ቅዱሳት መጻህፍት
አብርሐም ፫


ምዕራፍ ፫

አብርሐም ስለጸሀይ ጨረቃና ከዋክብት በኡሪምና ቱሚሙን መሰረት ተማረ—ስለመንፈሶች ዘለአለማዊነት ጌታ ገለጠለት—ከምድር በፊት ስለነበረው ህይወት፣ ስለቀድሞ መመረጥ፣ ስለፍጥረት፣ ስለአዳኝ ምርጫ፣ እና ስለሰው ዳግመኛ ሁኔታ ተማረ።

እና እኔ አብርሐም በከለዳውያን ዑር ውስጥ ጌታ አምላኬ የሰጠኝ ኡሪምና ቱሚም ነበረኝ፣

እና ከዋክብቱ ታላቅ እንደነበሩ፣ እና አንድያውም በእግዚአብሔር ዙፋን አጠገብ ቀርቦ ይገኝ እንደነበር አየሁ፤ እና በአጠገቡም የነበሩ ብዙ ታላላቆችም ነበሩ፤

እና ጌታም እንዲህ አለኝ፥ እነዚህ ገዢዎች ናቸው፤ እና አጠገቤ ስለሆነና፣ የታላቁ ስም ቆሎብ ነው፣ እኔ ጌታ አምላክ ነኝና፥ ይህ ከቆምክበት አንድ አይነት ስርዓት ለሆኑት ሁሉ እንዲመራም ሰጥቼዋለሁ።

በኡሪምና ቱሚም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፥ ያ ቆሎብ በሚዞርበት ጊዜያትና ወቅቶች መሰረት፣ እንደ ጌታ ስርዓት አማካይነት ነው፤ እናም አምላክ እንደሚያውቀው የአንድ ቀን መዞሪያ፣ አንተ በቆምክበት ስፍራ እንደተሰጠው ሰአት አንድ ሺህ አመት ነው። ይህም በቆሎብ የሚቆጠረው ሰአት፣ አምላክ የሚቆጥርበት ሰአት ነው።

ጌታም እንዲህ አለኝ፥ ታናሽ ብርሃን ያላት አለም፣ ቀኑን ከምታሰለጥነው በታች ብርሃን ያላት፣ እንዲሁም የማታው፣ አንተ አውቀሀት ከምትቆምባት አለም በላይ ታላቅ ነች፣ ይህች የምትሄደው በዝግታ ስለሆነ ነውና፤ ይህም ስርዓቱ የሆነበት ምክንያት ከቆምክበት መሬት በላይ ስለሚገኝ ነው፣ ስለዚህ የሚቆጠርበት ሰአቱ ከቀናት፣ ወራትና አመታት ቁጥር አይነት የሚበዛ አይደለም።

ጌታም እንዲህ አለኝ፥ አሁን፣ አብርሐም፣ እነዚህ ሁለት እውነቶች አሉ፣ እነሆ አይኖችህ ይህን አይተዋል፤ አንተም የጊዜ አቆጣጠርን፣ እና ሰአትን እንድትወስን፣ አዎን፣ በቆምክበት ምድር ላይ ሰአትን ለመወሰን፣ እና ቀኑን እንድታሰለጥን ለተሰጣት ብርሀን ሰአትን ለመወሰን፣ እናም ማታውንም እንድትመራ ለተሰጣት ታናሽ ብርሀን ሰአትን ለመወሰን ስለተሰጣት እንድታውቅ ተሰጥቶሀል።

አሁን ለታናሿ ብርሀን የተወሰነው ሰአት አንተ ከቆምክበት ምድር ከሚቆጠረው ጊዜ በላይ በጣም ረጅም ነው።

እና እነዚህ ሁለት እውነቶች በሚገኙበት፣ ሌላ የሚበልጣቸው እውነትም ይገኛል፣ ይህም የጊዜ አቆጣጠሩ ከዚህ የሚበልጥ ሌላ አለምም አለ።

እንደዚህም በጌታ ጊዜ አቆጣጠር ከሆነው ወደ ቆሎብ እስክትመጣ ድረስ፣ ከአንዱ አለም ውስጥ በአቆጣጠር ከሌላው የሚበልጥ አለ፤ ቆሎብም በእግዚአብሔር ዙፋን አጠገብ፣ አንተ በቆምክበት ስፍራ አይነት ስርዓት ካላቸው ሌሎች አለማትን እንድትመራ የተወሰነች ነች።

እና ወደ እግዚአብሔር ዙፋን እስክትቀርብ ድረስ፣ ብርሀን እንዲሰጡ ለታዘዙት ከዋክብት ላይ እንዴት ጊዜ እንደሚቆጠሩ እንድታውቅ ተሰጥቶሀል።

፲፩ እንደዚህም እኔ አብርሐም ከጌታ ጋር ፊት ለፊት፣ አንድ ሰው ከሌላ ጋር እንደሚነጋገር ተነጋገርኩ፤ እና በእጁም ስለሰራቸው ስራዎችም ነገረኝ፤

፲፪ እና እንዲህም አለኝ፥ ልጄ ሆይ ልጄ ሆይ (እና እጁ ተዘርግቶ ነበር)፣ እነሆ እነዚህን ሁሉ ነገሮች አሳይሀለሁ። እና እጁን በአይኖቼ ላይ አደረገ፣ እና በእጁ የሰራቸውን እነዚያን ነገሮች አየሁ፣ እነርሱም ብዙ ነበሩ፤ እና በአይኔ ፊት ተባዙ፣ እና መጨረሻቸውንም ማየት አልቻልኩም።

፲፫ እና እንዲህም አለኝ፥ ይህ ሽኒሀህ፣ ይህም ጸሀይ ነው። እና እንዲህም አለኝ፥ ቆቆብ፣ ይህም ኮኮብ ነው። እና እንዲህም አለኝ፥ ኦሌያ፣ ይህም ጨረቃ ነው። እና እንዲህ አለኝ፥ ቆቃውቢም፣ ይህም ከዋክብት ማለት፣ ወይም በሰማይ ጠፈር ላይ የሚገኙት የነበሩ ሁሉም ታላቅ ብርሃናት ናቸው።

፲፬ እና እነዚህን ቃላት ጌታ ሲነግረኝ ምሽት ነበር፥ አንተን እና ከአንተ በኋላ የሚመጡትን ዘሮችህን አበዛለሁ፤ እና አሸዋዎችን መቁጠር ከቻልክ፣ የአንተ ዘር ቁጥርም እንዲሁ ይሆናል።

፲፭ አምላክም እንዲህ አለኝ፥ አብርሐም፣ እነዚህን ቃላትን ትገልጽ፣ ወደግብፅ ከመግባትህ በፊት እነዚህን ነገሮች አሳየሁህ።

፲፮ ሁለት ነገሮች ቢኖሩ፣ እና አንዱም ከሌላው በላይ ቢሆን፣ ከእነርሱም በላይ የሚበልጡም ነገሮች ይኖራሉ፤ ስለዚህ ቆሎብ ካየሀቸው ቆቃውቢም በላይ ሁሉ ታላቅ ነው፣ ምክንያቱም ይህም ከሁሉም በላይ የቀረበ ስለሆነ ነው።

፲፯ አሁን፣ ሁለት ነገሮች ቢኖሩ፣ አንዱም ከሌላው በላይ ቢሆን፣ እና ጨረቃም ከምድር በላይ ብትሆን፣ ከዚያም ከዚህም በላይ የሆነ ሌላ አለም ወይም ኮኮብ ይኖራል፤ እና ጌታ አምላክህ ለሚያደርጋቸው ነገሮች ካልሆነ በስተቀር በልቡ ለማድረግ የሚያስብ ምንም ነገር የለም።

፲፰ ታላቅ ኮኮብ እንዴት ሰራ፤ ደግሞም፣ ሁለት መንፈሶች ከኖሩ፣ እናም አንዱ ከሌላው በላይ ባለእውቀት ከሆነ፣ ምንም እንኳን አንደኛው ከሌላው ባለእውቀት ቢሆንም እነዚህ መንፈሶች መጀመሪያ የላቸውም፤ ከዚህ በፊትም ኖረዋል፣ መጨረሻም አይኖራቸውም፣ ከዚህ በኋላም ይኖራሉ፣ እነርሱ ግኖሉም፣ ወይም ዘለአለማዊ ናቸውና።

፲፱ ጌታም እንዲህ አለኝ፥ እነዚህ ሁለት እውነቶች አሉ፣ ሁለት መንፈሶች አሉ፣ እናም አንዱ ከሌላው በላይ እውቀተኛ ነው፤ ከእነርሱ በላይ እውቀት ያለው ሌላም ይኖራል፤ እኔ ጌታ አምላክህ ነኝ፣ እኔም ከሁሉም በላይ እውቀተኛ ነኝ።

ጌታ አምላክህ መላእክቱን ሰዶ ከኤልከናኽ ቄስ እጆች አድኖሀል

፳፩ ከእነርሱ ሁሉ መካከል እኖራለሁ፤ ስለዚህ አሁን ወደ አንተ ዘንድ፣ ከሁሉም ውስጥ ጥበቤ ታላቅ በሆነው፣ በእጄ ስለተሰሩት ስራዎች ልገልፅልህ ወርጄአለሁ፣ አይኖችህ ከመጀመሪያ ጊዜ ጀምሮ ካዩዋቸው ባለእውቀቶች ሁሉ ላይ በጥበብና በጥንቃቄ በበላይ ሰማይንና በበታች ምድርን እመራለሁና፤ ካየሀቸውም ባለእውቀቶች መካከል በመጀመሪያም ወርጄአለሁ።

፳፪ አሁን ለእኔ አብርሐም ጌታ አለም ከመመስረቱ በፊት የነበሩትን ባለእውቀቶችን አሳየኝ፤ ከእነዚህ መካከልም ብዙ ታላቅ እና መኳንንትም ነበሩ።

፳፫ እና እግዚአብሔር እነዚህ ነፍሶች መልካም እንደሆኑ አየ፣ እና በመካከላቸውም ቆመ፣ እንዲህም አለ፥ እነዚህን መሪዎቼ አደርጋለሁ፤ መንፈስ ከሆኑት መካከል ቆሞ ነበርና፣ እና መልካምም እንደነበሩ አየ፤ እንዲህም አለኝ፥ አብርሐም፣ አንተ ከእነርሱ አንዱ ነህ፤ ከመወለድህ በፊትም ተመርጠህ ነበር።

፳፬ እና ከእነርሱም መካከል እግዚአብሔርን የሚመስል አንድም ቆሞ ነበር፣ እና ከእርሱ ጋር ለነበሩትም እንዲህ አላቸው፥ እንወርዳለን፣ በዚያም ስፍራ አለና፣ እና እነዚህን ነገሮች እንወስዳለን፣ እና እነዚህ ሊኖሩበት የሚችሉበትን ምድርን እንሰራለን

፳፭ እና ጌታ አምላክ የሚያዛቸውን ማናቸውንም ነገሮች ሁሉ እንደሚያደርጉ ለማየት፣ በዚህ እንፈትናቸዋለን

፳፮ እና የመጀመሪያ ሁኔታቸውን የጠበቁትም ይጨመርላቸዋል፤ እና ይህን የመጀመሪያውን ሁኔታቸውን ያልጠበቁትም ከዚህ አይነት መንግስት ውስጥ የመጀመሪያው ሁኔታቸውን ከጠበቁት ጋር ክብር አይኖራቸውም፤ እና ሁለተኛ ሁኔታቸውን የጠበቁትም በራሳቸው ላይ ክብር ከዘለአለም እስከ ዘለአለም ይጨመርላቸዋል።

፳፯ እና ጌታ እንዲህ አለ፥ ማንን እልካለሁ? እና አንዱም እንደ ሰው ልጅ መለሰ፥ እዚህ አለሁ፣ እኔን ላከኝ። እና ሌላም መለሰ እና እንዲህም አለ፥ በዚህ አለሁ፣ እኔን ላከኝ። እና ጌታ እንዲህ አለ፥ የመጀመሪያውን እልካለሁ።

፳፰ እና ሁለተኛውም ተቆጣ፣ እና የመጀመሪያ ሁኔታውን አልጠበቀም፤ እናም በዚያም ቀን፣ ብዙዎች ተከተሉት።