ጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ
በ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) ለነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተገለጠለት የመፅሐፍ ቅዱስ ትርጉም ልዩ እትም፥ ማቴዎስ ፳፫፥፴፱ እና ምዕራፍ ፳፬።
ምእራፍ ፩
ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ላይ ስለሚመጣው ጥፋት አስቀድሞ ነገራቸው—ስለሰው ልጅ ስለክፉው መጥፊያ ዳግም ምፅዓት፣ እና ስለክፉዎች ጥፋት አስተማረ።
፩ እላችኋለሁና፣ በጌታ ስም በሰማይ ደመናዎች ውስጥ፣ እና ሁሉም ቅዱስ መላእክት ከእርሱም ጋር ሀየሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም እና በነቢያት ስለእርሱ ነው የተጻፈው ብላችሁ ልታውቁኝ አትችሉም። ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ለበእግዚአብሔር ቀኝ እጅ በኩል በክብር ዘውድ ተጭኖለት ዳግም ተመልሶ እንደሚመጣ ገባቸው።
፪ ኢየሱስ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሄደ፤ እና ደቀ መዛሙርቱም የሚለውን ለመስማት ወደእርሱ መጥተው እንዲህ አሉ፥ መምህር፣ ስለቤተመቅደሱ ህንጻ አሳየን፣ አንተ እንዳልከው—እነርሱም ይፈርሳሉ፣ እና የተፈታ ሆኖ ትቀርላቸዋለች።
፫ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አታዩም፣ እና አይገቧችሁምን? እውነት እላችኋለሁ፣ ከዚህ ቤተመቅደስ ሀድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ የሚቀር አይኖርም።
፬ እና ኢየሱስ ትቶአቸው ሄደ፣ እና ወደ ሀደብረ ዘይት ተራራም ሄደ። በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ፣ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው፣ ስለ ቤተመቅደሱ መፍረስና ስለ አይሁድ በተመለከተ ያልካቸው እነዚህ ነገሮች መቼ እንደሚሆኑ ንገረን፤ እና የአንተ ለደግሞ መመለሻና ሐየአለም መጨረሻ፣ ወይም የአለም መጨረሻ የሆነው መየክፉዎቹ መጥፊያ ሠምልክትስ ምንድን ነው? አሉት።
፭ እና ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤
፮ ብዙዎች በስሜ—እኔ ክርስቶስ ነኝ—በማለት ይመጣሉና፣ እና ብዙዎችንም ያስታሉ፤
፯ ከዚያም በስሜ ምክንያትም ሀለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፣ እናም ይገድሏችኋል፣ እናም በህዝብ ሁሉ ዘንድ ለየተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤
፰ እና ብዙዎችም ይቀየማሉ፣ እና እርስ በራስ ይክዳሉ፣ እርስ በራስም ይጣላሉ፤
፱ እና ብዙ ሐሰተኛ ነቢያትም ይነሳሉ፣ እና ብዙዎችንም ያስታሉ፤
፲ እና ክፋት በብዛት ስለሚገኝ፣ የብዙዎችም ሀፍቅር ትቀዘቅዛለች፤
፲፩ በፅናት የሚቋቋመውና የማይሸነፈው ግን፣ እርሱ ይድናል።
፲፪ ሀኢየሩሳሌምን በሚመለከት በጥፋት ነቢዩ ለዳንኤል የተናገረውን የጥፋት ሐርኩሰት ስታዩ፣ ከዚያም መበተቀደሰ ስፍራም ቁሙ፤ ይህን የሚያነብ ይግባው።
፲፫ ከዚያም በይሁዳ የሚገኙ ወደ ሀተራሮች ይሽሹ፤
፲፬ በቤቱ ጣራ ላይ የሚገኝ ማንም ሰው እቃውን ከቤቱ ለማውጣት አይውረድ፤
፲፭ በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ።
፲፮ በዚያችም ወራት ሀለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው፤
፲፯ ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤
፲፰ በዚያን ጊዜ ከመንግስታቸው መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከእግዚአብሔር ወደ እስራኤል ተልኮ ያልነበረ ታላቅ ስቃይ ሀበአይሁዶች፣ እና ለበኢየሩሳሌም ኗሪዎች ላይ ይደርሳል፤ ከዚህም በኋላ በእስራኤል ላይ እንደገና አይላክም።
፲፱ እነርሱ ላይ የደረሱባቸው ገና ከሚመጡባቸው ሀዘን የመጀመሪያዎቹ ናቸው።
፳ እና እነዚያ ቀናትስ ካላጠሩ በስተቀር፣ ሥጋ ከለበሰ የሚድን ማንም አይኖርም፤ ነገር ግን እነዚያ ቀናት ለተመረጡ ሰዎች፣ በቃል ኪዳን መሰረት፣ ያጥራሉ።
፳፩ አይሁዶችን በሚመለከት የነገረኳችሁ እነዚህን ነገሮች ተመልከቱ፤ ደግሞም በኢየሩሳሌም ላይ ከሚመጡት ከእነዚያ ቀናት በኋላ፣ ማናችሁም አስተውሉ ክርስቶስ በዚህ አለ ወይም በዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤
፳፪ በእነዚያ ቀናት ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉና፣ ቢቻላቸውም፣ በቃል ኪዳን መሰረት ምርጥ የነበሩትን፣ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅን ያሳያሉ።
፳፫ እነሆ፣ እነዚህን ነገሮች የምነግራችሁ ሀለተመረጡት ጥቅም ነው፤ ለጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰማላችሁ፤ አትጨነቁም፣ የነገርኳችሁ ሁሉ መፈጸም አለባቸውና፤ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው።
፳፬ እነሆ፣ አስቀድሜ ነግሬአችኋለሁ፤
፳፭ ስለዚህ፣ እነሆ፣ በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፣ አትውጡ፥ እነሆ፣ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፣ አትመኑ፤
፳፮ የጠዋት ብርሀን ሀከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚያበራ፣ እና ምድርን በሙሉ እንደሚሸፍን፣ የሰው ልጅ ምፅዓትም እንዲሁ ይሆናልና።
፳፯ አሁንም ምሳሌ አሳያችኋለሁ። እነሆ፤ ቅሪቶች ባሉበት፣ አሞራም አብረው ሀይሰበሰባሉ፣ እንደዚህም የእኔ ምርጦች ከአራቱ የምድር ማዕዘናት ይሰበሰባሉ።
፳፰ እና ጦርንም የጦርንም ወሬ ይሰማሉ።
፳፱ እነሆ፣ የምናገረው ለምርጦቼ ጥቅም ነው፤ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፣ ሀራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤
፴ ደግሞም ከዓመፃ ብዛት የተነሣ የሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች፤ እስከ ፍጻሜው የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።
፴፩ ደግሞም፣ ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል ሀበዓለም ሁሉ ይሰበካል፣ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ወይም የክፋተኞቹ ጥፋት ይመጣል።
፴፪ ደግሞም በነቢዩ በዳንኤል የተነገረው የጥፋት ርኩሰትም ይፈጸማል።
፴፫ ከዚያች መከራ ቀናት በኋላ ወዲያው ሀፀሐይ ትጨልማለች፣ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፣ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፣ እና የሰማይ ሀይላትም ይናወጣሉ።
፴፬ በእውነት እላችኋለሁ፣ የነገርኳችሁ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ፣ እነዚህ ነገሮች የሚታዩባቸው ይህ ትውልድ አያልፍም።
፴፭ ምንም እንኳን ሰማይና ምድር የሚያልፉበት ቀን ቢመጣም፣ ሀቃሌ ግን አያልፍም፣ ነገር ግን ሁሉም ይፈጸማሉ።
፴፮ አስቀድሜ እንዳልኳችሁ፣ ከዚያች ሀየመከራ ቀናት በኋላ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ፣ በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፣ ከዚያም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፤ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ለሲመጣ ያዩታል፤
፴፯ እና ሀቃላቶቼን እንደ ሀብት የሚያከማቸው ማንም አይታለልም፣ የሰው ልጅም ይመጣልና፣ እና ለመላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፣ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ሐይሰበስባሉ።
፴፰ አሁን ሀየበለስ ዛፍን ምሳሌ ተማሩ—ቅርንጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፣ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤
፴፱ እንደዚሁም እነዚህን ሁሉ ምርጦቼ ሲያዩ፣ እርሱ በደጅ እንደቀረበ፣ እንዲሁም በበር ላይ እንዳለ ያውቃሉ፤
፵ ስለዚያች ቀንና ሰዓት ግን ከአባቴ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ማንም ሀየሚያውቅ የለም።
፵፩ ሀበኖህ ዘመን እንደ ነበረ፣ የሰው ልጅ መምጣትም እንዲሁ ይሆናል፤
፵፪ ሀከጥፋት ውሃ በፊት እንደነበረም ይሆንላቸዋል፤ ኖህ ወደ መርከቡ እስከገባበት ቀናት ድረስም ሲበሉና ሲጠጡ፣ ሲያገቡና ሲጋቡ ነበሩና፤
፵፫ እና የጥፋት ውኃም መጥቶ፣ ሁሉን እስከ ወሰዳቸው ድረስ አላወቁም፤ የሰው ልጅ መምጣትም ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።
፵፬ ከዚያም የተጻፈው ይፈጸማል፣ ሀበመጨረሻዎቹም ቀናት ሁለት ሰዎች በዕርሻ ላይ ይሆናሉ፣ አንዱ ይወሰዳል ሌላው ለይቀራል፤
፵፭ ሁለቱ በወፍጮ ይፈጫሉ፣ አንዷ ትወሰዳለች ሌላዋ ትቀራለች።
፵፮ እና እኔ ለአንዱ የምለውን፣ ለሁሉም ሰዎች እላለሁ፤ ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ሀንቁ።
፵፯ ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፣ ይነቃ ነበር፣ እና ቤቱም እንዲፈርስ አይፈቅድም ነበር፣ ነገር ግን ይዘጋጅም ነበር።
፵፰ ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጁ፣ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።
፵፱ በተገቢው ጊዜ ምግባቸውን እንዲሰጣቸው ባለቤቱ በቤተሰቦቹ ላይ የሾመው ሀታማኝና ብልህ አገልጋይ ያደረገው እንግዲህ ማን ነው?
፶ ባለቤቱ ተመልሶ ሲመጣ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ የተባረከ ነው፤ እና እውነት እላችኋለሁ፣ በእቃዎቹ ሁሉ ላይ ገዢ እንዲሆን ይሾመዋል።
፶፩ ነገር ግን ያ ክፉ ባርያ በልቡ እንዲህ ቢል፥ ጌታዬ መመለሻው ሀይዘገያል፣
፶፪ እና የባልንጀሮቹን ባሮች ሊመታ፣ እና ከሰካሮችም ጋር ሊበላና ሊጠጣ ጀመረ፣
፶፫ የዚያ ባርያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን፣ እና ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፣
፶፬ ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፣ እና እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ሀማፋጨት ይሆናል።
፶፭ በሙሴ ትንቢት መሰረት፣ እንደዚህም የክፉዎች መጨረሻ ይመጣል፣ ብሏል፥ ከሰዎች መካከል ይቆረጣሉ፤ ነገር ግን የምድር ሀመጨረሻው ገና አይደለም፣ ነገር ግን ከጥቂት ጊዜ በኋላ ነው።