ክፍል ፶
በግንቦት ፱፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ፣ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ እንደሚገልጸው፣ አንዳንድ ሽማግሌዎች እንዴት የተለያዩ መናፍስት ራሳቸውን በአለም ላይ እንደሚገልጹ እንዳልገባቸው፣ እናም ስለዚህ ጉዳይ ባደረገው ልዩ ጥያቄ ምክንያትም ይህ ራዕይ እንደተሰጠ ገለጸ። መንፈሳዊ አጋጣሚዎች የሚባሉት በአባላቱ መካከል አዲስ አልነበሩም፣ አንዳንዶችም ራዕዮችንና መግለጦንች ተቀብለናል ይሉም ነበር።
፩–፭፣ ብዙ የሀሰት መናፍስት በምድር ውስጥ ይገኛሉ፤ ፮–፱፣ ለግብዞች እና ከቤተክርስቲያኗ ለሚቆረጡት ወዮላቸው፤ ፲–፲፬፣ ሽማግሌዎች ወንጌሉን በመንፈስ ይስበኩ፤ ፲፭–፳፪፣ ሰባኪዎቹ እና ሰሚዎቹም በመንፈስ መታነጽ ያስፈልጋቸዋል፤ ፳፫–፳፭፣ የማያንጸውም ከእግዚአብሔርም የሚመጣ አይደለም፤ ፳፮–፳፰፣ ታማኞች የሁሉም ነገሮች ባለቤቶች ናቸው፤ ፳፱–፴፮፣ የንጹህ ሰዎች ጸሎቶችም መልስ ያገኛሉ፤ ፴፯–፵፮፣ ክርስቶስ መልካም እረኛ እና የእስራኤል አለት ነው።
፩ የቤተክርስቲያኔ ሽማግሌዎች ሆይ፣ አድምጡ፣ እና ለሕያው አምላክም ድምፅ ጆሮአችሁን ስጡ፤ እናም በምድር ውስጥ ስላሉት መናፍስት፣ እና ቤተክርስቲያኗን እንደሚነካው እና እንደተስማማችሁት ስለጠየቃችሁኝ የሚሰጣችሁን የጥበብ ቃላት አድምጡ።
፪ እነሆ፣ እውነት እንዲህ እላችኋለሁ፣ አለምን የሚያታልሉ፣ በምድር ውስጥ የሚሄዱ፣ ብዙ ሀየሀሰት መናፍስት የሆኑ መናፍስት አሉ።
፫ እናም ሀሰይጣን፣ እንዲጥላችሁም፣ ሊያታልላችሁ ፈልጓል።
፬ እነሆ፣ እኔ ጌታ እናንተን ተመልክቼአለሁ፣ እናም በስሜ ሀበምትታወቀው ቤተክርስቲያን ውስጥም አፀያፊነቶችን ተመልክቻለሁ።
፭ ነገር ግን፣ በህይወትም ይሁን በሞት፣ ታማኝ የሆኑ እና ሀየሚጸኑ የተባረኩ ናቸው፣ ዘለአለማዊ ህይወትን ይወርሳሉና።
፮ ነገር ግን ሀለሚያስቱ እና ለግብዞችም ወዮላቸው፣ ምክንያቱም፣ ጌታ እንዲህ ይላል፣ ወደ ፍርድ አመጣቸዋለሁና።
፯ እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ መካከል፣ አንዳንዶችን በማታለል ሀለጠላት ለሀይል የሰጡ ሐግብዞች አሉ፤ ነገር ግን እነሆ መእነዚህም ደግመው ሊመለሱ ይችላሉ፤
፰ ግብዞቹ ግን፣ በዚህ ህይወትም ይሁን በሞት፣ እንደፈቃዴ ይታወቃሉ እናም ይቆረጣሉ፤ እናም ከቤተክርስቲያኔ ሀለተቆረጡ ለእነርሱ ወዮላቸው፣ በአለም ተሸንፈዋልና።
፱ ስለዚህ፣ በፊቴ እውነት እና ፅድቅ ያልሆነውን እንዳያደርግ እያንዳንዱ ሰው ይጠንቀቅ።
፲ እናም አሁን፣ በመንፈስ ወደ ቤተክርስቲያኑ ሽማግሌዎች፣ ኑ ይላል ጌታ፣ እና ይገባችሁ ዘንድ ሀእንወቃቀስ፤
፲፩ ሰው እርስ በርሱ እንደሚወቃቀስም ፊት ለፊት እንወቃቀስ።
፲፪ አሁን፣ አንድ ሰው ሲወቃቀስ ሰውም ይረዳዋል፣ ምክንያቱም እንደ ሰው ይወቃቀሳልና፣ እንዲሁም እኔ ጌታ፣ ሀይገባችሁ ዘንድ ከእናንተ ጋር እወቃቀሳለሁ።
፲፫ ስለዚህም፣ እኔ ጌታ ይህን እጠይቃችኋለሁ—ስለምን ነበር ሀየተሾማችሁት?
፲፬ ሀበመንፈስ፣ እንዲሁም እውነትን ለማስተማር በተላከው ለአፅናኝ፣ ወንጌሌን ትሰብኩ ዘንድ ነው።
፲፭ እና ከዚያም የማይገባችሁን ሀመናፍስት ተቀብላችሁ፣ እናም ከእግዚአብሔር እንደሆኑም በማስመሰል እነዚህን ትቀበላላችሁ፤ እናም በዚህስ ትጸደቃላችሁን?
፲፮ እነሆ ይህን ጥያቄ ራሳችሁ ትመልሳላችሁ፤ ይሁን እንጂ፣ ምህረት አደርግላችኋለሁ፤ ከዚህ በኋላ በእናንተ መካከል ደካማ የሆነ ሀብርቱም ይሆናል።
፲፯ እውነት እላችኋለሁ፣ በእኔ ተሹሞ እና፣ በእውነት መንፈስ በኩል፣ በአፅናኙ የእውነትን ቃል ሀለመስበክ እንዲሄድ የታዘዘ፣ ለበእውነት መንፈስ ይሰብካልን ወይስ በሌላ ዘዴ?
፲፰ እናም በሌላ ዘዴ ከሆነ ከእግዚአብሔር አይደለም።
፲፱ እና ደግሞም፣ የእውነትንስ ቃል የተቀበለው፣ በእውነት መንፈስ ነው ወይስ በሌላ ዘዴ?
፳ በሌላ ዘዴ ከሆነ ከእግዚአብሔር አይደለም።
፳፩ ስለዚህ፣ ቃልን በእውነት መንፈስ የተቀበለው በእውነት መንፈስ ተሰብኮለት እንደተቀበለው፣ የማይገባችሁ እናም የማታውቁት ለምንድን ነው?
፳፪ በዚህም ምክንያት፣ የሚሰብከው እና የሚቀበለውም እርስ በርሳቸው ይግባባሉ፣ እና ሀይተናነጻሉ እና አብረውም ለይደሰታሉ።
፳፫ እና ያለማነጽ ያልሆነውም ከእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም፣ እና ሀከጭለማ ነው።
፳፬ ከእግዚአብሔር የሆነው ሀብርሀን ነው፤ እና ብርሀንን ተቀብሎ በእግዚአብሔር ለየሚቀጥል፣ ሐተጨማሪ ብርሀንን ይቀበላል፤ እናም ብርሀኑም ፍጹም እስከሆነው ቀን ድረስም እየጨመረ ይበራል።
፳፭ እና ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እናም ይህን የምለውም ሀእውነቱን ታውቁ ዘንድ፣ ከመካከላችሁም ጭለማን ታስወግዱ ዘንድ ነው፤
፳፮ ምንም እንኳን እርሱ ታናሽ እና የሁሉ ሀአገልጋይ ቢሆንም፣ በእግዚአብሔር የተሾመ እና የተላከ፣ እርሱ ለታላቅ ይሆን ዘንድ ተመርጧል።
፳፯ በመሆኑም፣ እርሱ የሁሉም ነገሮች ሀባለቤት ነው፤ በሰማይ እናም በምድር በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ አብ ፈቃድ የተላኩ ነገሮች ሁሉ፣ ህይወት እና ብርሀን፣ መንፈስ እና ለሀይል፣ ለእርሱ ተገዢ ናቸውና።
፳፰ ነገር ግን ከሁሉም ኃጢአት ሀየጸዳ እና ለየነጻ ካልሆነ በስተቀር ማንም ሰው የሁሉም ነገሮች ባለቤት ሊሆን አይችልም።
፳፱ እና ከሁሉም ኃጢአቶች ከጸዳችሁ እና ከነጻችሁ፤ የምትሹትን ሁሉ በኢየሱስ ስም ሀትጠይቃላችሁ እናም ይህም ይከናወናል።
፴ ነገር ግን ይህን እወቁ፣ የጠየቃችሁት ይሰጣችኋል፤ እናም ሀየመሪነት ሀላፊነት ሲሰጣችሁም፣ መናፍስትም ይገዙላችኋል።
፴፩ በመሆኑም፣ እንዲህም ይሆናል፣ የማትረዱትን ሀመንፈስ ስታዩ፣ እና መንፈሱንም ካልተቀበላችሁ፣ አብን በኢየሱስ ስም ጠይቁ፤ እና ያን መንፈስ እርሱ ካልሰጣችሁ፣ ከዚያም ከእግዚአብሔር እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።
፴፪ እና ለእናንተም በዚያ መንፈስ ላይም ሀሀይል ይሰጣችኋል፤ እና ያ መንፈስ ከእግዚአብሔር እንዳልሆነም በታላቅ ድምጽ ታሳውቁታላችሁ፣
፴፫ በመንፈሱም እንዳትሸንፉ፣ ሀበስድብ ቃል ሳይሆን፣ ወይም በዚያም እንዳትያዙ፣ ለበኩራት ወይም በደስታ ሳይሆን፣ ከእግዚአብሔር እንዳልሆነ ታሳውቁታላችሁ።
፴፬ ከእግዚአብሔር የተቀበለውም፣ ከእግዚአብሔር እንደተቀበለው ይቁጠረው፤ እናም ለመቀበልም በእግዚአብሔር ብቁ ሆኖ ስለተቆጠረም ይደሰት።
፴፭ እናም በማድመጥ እናም የተቀበላችሁትን እነዚህን ነገሮች—እናም ከአብ ሀመንግስቱን፣ እና ከእርሱ ያልተመደቡትን ነገሮች ለማሸነፍ ለሀይል ተሰጥቷችኋል—እናም ከዚህም በኋላ የምትቀበሏቸውን በማድረግ፣
፴፮ እናም እነሆ፣ በእውነትም እንዲህ እላችኋላሁ፣ በአገልጋዬ አንደበት የተሰጡትን እነዚህን ቃላቴን አሁን የምታደምጡ ሁሉ የተባረካችሁ ናችሁ፣ ለኃጢአቶቻችሁ ሀምህረት ተሰጥቷችኋልና።
፴፯ የተደሰትኩበት አገልጋዬ፣ ጆሴፍ ዌክፊልድ እና አገልጋዬ ሀፓርሊ ፒ ፕራት ከቤተክርስቲያናቱ መካከል ይሂዱ እናም ለበምክር ቃላትም ያጠናክሯቸው፤
፴፰ እናም አገልጋዬ ጆን ኮርል፣ ወይም ለዚህ ሀላፊነት የተሾሙት አገልጋዮቼ ሁሉ፣ ሀበወይን ስፍራ ወስጥ ያገልግሉ፤ እና ሀላፊነት የሰጠኋቸውን ነገሮች ያከናውኑ ዘንድ ማንም ሰው አያደናቅፋቸው—
፴፱ ስለዚህ፣ በዚህ ነገር አገልጋዬ ሀኤድዋርድ ፓርትሪጅ ትክክል አይደለም፤ ይህም ቢሆን ንስሀ ይግባ እናም ይቅርታን ይቀበላል።
፵ እነሆ፣ እናንት ህጻናት ናችሁ እና ሁሉንም ነገሮች አሁን ሀትሸከሙ ዘንድ አትችሉም፤ ለበጸጋ እና ሐበእውነት እውቀትም መማደግ አለባችሁ።
፵፩ እናንት ሀአትፍሩ፣ ለህጻናት፣ የእኔ ናችሁና፣ እናም እኔ አለምን ሐአሸንፌዋለሁ፣ እና እናንተም ከአባቴ ዘንድ መየተሰጣችሁ ናችሁ፤
፵፪ አባቴ ከሰጠኝ ማንኛቸውም ሀአይጠፋም።
፵፫ እናም አብ እና እኔ ሀአንድ ነን። እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ ነው፤ እና እኔን ከተቀበላችሁ፣ እናንተ በእኔ አላችሁ እና እኔም በእናንተ አለሁ።
፵፬ ስለዚህ፣ እኔ በመሀከላችሁ ነኝ፣ እና እኔም ሀመልካሙ እረኛ፣ እና የእስራኤል ለድንጋይ ነኝ። በዚህ ሐአለት ላይ የተመሰረተም መአይወድቅም።
፵፭ እና ድምጼን የምትሰሙበትና እና ሀየምታዩኝ፣ እና እኔ እንደሆንኩኝም የምታውቁበት ቀን ይመጣል።