ቅዱሳት መጻህፍት
አብርሐም ፬


ምዕራፍ ፬

አማልክት ምድርንና በዚያም ህይወቶችን በሙሉ ለመፍጠር አቀዱ—በስድስት ቀን የመፍጠሪያ እቅዳቸው ተዘርዝረዋል።

እና ጌታም እንዲህ አለ፥ ወደዚያ እንውረድ። በመጀመሪያውም ጊዜ ወረዱ፣ እና እነርሱ፣ ይህም ማለት አማልክቱ፣ ወረዱና ሰማያትንና ምድርን መሰረቱም ሰሩም።

ከምድር ሌላ ምንም ነገሮች ስላልሰሩ፣ ምድርን ከሰሯት በኋላ ባዶ እና ባዶማ ነበረች፤ ጭለማም በጥልቁ ፊት ላይ ነግሶ ነበር፣ እናም የአማልክቱ መንፈስም በውሃዎቹ ፊት ላይ በቅርበት ተንጠለጠሉ

እነርሱም (አማልክቱ) ብርሀን ይሁን አሉ፤ እና ብርሃንም ሆነ።

እና እነርሱ (አማልክቱ) ብርሀኑ ገባቸው፣ ደማቅ ነበርና፤ እና እነርሱም ብርሀኑን ከጭለማ ከፋፈሉት፣ ወይም እንዲከፋፈል አደረጉት።

አማልክቱም ብርሀኑን ቀን ብለው ጠሩት፣ እና ጭለማውን ሌሊት ብለው ጠሩት። እንዲህም ሆነ ከምሽት እስከ ጠዋት ድረስ ሌሊት ብለው ጠሩት፤ ከጠዋት እስከ ምሽት ድረስም ቀን ብለው ጠሩት፤ እና ቀንና ሌሊት ብለው ከጠሩት ይህ የመጀመሪያው ቀን ነበር።

አማልክቱም ደግመው እንዲህ አሉ፥ በውሃዎቹ መሀከል ጠፈር ይኑሩ፣ እና ይህም ውሀዎችን ከውሀዎች ይክፈል።

እና አማልክቱ ጠፈሩን አዘዙ፣ በዚህም ይህም ከጠፈሩ በታች የነበሩትን ከጠፈሩ በላይ ከነበሩት ከፋፈላቸው፤ እና እንደዚህም፣ እንዲሁም እንዳዘዙት ሆነ።

እና አማልክቱ ጠፈሩን ሰማይ ብለው ጠሩት። እንዲህም ሆነ ከምሽት እስከ ጠዋት ድረስ ሌሊት ብለው ጠሩት፤ ከጠዋት እስከ ምሽት ድረስም ቀን ብለው ጠሩት፤ እና ይህም ለሁለተኛ ጊዜ ሌሊትና ቀን ብለው ይጠሩት ነበር።

እና አማልክት እንዲህ በማለት አዘዙ፥ ከሰማይ በታች ያሉት ውሀዎች በአንድ ስፍራ ይከማቹ፣ እና ምድሩም ወጥቶ ይድረቅ፤ እና እንዳዘዙትም እንዲህ ሆነ።

እና አማልክቱ ደረቁን ምድር መሬት ብለው አስታወቁ፤ እና በአንድነት የተሰበሰበውን ውሃ፣ ታላቅ ውሀዎች ብለው አስታወቁት፤ እናም አማልክቱ ትእዛዛቸው እንደተከበሩ አዩ።

፲፩ አማልክቱም እንዲህ አሉ፥ ምድርን ሳር እንድታሳድግ፤ ተክሎችም ዘር እንዲሰጡ፣ ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችም የራሳቸው አይነት ፍሬዎች እንዲያፈሩ፣ ዘራቸውም በምድር ላይ የእነርሱን አይነት እንዲሰጥ እናዘጋጃቸው፤ እና እንዳዘዙትም እንዲህ ሆነ።

፲፪ እና አማልክት ሳሮች ዘራቸው እንዲያመጡ፣ ተክል ከራሱ ዘር ተክልን እንዲያሳድግ፣ በራሱም አይነት ዘር እንዲሰጥ፣ ምድርን አደራጁ፤ እና ምድርም ዛፍ ከዘሯ እንድታሳድግ፣ ዘር እንድታፈራ፣ በዘርም የራሷን አይነት እንድታሳድግ፤ እና አማልክት ትእዛዛቸው እንደተከናወኑ አዩ።

፲፫ እና እንዲህ ሆነ ቀናትንም ቆጠሯቸው፤ ከምሽት እስከ ጠዋት ድረስ ሌሊት ብለው ጠሩት፤ እና እንዲህም ሆነ፣ ከጠዋት እስከ ምሽት ድረስም ቀን ብለው ጠሩት፤ ይህም ሶስተኛው ጊዜ ነበር።

፲፬ እና አማልክት ብርሃናትን በሰማይ ጠፈር አደራጁ፣ እና ቀን ከሌሊት እንዲከፋፈሉ አደረጓቸው፤ እና ለምልክቶችና ለዘመናት፣ እና ለቀናትና ለአመታት እንዲሆኑም አደራጁአቸው።

፲፭ እና በሰማይ ጠፈር ለምድር ብርሀን እንዲሰጡ ብርሃናት እንዲሆኑ አደራጁአቸው፤ እና እንዲህም ሆነ።

፲፮ አማልክትም ሁለት ታላቅ ብርሃናትን አደራጁ፣ ታላቁን ብርሃን በቀን እንዲሰለጥን፣ እና ታናሹን ብርሀን በሌሊት እንዲሰለጥን፤ ከታናሹ ብርሀንም ጋር ከዋክብትን አስቀመጡ፤

፲፯ አማልክትም ለምድር ብርሀንን እንዲሰጡ፣ እና ቀንንና ለሊትን እንዲያሰለጥኑ፣ እናም ብርሀኑን ከጭለማ እንዲከፋፍሉ፣ እነዚህን በሰማይ ጠፈሮች ላይ አስቀመጧቸው።

፲፰ እና ያዘዙት እስከሚከናወኑም ድረስ እነዚህን ነገሮች አማልክቱ ተመለከቱ።

፲፱ እና እንዲህ ሆነ ከምሽት እስከ ጠዋት ድረስ ሌሊት ነበር፤ እንዲህም ሆነ ከጠዋት እስከ ምሽት ድረስ ቀን ነበር፤ እናም ይህም የአራተኛው ጊዜ ነበር።

አማልክቱም አሉ፥ ውሀዎች ህይወት ባላቸው ፍጡራን እንዲሞሉ ውሀዎችን እናዘጋጅ፣ እና ወፎች ከምድር በላይ በሰማይ ጠፈር እንዲበሩም እናዘጋጅ።

፳፩ እና አማልክት ታላቅ አሳነባሪዎችን፣ እና የሚርመሰመሱ ህይወት ያላቸው ፍጡራንን፣ ውሀዎች እንደየወገናቸው በብዛት ውሀዎች እንዲያመጡ አዘጋጁ፤ እና ክንፍ ያላቸውን ወፎች እንደየወገናቸው። እና አማልክቱ ትእዛዛቸው እንደሚከናወኑ፣ እናም እቅዳቸው መልካም እንደሆኑም አዩ።

፳፪ እና አማልክቱ አሉ፥ እንባርካቸዋለን፣ እና እንዲበዙና እንዲባዙ እናደርጋቸዋለን፣ እና የባህር ወይም የታላቅ ውሃዎችን ውሀ እንሞላቸዋለን፤ እና ወፎችንም በምድር እንዲባዙ እናደርጋቸዋለን።

፳፫ እና እንዲህ ሆነ ከምሽት እስከ ጠዋት ድረስ ሌሊት ብለው ጠሩት፤ እና እንዲህ ሆነ ከጠዋት እስከ ምሽት ድረስም ቀን ብለው ጠሩት፤ እና ይህም የአምስተኛው ጊዜ ነበር።

፳፬ እና አማልክቱ ምድር ህያው ፍጡራንን እንደወገናቸው፣ ከብቶችንና ተንቀሳቃሾች ነገሮችን፣ እና የምድርን የዱር እንስሣት እንደወገናቸው እንዲመጡ አዘጋጁአቸው፤ እንዳሉትም፣ እንዲህ ሆነ።

፳፭ አማልክት ምድር የዱር እንሣት እንደየወገናቸው፣ እና ከብቶችን እንደወገናቸው፣ እና በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጡራንን እንደየወገናቸው አደራጁ፤ እና አማልክት እንደሚታዘዙም አዩ።

፳፮ እና አማልክት ተመካከሩና እንዲህ አሉ፥ እንሂድና ሰውን በመልካችን፣ በአምሳላችን፣ እንስራ፤ እና በባህር ዓሶች፣ በሰማይ ወፎች፣ በከብቶች፣ እናም በምድር ሁሉ ላይ፣ እናም በምድር በሚንቀሳቀሱት ፍጡራን ሁሉ ላይ ስልጣን እንስጣቸው።

፳፯ ስለዚህ አማልክት ሰውን በእራሳቸው መልክ፣ በአማልክቱ መልክም እነርሱን፣ ወንድና ሴትን አድርገው አደራጇቸው።

፳፰ እና አማልክትም እንዲህ አሉ፥ እንባርካቸዋለን። እና አማልክትም እንዲህ አሉ፥ እንዲበዙና እንዲባዙ፣ እና ምድርንም እንዲሞሏት፣ እና እንዲገዟት፣ እና የባህር ዓሶችን፣ እና የሰማይን ወፎች፣ እና በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትን ህያዋን ፍጡራንን ሁሉ እንዲገዟቸው እናደርጋለን።

፳፱ እና አማልክትም እንዲህ አሉ፥ እነሆ፣ በምድር ላይ የሚመጡትን ዘር የሚሰጡ ተክሎችን ሁሉ፣ እና ፍሬያቸው ያለባቸውን እያንዳንዱን ዛፎች ሁሉ እንሰጣቸዋለን፤ አዎን፣ ዘሮች የሚሰጡ የዛፍ ፍሬዎች እንሰጣቸዋለን፤ ይህም ለእነርሱ ምግባቸው ይሆናሉ።

እና ለምድር አራዊት ሁሉ፣ እና ለሰማይ ወፎች ሁሉ፣ እና በምድር ላይ ለሚንቀሳቀሱ ህያዋን ፍጡራን ሁሉ፣ እነሆ፣ ህይወትን እንሰጣቸዋለን፣ እና እያንዳንዱን ለምለም ተክል ምግብ እንዲሆናቸው እንሰጣቸዋለን፣ እና እነዚህ ነገሮች ሁሉ እንደዚህ ይደራጃሉ።

፴፩ እና አማልክትም እንዲህ አሉ፥ ያልናቸውን ነገሮች ሁሉ እናደርጋለን፣ እና እናደራጃቸዋለን፤ እና እነሆ፣ በጣም ታዛዦች ይሆናሉ። እና እንዲህ ሆነ ከምሽት እስከ ጠዋት ድረስ ብለው ጠሩት፤ እና እንዲህ ሆነ ከጠዋት እስከ ምሽት ድረስም ቀን ብለው ጠሩት፤ እና ለስድስተኛ ጊዜ ቆጠሩት።