ክፍል ፷፬
መስከረም ፲፩፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ለቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎች የተሰጠ ራዕይ። በሚዙሪ ውስጥ እያለ ለሌላ ጊዜ ያስተላለፈውን የመፅሐፍ ቅዱስን ትርጉም ስራ ደግሞ ለመጀመር፣ ነቢዩ ወደ ሀይረም ኦሀዮ ለመሄድ እየተዘጋጀ ነበር። ወደ ፅዮን (ሚዙሪ) እንዲጓዙ የታዘዙት ወንድሞችም በጥቅምት ለመሄድ በቅንነት እየተዘጋጁ ነበር። በዚህ ስራ በበዛበት ጊዜ፣ ይህን ራዕይ ተቀብሎ ነበር።
፩–፲፩፣ በራሳቸው ታላቅ ኃጢአት እንዳይቀር፣ ቅዱሳን እርስ በራሳቸውም ይቅር እንዲባባሉ ታዘዋል፤ ፲፪–፳፪፣ ንስሀ የማይገቡት በቤተክርስቲያኗ ለፍርድ ይቅረቡ፤ ፳፫–፳፭፣ አስራትን የሚከፍል በጌታ መምጫ ጊዜ አይቃጠልም፤ ፳፮–፴፪፣ ቅዱሳን እዳን እንዲያስወግዱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፤ ፴፫–፴፮፣ አመጸኞች ከፅዮን ውስጥ ይቆረጣሉ፤ ፴፯–፵፣ ቤተክርስቲያኗ አገሮችን ትፈርዳለች፤ ፵፩–፵፫፣ ፅዮን ታብባለች።
፩ እነሆ፣ ጌታ አምላካችሁ እንዲህ ይላችኋል፣ አቤቱ እናንት የቤተክርስቲያኔ ሽማግሌዎች ሆይ፣ አድምጡ እናም ስሙ፣ እናም እኔ እናንተን በተመለከተ ያለኝን ፈቃድ ተቀበሉ።
፪ እውነት እላችኋለሁ፣ አለምን ሀእንድታሸንፉ እፈልጋለሁ፤ ስለዚህ፣ በእናንተ ላይ ለርህራሄ ይኖረኛል።
፫ በመካከላችሁ ኃጢአት የሰሩ አሉ፤ ነገር ግን በእውነት እላለሁ፣ አንድ ጊዜ፣ ሀለክብሬ ስል፣ እናም ለነፍሳት ደህንነት ስል፣ ለኃጢአታችሁ ለይቅርታን አድርጌአለሁ።
፬ ለእናንተም መሀሪ እሆናለሁ፣ መንግስትንም ሰጥቻችኋለሁና።
፭ ሀስርዓቶቼን እስካከበረ ድረስ፣ በህይወት እያለ፣ የመንግስቱ የሚስጥራት ለቁልፎችም ከአገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ፣ በመሰረትኩበት መንገድ፣ አይወሰድበትም።
፮ በከንቱ በእርሱ ላይ ምክንያት የሚፈልጉበት አሉ፤
፯ ይሁን እንጂ፣ እርሱም ኃጢአትን ሰርቷል፤ ነገር ግን፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ኃጢአታቸውን በፊቴ የሚናዘዙ፣ እና ሀይቅርታን የሚጠይቁ፣ ለለሞት ኃጢአትን ላልሰሩት፣ እኔ ጌታ ሐይቅርታ አደርግላቸዋለሁ።
፰ ደቀ መዛሙርቶቼ፣ በቀደሙት ቀናት፣ እርስ በርሳቸው ሀምክንያት ይፈልጉ ነበር እና በልቦቻቸውም ይቅርታን አያደርጉም ነበር፤ እናም በዚህ ክፉ ነገርም ተሰቃይተው እናም በምሬት ለተቀጥተው ነበር።
፱ ስለዚህ፣ እርስ በርሳችሁ ሀይቅርታን መስጠት አለባችሁ እላችኋለሁ፤ ወንድሙ ለተላለፈው ለይቅርታን የማይሰጠው በጌታ ፊት ይኮነናል፤ ምክንያቱም በእርሱ ታላቁ ኃጢአት ይኖራልና።
፲ እኔ ጌታ ሀይቅር የምለውን ይቅር እላለሁ፣ ነገር ግን እናንተ ለሁሉም ሰዎች ለይቅርታን ታደርጉ ዘንድ ይጠበቅባችኋል።
፲፩ እና በልባችሁም እንዲህ ማለት ይገባችኋል—በእኔ እና በአንተ መካከል እግዚአብሔር ሀይፍረድ፣ እናም ለእንደስራህም ይከፍልሀልና።
፲፪ እናም ለኃጢአቶቹ ንስሀ ያልገባውም፣ እና ያልተናዘዘውንም፣ ሀበቤተክርስቲያኗ ፊት አምጡት፣ እናም በቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ በትእዛዝም ሆነ በራዕይ እንደሚላችሁም እንዲሁ አድርጉበት።
፲፫ እናም ይህንንም የምታደርጉት ለእግዚአብሔር ክብር ነው፣ ይቅርታ ስላላደረጋችሁ፣ ወይም ርህራሄ ስለሌላችሁ ሳይሆን፣ ነገር ግን በህግ ፊት ይህንኑ ለማረጋገጥ፣ ህግን የሰጣችሁን እንዳታስቀይሙ ነው—
፲፬ እውነት እላለሁ፣ በእነዚህ ምክንያቶች እነዚህን ነገሮች አድርጉ።
፲፭ እነሆ፣ እኔ ጌታ አገልጋዬ በነበረው ኤዝራ ቡዝ፣ እና ደግሞም በአገልጋዬ አይዛክ ሞርሊ ተቆጥቻለሁ፣ ምክንያቱም ህግንም ይሁን ትእዛዝን አላከበሩምና።
፲፮ በልቦቻቸው ክፋትን ፈልገዋል፣ እናም እኔ ጌታ መንፈሴን ከእነርሱ አርቄአለሁ። ክፉት የሌለባቸውን ነገሮች እንደክፉ ሀኮንነዋልና፤ ይሁን እንጂ፣ አገልጋዬን አይዛክ ሞርሊን ይቅር ብዬዋለሁ።
፲፯ እና ደግሞም አገልጋዬ ሀኤድዋርድ ፓርትሪጅ፣ እነሆ፣ ኃጢአትን ሰርቷል፣ እናም ለሰይጣንም ነፍሱን ሊያጠፋ ይሻል ነገር ግን፣ እነዚህን ነገሮች ሲያውቋቸው፣ እናም ለክፋታቸው ንስሀ ሲገቡ፣ ይቅርም ይሰጣቸዋል።
፲፰ እናም አሁን፣ እውነትም እላለሁ፣ አገልጋዬ ስድኒ ጊልበርት፣ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ወደ ሀላፊነቱ፣ እና በፅዮን ምድር ወዳለው ወኪሉ፣ ይመለስ ዘንድ ፍቃዴ ነው፤
፲፱ እናም፣ እንዳይጠፉም፣ ያያቸውን እና የሰማቸውን ነገሮች ደቀ መዛሙርቴ እንዲያውቋቸው ያደርጋል። እናም በእዚህም ምክንያት እነዚህን ነገሮች ተናግሬአለሁና።
፳ እና እንዲህም እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ አይዛክ ሞርሊ ለመሸከም ከሚችለው በላይ ሀእንዳይፈተን፣ እናም ሊጎዳችሁም የስህተት ምክር እንዳይሰጥም፣ የእርሻ ቦታው ይሸጥ ዘንድ አዘዝኩኝ።
፳፩ አገልጋዬ ፍሬድሪክ ጂ ዊልያምስ የእርሻ ቦታውን መሸጡ የእኔ ፈቃድ አይደለም፣ እኔ ጌታ፣ ኃጢአተኞችን በማልጥልበት አምስት አመት ጊዜያት፣ በዚህም የተወሰኑትን አድን ዘንድ፣ በከርትላንድ ምድር የምሽግ ስፍራን ለመጠበቅ እፈልጋለሁና።
፳፪ እናም ከዚያ ቀን በኋላ፣ እኔ ጌታ ወደ ፅዮን ምድር በተከፈተ ልብ የሚሄደውን ማንንም እንደ ሀጥፋተኛ አልቆጥርም፤ እኔ ጌታ የሰው ልጆችን ለልብ እሻለሁና።
፳፫ እነሆ፣ አሁን እስከ ሰው ልጅ ሀምፅዓት ድረስ ቀኑም ለዛሬ ተብሎ ይጠራል፣ እናም እውነትም ሐየመስዋዕት ቀን ነው፣ እናም ህዝቤ አስራትን የሚከፍሉበትም ቀን ነው፤ መአስራትን የሚከፍልም በእርሱ ምፅዓት ጊዜ ሠአይቃጠልም።
፳፬ ከዛሬ በኋላ እንደ ምድጃ እሳት ሀየሚነድ ቀን ይመጣልና—ይህም እንደ ጌታ አባባል ነው—እውነትም እላለሁ፣ ለትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፤ እናም አቃጥላቸዋለሁ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነኝና፤ እናም ሐበባቢሎን ውስጥ የሚቀሩትንም አላድንም።
፳፭ ስለዚህ፣ ካመናችሁኝ፣ ዛሬ ተብሎ በሚጠራው ቀን ትሰራላችሁ።
፳፮ እናም አገልጋዬ ሀኒወል ኬ ውትኒ እና ስድኒ ጊልበርት በዚህ ያላቸውን ንብረት እና ለግምጃዎቻቸውን መሸጣቸው አስፈላጊ አይደለም፤ በዚህ ስፍራ ቤተክርስቲያን የሚቀሩት ወደ ፅዮን ምድር ከመሄዳቸው በፊት ይህም ጥበብ አይደለምና።
፳፯ እነሆ፣ በህግጋቴ ውስጥ በጠላታችሁ ዘንድ ሀእዳ አትግቡ ይላል፣ ወይም የተከለከለ ነው፤
፳፰ ነገር ግን እነሆ፣ በሚያስደስተው ጊዜ ጌታ አይወስድም፣ እናም መልካም በመሰለውም ይከፍላል አልተባለም።
፳፱ ስለዚህ፣ እናንት ወኪል ስለሆናችሁ፣ በጌታ መልእክት ትጓዛላችሁ፤ እናም እንደ ጌታ ፈቃድ በኩል የምታደርጉት ነገር ሁሉ የጌታ ስራ ነውና።
፴ እናም በእነዚህም የመጨረሻ ቀናት ለቅዱሳኑ፣ በፅዮን ምድር ሀውርስን እንዲያገኙ ታደርጉ ዘንድ ተሹማችኋል።
፴፩ እናም እነሆ፣ ሀቃላቴ እርግጥ በመሆናቸውና ለስለማይወድቁ፣ እነርሱም እንደሚያገኟቸው እኔ ጌታ እገልፅላችኋለሁ።
፴፪ ነገር ግን ሁሉም ነገሮች በጊዜአቸው ይከናወኑ ዘንድ ግድ ነው።
፴፫ ስለዚህ፣ መልካም ሥራን ትሰሩ ዘንድ ሀአትታክቱ፣ የታላቅ ስራን መሰረት እየገነባችሁ ነውና። እናም ለከትትንሽ ነገሮች ታላቅ ነገሮች ይወጣሉና።
፴፬ እነሆ፣ ጌታ ሀልብን እና መልካም ፈቃድ ያለውን አዕምሮ ለይሻል፤ እናም ፈቃድ ያለው እና ሐታዛዡ የሆነው እርሱ በእነዚህ በመጨረሻዎቹ ቀናት የፅዮንን ምድርን በረከት ይበላሉ።
፴፭ እናም ሀአመጸኞችም ከፅዮን ምድር ለይቆረጣሉ፣ እናም ተለይተው ይሄዳሉ፣ እናም ምድሩንም አይወርሱም።
፴፮ በእውነት እላለሁ፣ አመጸኞቹ ሀከኤፍሬም ወገን አይደሉም፣ ስለዚህም ይነቀላሉ።
፴፯ እነሆ፣ እኔ ጌታ በእነዚህ በመጨረሻዎቹ ቀናት ቤተክርስቲያኔን በኮረብታ ላይ እንደተቀመጠ ዳኛ በአህዛብ ትፈርድ ዘንድ እንድትቀመጥ ሰርቻታለሁ።
፴፰ እንዲህም ይሆናል የፅዮን ኗሪዎች ፅዮንን በሚመለከቱ ነገሮችን ላይ ሀበፍርድ ይቀመጣሉ።
፴፱ እናም ሐሰተኞች እና ግብዞች በእነርሱ ይፈተናሉ፣ እናም ሀሐዋርያት እና ነቢያት ያልሆኑትም ይታወቃሉ።
፵ እናም ሀዳኛ የሆነው ለኤጲስ ቆጶስ እና አማካሪዎቹም፣ ሐበሀላፊነታቸው ታማኝ ካልሆኑ፣ ይኮነናሉ፣ እናም መሌሎችም በእነርሱ ስፍራ ይተከላሉ።
፵፩ እነሆ፣ እንዲህ እላችኋለሁ ሀፅዮን ታብባለች፣ እናም የጌታም ለክብር በእርሷ ላይ ያርፋል፤
፵፪ እናም እርሷም ለህዝብ ሀምልክት ሆና ትቆማለች፣ እናም ከሰማይ በታች ካሉት ሀገሮች ውስጥም ወደ እርሷ ይመጣሉ።
፵፫ እናም በእርሷ ምክንያት የአለም ሀገሮች ሁሉ ሀየሚንቀጠቀጡበት፣ እናም በአስፈሪዎቿም ምክንያት የሚደነግጡበት ቀን ይመጣል። ጌታም ይህን ተናግሯል። አሜን።