኩራቱ እና ራሱን ለመውደዱ ንስሀ መግባት፣ እናም ስለሚኖርበት ስፍራ በፊት የሰጠሁትን ትእዛዝ ማክበር አለበት።
፱ እና ይህን ቢያደርግ፣ በምድሩም ላይ መከፋፈል ስለማይኖር፣ ወደ ሚዙሪ አገር እንዲሄድም ይመረጣል፤
፲ አለበለዚያም፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ የከፈለውን ገንዘብ ይቀበላል፣ እናም ከስፍራው ይሄዳ፣ ከቤተክርስቲያኔም ሀይቆረጣል፤
፲፩ እና ምንም እንኳን ሰማይ እና ምድር ቢያልፉም፣ እነዚህ ቃላት ሀአያልፉም፣ ነገር ግን ሁሉም ይፈጸማሉ።
፲፪ እናም አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊም ገንዘቡን መክፈል ቢኖርበትም፣ እነሆ፣ እኔ ጌታ መልሼ በሚዙሪ አገር ውስጥ እከፍለዋለሁ፣ እና እርሱ የሚቀበላቸውም ባደረጉት መጠን ደግመው ዋጋቸውን ይቀበላሉ፤
፲፫ በውርስ መሬቶቻቸውም እንኳ ቢሆን ባደረጉት መጠን ይቀበላሉ።
፲፬ እነሆ፣ ጌታ ለህዝቤ እንዲህ ይላል—እናንት ብዙ የምታደርጉት እና ንስሀ የምትገቡባቸው ነገሮች አሉአችሁ፤ እነሆ፣ ኃጢአቶቻችሁ ወደ እኔ መጥተዋል፣ እና ይቅርታም አልተሰጣቸውምና፣ ምክንያቱም በገዛ መንገዳችሁ ሀምክርን ስለምትሹ ነው።
፲፭ እናም ልባችሁም አልረኩም። እናም እውነትን አታከብሩም፣ ነገር ግን ፅድቅ ባልሆነው ሀትደሰታላችሁ።
፲፮ ንብረታችሁን ሀለድሆች ለየማትሰጡ እናንት ሐባለጠጎች ወዮላችሁ፣ መሀብቶቻችሁም ነፍሳችሁንያዝላሉና፤ እና በጉብኝት እና በፍርድ እና በቁጣም ቀንም ለቅሶአችሁ ይህ ይሆናል፥ ሠየአዝመራ ወቅት አለፈ፣ በጋም አለቀ፣ እና ነፍሴም አልዳነም!
፲፯ ልባችሁ ያልተሰበሩ፣ መንፈሶቻችሁም ያልተዋረዱ፣ እና ሆዳችሁ ያልሞላና፣ የሌሎች ሰዎች ንብረቶችን ከመያዝ እጆቻችሁን ያላቆማችሁ፣ አይኖቻችሁ ሀበስግብግብነት የተሞላና፣ በእጆቻችሁ የማትሰሩ ለድሀ ሰዎችም ወዮላችሁ!
፲፰ ነገር ግን ልባቸው ንጹህ የሆኑ፣ ልቦቻቸው ሀየተሰበሩ፣ እና መንፈሶቻቸው የተጸጸቱ ለድሆች ግን ብፁዓን ናቸው፣ ምክንያቱም ለደህንነታቸው የእግዚአብሔር ሐመንግስት በሀይልና በታላቅ ክብር ሲመጣ ይመለከታሉና፤ መየምድርም ስብ ለእነርሱ ይሆናልና።
፲፱ እነሆ፣ ጌታ ይመጣል፣ እናም ሀሽልማቱም ከእርሱ ጋር ይሆናል፣ እና ለእያንዳንዱን ሰውም ዋጋውን ይሰጠዋል፣ እና ድሀውም ይደሰታልና፤
፳ ትውልዶቻቸውም ምድርን ከትውልድ እስከ ትውልድ፣ ከዘለአለም እስከ ዘለአለም ድረስ ሀይወርሳሉ። እና አሁን የምነግራችሁን እፈፅማለሁ። እንዲሁም ይሁን። አሜን።