ከመፅሐፈ አብርሐም ቅርፅ
ቁጥር ፫
መግለጫ
ስዕል ፩ በንጉሱ ትሁትነት፣ አብርሐም የሰማይ ታላቅ አመራር አርማ የሆነውን ክህነት የሚወክለውን ዘውድ በራሱ ላይ ተደርጎለት፣ የፍርድና የፍትሕ በትረ መንግስት በእጁ ይዞ፣ በፈርዖን ዙፋን ላይ ተቀምጦ።
ስዕል ፪ ስሙ በፊደል ከራሱ በላይ የተጻፈለት ንጉስ ፈርዖን።
ስዕል ፫ በስዕል ፲ ላይ እንደተሰጠው አብርሐም በግብፅ ውስጥ የሚያስመለክት።
ስዕል ፬ ከእጅ በላይ እንደተጻፈው፣ የግብፅ ንጉስ ፈርዖን ልዑል።
ስዕል ፭ ከእጁ በላይ በፊደል በተጻፈው እንደሚወከለው፣ የንጉሱ ዋና አስተናጋጅ ሹለም።
ስዕል ፮ የልዑሉ ንብረት ባሪያ ኦሊምላኽ።
አብርሐም በንጉሱ አደባባይ ውስጥ ስለ ስነ ፈለክ ጥናት መሰረታዊ መርሆች ሲሟገት።