ክፍል ፮
ሚያዚያ ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ፣ ፔንስልቬንያ፣ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ለኦሊቨር ካውድሪ የተሰጠ ራዕይ። በሚያዚያ ፯፣ ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) ኦሊቨር ካውድሪ የመፅሐፈ ሞርሞን ትርጉም ጸሐፊ በመሆን ማገልገል ጀመረ። የመፅሐፈ ሞርሞን መዛግብት የተቀረጹበትን ሰሌዳዎች በተመለከተ ስለነቢዩ ምስክርነት እውነትነት ቀደም ብሎ መለኮታዊ መገለጥን ተቀብሎ ነበር። ነቢዩ በኡሪምና ቱሚም ጌታን ጠየቀ እናም ይህን መልስ ተቀበለ።
፩–፮፣ በጌታ የእርሻ ስፍራ የሚያገለግሉ ሰራተኞች ደህንነትን ያገኛሉ፤ ፯–፲፫፣ ከደህንነት ስጦታ የበለጠ ስጦታ የለም፤ ፲፬–፳፯፣ የእውነት ምስክርነት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይመጣል፤ ፳፰–፴፯፣ ወደ ክርስቶስ ተመልከቱ እናም ሁልጊዜ መልካምን አድርጉ።
፩ ታላቅ እና ሀድንቅ ስራ ወደ ሰዎች ልጆች ሊመጣ ነው።
፪ እነሆ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ፈጣን እና ሀያል፣ ሁለት ስለት ካለው ሰይፍ ይልቅ ሀየተሳለ፣ መገጣጠሚያን እና መቅኔን እስኪለይ ድረስ የሚሰራውን ለቃሌን አድምጡ፤ ስለዚህ ቃሎቼን አድምጡ።
፫ እነሆ፣ ሀየእርሻው ስፍራ ነጭ ሆኖ አዝመራው ዝግጁ ነው፣ ስለዚህ፣ ለነፍሱም ዘለአለማዊ ደህንነት በእግዚአብሔር መንግስት ያከማች ዘንድ መሰብሰብ የሚሻ በኃይሉ ይጨድ እናም ቀኑም እየመሸ ሳለም ይሰብስብ።
፬ አዎን፣ ማንኛውም ሀየሚያጭድ እናም የሚሰበስብ፣ እንዲሁ በእግዚአብሔር የተጠራ ነው።
፭ ስለዚህ፣ እኔን ሀብትጠይቁኝ ትቀበላላችሁ፣ ካንኳኳችሁ ይከፈትላችኋል።
፮ አሁን፣ እንደጠየቃችሁት፣ እነሆ፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ ትእዛዛቴን ጠብቁ እናም ሀየፅዮንን አስተሳሰብ ለማምጣት እና ለመመስረት ለእሹ፤
፯ ሀጥበብን እንጂ ለሀብትን ሐአትሹ፣ እናም እነሆ፣ የእግዚአብሔር መሚስጥራት ይገለጡላችኋል፣ እናም ባለጠጋም ትሆናላችሁ። እነሆ፣ ሠዘለዓለማዊ ሕይወት ያለው እርሱም ባለጠጋ ነውና።
፰ እውነት፣ እውነት፣ እላችኋለሁ፣ ላደርግላችሁ እንደምትሹ እንዲሁ ይሆንላችኋል፤ የምትሹ ከሆነም ካላችሁ፣ በዚህ ትውልድ ውስጥ ለብዙ መልካም ነገሮች መከናወን መሳሪያ ትሆናላችሁ።
፱ ለዚህ ትውልድ ሀከንስሀ በቀር ሌላ ምንም አትናገሩ፤ ትእዛዛቴን ጠብቁ፣ እናም ስራዬን በትእዛዛቴ መሰረት ለማምጣት እርዱ፣ እናም ትባረካላችሁ።
፲ እነሆ ስጦታ አላችሁ፣ እናም በስጦታችሁም የተነስ የተባረካችሁ ናችሁ። ሀይህም የተቀደሰ እና ከላይ የመጣ መሆኑን አስታውሱ—
፲፩ እናም ሀከጠየቅህ፣ ታላቅ እና ድንቅ የሆኑ ለሚስጥራትን ታውቃለህ፤ ስለዚህም ሚስጥራትን ታውቅ ዘንድ፣ ብዙዎችንም ወደ እውነት እውቀት ታመጣ ዘንድ፣ አዎን፣ የተሳሳተ መንገዳቸውን ሁሉ እንዲተው ሐታሳምናቸውም ዘንድ መስጦታህን ትጠቀምበታለህ።
፲፪ በአንተ እምነት ውስጥ ካልሆኑ በስተቀር ስጦታህን ለማንም አታሳውቅ። ሀበተቀደሱ ነገሮች አትቀልድ።
፲፫ መልካምን ካላደረግህ፣ እናም እስከ ሀመጨረሻም ለበእምነት ሐከጸናህ ከእግዚአብሔር የስጦታዎች ሁሉ የበላይ በሆነው በእግዚአብሔር መንግስት ትድናለህ፤ መከደህንነት በላይ የሆነ ምንም ስጦታ የለምና።
፲፬ እውነት፣ እውነት፣ እልሀለሁ፣ ባደረግኸው የተባረክህ ነህ፤ ምክንያቱም እኔን ሀጠይቀኃል እናም በጠየቅኸው መጠን የመንፈሴን መመሪያ ተቀብለኃል። ይህ ባይሆን ኖሮ አሁን ያለህበት ስፍራ ባልደረስህ ነበር።
፲፭ እነሆ፣ እንደጠየቅኸኝ ታውቃለህ እናም ሀአዕምሮህን አብርቻለሁ፤ እናም አሁን በእውነት መንፈስ መረዳትን እንዳገኘህ ታውቅ ዘንድ እነዚህን ነገሮች እነግርሀለሁ፤
፲፮ አዎን፣ ከእግዚአብሔር በስተቀር ማንም ሀሳብህንና ሀየልብህን ፈቃድ እንደማያውቅ ለእንድታውቅ ዘንድ እነግርሀለሁ።
፲፯ እየጻፍህ ያለው ቃላት ወይም ስራ ሀእውነት እንደሆነ—ለአንተ እንደምስክርነት እነዚህን ነገሮች እነግርሀለሁ።
፲፰ ስለዚህ ሀትጉህ ሁን፤ በታማኝነት፣ ለቃሉ ሲል በሚገጥመው በማንኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ከአገልጋዬ ከጆሴፍ ጎን ለቁም።
፲፱ በስህተቱም ገስጸው፣ እናም ከእርሱም ተግሳጽን ተቀበል። ትዕግስተኛ ሁን፤ የተረጋጋህ ሁን፣ ራስህን ግዛ፣ ትዕግስት፣ እምነት፣ ተስፋ እና ልግስና ይኑርህ።
፳ እነሆ፣ አንተ ኦሊቭር ነህ፣ እናም በፈቃድህ ምክንያት ተናግሬሀለሁ፤ ስለዚህ እነዚህን ቃላት በልብህ ሀአከማች። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጠበቅታማኝ እና ትጉህ ሁን፣ እናም በፍቅሬ እቅፍ ውስጥም አደርግሀለሁ።
፳፩ እነሆ፣ እኔ ሀየእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ። ለየእኔው ወደሆኑት የመጣሁት እናም የራሴም ያልተቀበሉኝ እኔው ነኝ። እኔ በጭለማም የማበራ ሐብርሀን ነኝ፣ እናም መጭለማውም አይገነዘበውም።
፳፪ እውነት፣ እውነት፣ እልሀለሁ፣ ተጨማሪ ምስክርነትን ከፈለግህ፣ ስለ እነዚህ ነገሮች ሀእውነትነት ታውቅ ዘንድ በልብህ ወደ እኔ የጮህክበትን ምሽት አስታውስ።
፳፫ ይህንን ነገር በተመለከተ ለአምሮህ ሀሰላምን አልተናገርኩምን? ከእግዚአብሔር ከመጣ ምስክርነት ይልቅ ምን አይነት ለምስክርነት ትፈልጋለህ?
፳፬ እናም አሁን፣ እነሆ፣ ምስክርነትን ተቀብለሀል፤ ሌላ ሰው የማያውቃቸውን ነገሮች ነግሬህ ምስክርነትን አልተቀበልክምን?
፳፭ እናም፣ እነሆ፣ ከእኔም የምሻ ከሆነ ልክ እንደ አገልጋዬ ጆሴፍ ሀትተረጉም ዘንድ ስጦታን እሰጥሀለሁ።
፳፮ እውነት፣ እውነት፣ እልሀለሁ፣ በሰዎች ሀኃጢአት የተነሳ ያስቀረኋቸው አብዛኛውን ወንጌሌን የያዙ ለጽሁፎች አሉ።
፳፯ እናም አሁን አዝሀለሁ፥ ለራስህ ሀብትን በሰማይ የማከማቸት ፈቃድ የሆነ መልካም ፈቃድ ካለህ፣ ከዚያም፣ በኃጢአት የተነሳ ተደብቀው የነበሩትን ሀቅዱሳን መጻህፍቴን በስጦታህ ወደ ብርሀን በማምጣት ትረዳለህ።
፳፰ እናም አሁን፣ እነሆ፣ ለአንተ እና ለአገልጋዬ ለጆሴፍ ይህንን አገልግሎት ወደ ብርሀን የሚያመጣውን ስጦታ ቁልፍ እሰጣችኋለሁ፤ በሁለት ወይም በሶስት ሀምስክር አንደበት ሁሉም ቃል ይጸናል።
፳፱ እውነት፣ እውነት፣ እልሀለሁ፣ ቃሌን እና የዚህን የወንጌል ክፍል እናም አገልግሎቴን የማይቀበሉ ከሆኑ፣ የተባረካችሁ ናችሁ፣ ምክንያቱም በእኔ ላይ ካደረጉብኝ በላይ ሊያደርጉባችሁ አይችሉምና።
፴ እናም በእኔ ላይ እንዳደረጉት እንዲሁ በእናንተ ላይ ሀቢያደርጉም እንኳን፣ የተባረካችሁ ናችሁ፣ ከእኔም ጋር ለበክብር ሐትኖራላችሁና።
፴፩ ነገር ግን በሚሰጠው ሀምስክርነት የሚጸናውን ቃሌን ለካልተቃወሙ፣ የተባረኩ ናቸው፣ እና ከዚያም በስራችሁ ፍሬ ትደሰታላችሁ።
፴፪ እውነት፣ እውነት፣ እልሀለሁ፣ ልክ ለደቀመዛሙርቴ እንደተናገርሁት፣ ሁለት ወይም ሶስት ሆነው በስሜ፣ አንድን ነገር በተመለከተ፣ ሀበሚሰበሰቡበት፣ በዚያም ለበመካከላቸው እሆናለሁ፣ እንዲሁም በመካከላችሁ ነኝ።
፴፫ ልጆቼ፣ መልካምን ለማድረግ ሀአትፍሩ፣ ለየዘራችሁትን ያንኑ መልሳችሁ ታጭዳላችሁ፤ ስለዚህ መልካምን ከዘራችሁ ያንኑ መልካም የሆነውን እንደ ደመወዝ ታጭዳላችሁ።
፴፬ ስለዚህ፣ አትፍሩ፣ እናንት ትንሽ መንጋዎች፣ መልካምን አድርጉ፤ ምድርና ገሀነም ቢቀናጁባችሁም፣ በእኔ ሀዐለት ላይ ከተገነባችሁ ሊቋቋሟችሁ አይችሉምና።
፴፭ እነሆ፣ አልኮንናችሁም፤ በመንገዳችሁ ሂዱ እናም ዳግምም ሀኃጢአትን አትስሩ፤ ያዘዝኳችሁን ስራ በርጋታ እከናውኑ።
፴፮ ባሰባችሁት ነገር ሁሉ ወደ እኔ ሀተመልከቱ፤ አትጠራጠሩ፣ አትፍሩ።
፴፯ ጎኔ ላይ የተወጋሁት ቁስል፣ እናም በእጄ እና በእግሬ ላይ ያሉትን ሀየምስማር ምልክቶች ለአስቧቸው፤ እናም እምነት ይኑራችሁ፣ ትእዛዛቴን ጠብቁ፣ እናም ሐመንግስተ ሰማያትን መትወርሳላችሁ። አሜን።