ክፍል ፺፫
በግንቦት ፮፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ።
፩–፭፣ ታማኝ የሆኑ ሁሉ ጌታን ያያሉ፤ ፮–፲፰፣ የእግዚአብሔር ልጅ የአብን ክብር በሙላት እስከሚቀበል ድረስ ከጸጋ ወደ ጸጋ እንደሄደ ዮሐንስ መሰከረ፤ ፲፱–፳፣ ታማኝ ሰዎች፣ ከጸጋ ወደ ጸጋ በመሄድ ሙሉነቱን ደግመው መቀበል ይችላሉ፤ ፳፩–፳፪፣ በክርስቶስ በኩል የተወለዱትም የበኩር ቤተክርስቲያን ናቸው፤ ፳፫–፳፰፣ ክርስቶስ የእውነትን ሁሉ ሙላት ተቀበለ፣ እና ሰውም በታዛዥነት ይህንኑ ሊያደርግ ይችላል፤ ፳፱–፴፪፣ ሰው በመጀመሪያም ከእግዚአብሔር ጋር ነበር፤ ፴፫–፴፭፣ ንጥረ-ነገሮች ዘለአለማዊ ናቸው፣ እና ሰው የደስታን ሙላት በትንሳኤ ሊቀበል ይችላል፤ ፴፮–፴፯፣ የእግዚአብሔር ክብር የመረዳት ችሎታ ነው፤ ፴፰–፵፣ በክርስቶስ ቤዛነት ምክንያት ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ንጹሀን ናቸው፤ ፵፩–፶፫፣ መሪ ወንድሞች ቤተሰቦቻቸውን በስርዓት እንዲያደራጁ ታዘዙ።
፩ በእውነት፣ ጌታ እንዲህ ይላል፥ ሀኃጢአቶቹን የሚተውና ወደ እኔ የሚመጣ፣ እና ስሜን ለየሚጠራ፣ እና ድምጼን ሐየሚያከብር፣ እና ትእዛዛቴን የሚያከብር እያንዳንዱ ነፍስ ሁሉ መፊቴን ሠየሚያይበት እና እኔ እንደሆንኩም የሚያውቅበት ጊዜ ይመጣል፤
፪ እና እኔ ወደ አለም ለሚመጣ ለእያንዳንዱ ሰው ሁሉ የማበራ የእውነት ሀብርሀን ነኝ፤
፫ እኔ በአብ ሀእንዳለሁ አብም በእኔ ነው እናም አብና እኔም አንድ ነን—
፬ ሙላቱን ሀስለሰጠኝ አብ ነኝ፣ እና በአለም ውስጥ ስለነበርኩና ለስጋንም ድንኳኔ ስላደረግሁ፣ እና በሰውም ልጆች መካከል ስለኖርኩ ወልድ ነኝ።
፭ በአለም ውስጥ ነበርኩ እና አባቴንም ተቀበልኩኝ፣ እና ሀስራዎቹም በግልፅ የታዩ ነበሩ።
፮ እና ሀዮሐንስ አየና ለስለክብሬ ሙላት መሰከረ፣ እና ሐየዮሐንስ ሙሉ ምስክር ከዚህ በኋላ ይገለጣል።
፯ እናም እንዲህ በማለትም መሰከረ፥ ክብሩን፣ አለም ከመሆኗ በፊት ሀከመጀመሪያ ጀምሮ እንደነበረ አየሁ፤
፰ ስለዚህ፣ በመጀመሪያው ሀቃል ነበር፣ እርሱም ቃል፣ እንዲሁም የደህንነት መላእክተኛ ነበርና—
፱ የአለም ሀብርሀን እና ለአዳኝ፤ አለም በእርሱ ሆኗልና፣ እና በእርሱም ውስጥ የሰዎች ህይወት እና የሰዎች ብርሀን ነበር፣ ወደ አለምም የመጣ የእውነት መንፈስ እርሱ ነውና።
፲ አለማት በእርሱ ሀሆነዋልና፤ ሰዎችም በእርሱ ተፈጥረዋል፤ ሁሉም ነገሮች በእርሱ፣ በእርሱም አማካይነት፣ እና ከእርሱ ሆነዋል።
፲፩ እና እኔ ዮሐንስ ክብሩን፣ በጸጋ እና በእውነት፣ እንዲሁም በመጣው እና በስጋም በኖረው፣ እና በመካከላችን በኖረው፣ በእውነት መንፈስ ተሞልቶ፣ እንደ አብ አንድያ ልጅ ክብሩን እንዳየሁ እመሰክራለሁ።
፲፪ እና እኔ ዮሐንስ በመጀመሪያ ሀሙላትን እንዳልተቀበለ፣ ነገር ግን ለበጸጋ ላይ ጸጋን እንደተቀበለ አየሁ፤
፲፫ እና ሙላትን በመጀመሪያ አልተቀበለም፣ ነገር ግን ሙላትን እስከሚቀበል ድረስ ሀከጸጋ ወደ ጸጋ ቀጠለ፤
፲፬ እና ሙላትን በመጀመሪያ ስላልተቀበለ፣ በዚህም ሀየእግዚአብሔር ልጅ ተብሎ ተጠርቷል።
፲፭ እና እኔ ሀዮሐንስ እመሰክራለሁ እና አስተውሉ፣ ሰማያት ተከፈቱ ለመንፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይም ሐበርግብ አምሳል ወረደ፣ እናም አረፈበት፣ እና ድምፅ ከሰማያት መጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ መየምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።
፲፮ እና እኔ ዮሐንስ እርሱ የአብን ክብር በሙላት እንደተቀበለ እመሰክራለሁ፤
፲፯ እና ሀሀይልን ለሁሉ፣ በሰማይ እና በምድር ላይ ተቀበለ፣ እና ሐየአብ ክብርም ከእርሱ ጋር ነበር፣ በእርሱ ውስጥም ይኖራልና።
፲፰ እና እንዲህም ይሆናል፣ እናንት ታማኝ ብትሆኑ የዮሐንስን ምስክር በሙላት ትቀበላላችሁና።
፲፱ እነዚህን አባባል የምሰጣችሁ እንድትረዱ እና እንዴት እንደምታመልኩ እንድታውቁ፣ እና ምን ሀእንደምታመልኩ እንድታውቁ፣ በስሜ ወደ አብ እንድትመጡ፣ እና በጊዜም ሙላትን ትቀበሉ ዘንድ ነው።
፳ ሀትእዛዛቴን የምታከብሩ ከሆናችሁም ለሙላቱን ትቀበላላችሁና፣ እና እኔ በአብ እንደሆንኩ እናንት በእኔ ሐትከብራላችሁ፤ ስለዚህ፣ እላችኋለሁ፣ መበጸጋ ላይ ጸጋን ትቀበላላችሁ።
፳፩ አሁንም፣ እውነት እላችኋለሁ ሀበመጀመሪያም ከአብ ዘንድ ነበርኩኝ፣ እና ለበኩርም ነኝ፤
፳፪ እና በእኔ የተወለዱትም የዚህ ሀክብር ለተካፋዮች ናቸው፣ እና የበኩር ቤተክርስቲያንም ናቸው።
፳፫ አስቀድማችሁ ሀከአብ ጋር የነበራችሁ እናንተ መንፈስ፣ እንዲሁም የእውነት መንፈስ ነበራችሁ፤
፳፬ እና ነገሮች እንዳሉ፣ እንደነበሩ፣ እናም ወደፊት እንደሚሆኑ ሀየሚታወቅበት ለእውነት ነው።
፳፭ እና ማንኛውም ከዚህ ሀበላይ ወይም በታች የሆነው ከክፉው መንፈስ ነው፣ እርሱም ከመጀመሪያ ለሀሰተኛ የነበረው ነው።
፳፮ ሀየእውነት መንፈስም እግዚአብሔር ነው። እኔ የእውነት መንፈስ ነኝ፣ እና ዮሐንስ ስለእኔ እንዲህ በማለት መስክሯል፥ የእውነትን ሙላት፣ አዎን፣ እንዲሁም ሁሉንም እውነቶች ተቀበለ።
፳፯ እና ትእዛዛቱን ካላከበረ በስተቀር ማንም ሰው ሀሙላትን አይቀበልም።
፳፰ ትእዛዛቱን ሀየሚያከብርም፣ በእውነት እና ሁሉንም ነገሮች ለበማወቅ እስከሚከበር ድረስ፣ እውነት እና ሐብርሀንን ይቀበላል።
፳፱ ሰው ደግሞ ሀበመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር ነበር። ለየመረዳት ችሎታ፣ ወይም የእውነት ብርሀን፣ የተፈጠረ ወይም የተሰራ አይደለም፣ በእርግጥም ሊሆን አይችልም።
፴ ሁሉም እውነት እግዚአብሔር ባስቀመጣቸው ተፅዕኖ አካባቢያቸው፣ በራሳቸው ሀየሚሰሩ፣ እንደየራሳቸው የመረዳት ችሎታ፣ ራሳቸውን የቻሉ ናቸው፤ አለበለዚያም ምንም አይኖርም።
፴፩ እነሆ፣ ይህ የሰው ሀነጻ ምርጫ ነው፣ እና ይህ የሰው ኩነኔ ነው፤ ከመጀመሪያ የነበረው ለበግልጽ ስለታየላቸው፣ እና ብርሀንንም አልተቀበሉትምና።
፴፪ እና መንፈሱ ሀብርሀንን የማይቀበል በእርሱ በፍርድ ላይ ነው።
፴፫ ሰው ሀመንፈስ ነውና። ለንጥረ-ነገሮች ዘለአለማዊ ናቸው፣ እና መንፈስ እና ንጥረ-ነገር ሳይለያዩ የተያያዙ፣ የደስታን ሙላትን የሚቀበሉ ናቸው።
፴፬ እና ሀሲለያዩም፣ ሰው ለየደስታን ሙላት አይቀበልም።
፴፭ ሀንጥረ-ነገሮች የእግዚአብሔር ድንኳን ናቸው፤ አዎን፣ ሰውም የእግዚአብሔር ድንኳን፣ እንዲሁም ለቤተመቅደሳት፣ ነው፤ እና ቤተመቅደሱ የረከሰ ቢሆን፣ እግዚአብሔር ያንን ቤተመቅደስ ያፈርሰዋልና።
፴፮ የእግዚአብሔር ሀክብር ለየመረዳት ችሎታ ነው፣ ወይም በሌላ ቃላት፣ ሐብርሀንና እውነት ነው።
፴፯ ብርሀን እና እውነት ሀክፉውን ይተዋል።
፴፰ እያንዳንዱ የሰው መንፈስ በመጀመሪያ ሀየዋህ ነበር፤ እና እግዚአብሔር ሰውን ለከውድቀቱ ሐሲያድን፣ ሰዎችም ዳግም በህጻንነት በእግዚአብሔር ፊት መየዋህ ሆኑ።
፴፱ ክፉውም መጣ እና፣ ባለመታዘዝና በአባቶቻቸው ሀባህል ምክንያት፣ ብርሀንን እና እውነትን ከሰዎች ልጆች ለነጠቀ።
፵ ነገር ግን ሀልጆቻችሁን በብርሀን እና በእውነት እንድታሳድጓቸው ዘንድ አዛችኋለሁ።
፵፩ ነገር ግን አገልጋዬ ፍረድሪክ ጂ ዊሊያምስ እውነት እልሀለሁ፣ በዚህ ኩነኔ ቀጥለሀል፤
፵፪ በትእዛዛትም በኩል ልጆችህን ብርሀን እና እውነት ሀአላስተማርክም፤ እና ክፉውም በአንተ ላይ ሀይል አለው፣ እና ይህም የስቃይህ ምክንያት ነው።
፵፫ አሁንም ትእዛዝ እሰጥሀለሁ—የምትድን ቢሆን ቤትህን ሀበስርዓት አደራጅ፣ በቤትህ ውስጥ አያሌ ትክክል ያልሆኑ ነገሮች አሉና።
፵፬ ለአገልጋዬ ስድኒ ሪግደን በእውነት እለዋለሁ፣ በአንዳንድ ነገሮች ልጆቹን በሚመለከት ትእዛዝን አላከበረም፤ ስለዚህ፣ አስቀድሞ ቤቱን በስርዓት ያደራጅ።
፵፭ በእውነት፣ ለአገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ ይህን እላለሁ፣ ወይም በሌላ ቃላት፣ ባልንጀሮቼ ብዬ እጠራችኋለሁ፣ እናንት ሀባልንጀሮቼ ናችሁና፣ እና ከእኔም ጋር ውርስ ይኖራችኋል—
፵፮ ሀአግልጋዮቼ ብዬ የምጠራችሁ በአለም ምክንያት ነው፣ እና እናንተም ለእነርሱ በእኔ ምክንያት አገልጋዮቻቸው ናችሁ—
፵፯ አሁንም፣ በእውነት ለአገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ እላለሁ—ትእዛዛትን አላከበርክም፣ እና በጌታ ፊትም ሀተገስጸህ መቆም ያስፈልግሀል፤
፵፰ ሀቤተሰብህ ንስሀ መግባትና አንዳንድ ነገሮችን መተው አለባቸው፣ እና የምትላቸውንም በቅንነት ማድመጥ ያስፈልጋቸዋል፣ ወይም ከስፍራቸው ይወጣሉ።
፵፱ ለአንዱ የምለው ለሁሉም እላለሁ፤ ዘወትር ሀጸልዩ አለበለዚያም ክፉው በውስጣችሁ ሀይል ይኖረዋል፣ እና ከስፍራችሁ ያስወጣችኋል።
፶ የቤተክርስቲያኔ ኤጲስ ቆጶስ፣ አገልጋዬ ኒውል ኬ ዊትኒም፣ ሊገሰፅ፣ እና ቤተሰቡን በስርዓት ሊያደራጅ፣ እና በቤትም በተጨማሪ ቅን እና አሳቢ እንዲሆኑ፣ እና ዘወትርም እንዲጸልዩ ሊያደርግ ያስፈልገዋል፣ ወይም ሀከስፍራቸው ይወጣሉ።
፶፩ ባልንጀሮቼ፣ አሁን እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ ስድኒ ሪግደን በጉዞው ይሂድ፣ እና ይፍጠን፣ እና ደግሞም በምሰጠው የንግግር ችሎታ የጌታን ሀየተወደደች አመትን፣ እና የደህንነትን ወንጌልን ያውጅ፤ እና በአንድ አላማ በምታደርጉት የእምነት ጸሎት እደግፈዋለሁ።
፶፪ እና አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ፣ እና ፍረድሪክ ጂ ዊሊያምስም ይፍጠኑ፣ እና እንድ እምነት ጸሎታቸውም ይሰጣቸዋል፤ እና እኔ የምላችሁን እስከጠበቃችሁ ድረስ በዚህ አለምም፣ ሆነ በሚመጣው አለም አትሸነፉም።
፶፫ እና፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ቅዱስ መጻሕፍቴን ሀለመተርጎም እንድትፈጥኑ፣ እና የታሪክ፣ እና የሀገሮች፣ እና የመንግስታት፣ የእግዚአብሔር እና የሰው ህግጋት ለእውቀትን ሐእንድታገኙ ፍቃዴ ነው፣ ይህም ሁሉ ለፅዮን ደህንነት ነው። አሜን።