ክፍል ፶፱
በነሀሴ ፯፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) በጃክሰን የግዛት ክፍል ሚዙሪ፣ በፅዮን ውስጥ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ከዚህ ራዕዩ በፊትም፣ ህዝቡ በዚያን ጊዜ ስለተሰበሰቡበት የፅዮን መሬት ነቢዩ በግልፅ ጻፈ። ምድሩም ጌታ እንዳዘዘው ተቀድሶ ነበር፣ እናም ወደፊት ቤተመቅደስ የሚሰራበት ስፍራም ተመርቆ ነበር። ይህ ራዕይ በተቀበለበት ቀን፣ የጆሴፍ ናይት ቀዳማዊ ባለቤት ፖሊ ናይት ሞተች፣ እርሷም በ ፅዮን የሞተች የመጀመሪያ የቤተክርስቲያኗ አባል ነበረች። የመጀመሪያ አባላት ይህን ራዕይ “ቅዱሳን ሰንበትን የሚጠብቁበት እና እንዴት እንደሚጾሙና እንደሚጸልዩ የሚያስተምር” ነው ብለው ይናገሩበት ነበር።
፩–፬፣ በፅዮን ውስጥ የሚገኙት ታማኝ ቅዱሳን ይባረካሉ፤ ፭–፰፣ ጌታን በማፍቀር እና በማገልገል ትእዛዛቱን ያክብሩ፤ ፱–፲፱፣ የጌታን ቀን ቅዱስ አድርጎ በመጠበቅ፣ ቅዱሳን በስጋ እና በመንፈስ ተባርከዋል፤ ፳–፳፬፣ ጻድቃኑም በዚህ አለም ሰላም እና በሚመጣው አለም ዘለአለማዊ ህይወት ቃል ተገብቶላቸዋል።
፩ እነሆ፣ ጌታም እንዲህ ይላል፣ እንዳዘዝኳቸው ሙሉ ሀአይናቸውን ወደ ክብሬ አድርገው ወደዚህ አገር የመጡት የተባረኩ ናቸው።
፪ በህይወት ያሉት ምድርን ሀይወርሳሉ፣ እና ለየሞቱትም ከሁሉም ድካሞቻቸው ያርፋሉ፣ እናም ስራዎቻቸው ይከተሏቸዋል፤ እናም ባዘጋጀሁላቸው በአባቴም ሐቤቶች ውስጥ መአክሊልን ይቀበላሉ።
፫ አዎን፣ ወንጌሌን በማክበር በፅዮን ምድር ላይ እግሮቻቸውን ያሳረፉትም የተባረኩ ናቸው፤ ምክንያቱም፤ የምድር መልካም ነገሮች የእነርሱ ደመወዛቸው ይሆናልና፣ እና ምድርም ሀበጥንካሬዋ መልካምን ውጤት ታመጣለች።
፬ ከላይ በሚመጡም በረከቶችም፣ አዎን፣ እናም በፊቴ ሀታማኝ እና ለትጉሆች ለሆኑትም፣ ጥቂት ባልሆኑ ትእዛዛት፣ እናም በጊዜአቸውም ሐራዕይና አክሊልን ይቀበላሉ።
፭ ስለዚህ፣ እንዲህ በማለት ትእዛዛትን እሰጣቸዋለሁ፥ ጌታ አምላክህን በፍጹም ሀልብህ፣ በሙሉ ሀይልህ፣ አዕምሮህ፣ እና ጉልበትህ ለውደድ፤ እናም በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም ሐአገልግለው።
፮ ሀባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ። ለአትስረቅ፤ ወይም ሐአታመንዝር፣ ወይም መአትግደል፣ ወይም እንደዚህ አይነት ነገሮችን አታድርግ።
፯ ጌታ አምላክህን በሁሉም ነገሮች ሀአመስግን።
፰ የተሰበረ ልብን እና ሀየተዋረደ መንፈስን ለመስዋዕት አድርገህ ለጌታ አምላካህ ሐበፅድቅ አቅርብ።
፱ ከአለም ነገሮች ራስህን ንጹህ እና ሀነውር የሌለበት ለማድረግ ወደ ጸሎት ቤት ሂድ፣ እናም ለበቅዱስ ቀኔም ቅዱስ ስርዓቶችህን አቅርብ፤
፲ በእውነት ከስራህ እንድታርፍ እናም ለልዑልም አምልኮህን ሀእንድትሰጥ ይህ ቀን ተሰጥቶሀልና፤
፲፩ ነገር ግን፣ በሁሉም ቀናት እና በሁሉም ጊዜያት ስእለትህም በፅድቅ ይቅረብ።
፲፪ በዚህ በጌታ ቀን ግን፣ በወንድሞችህ እና በጌታህ ፊት ኃጢአትህን ሀበመናዘዝ፣ መስዋዕትህን እና ቅዱስ ለቁርባንህን ለልዑልህ ለማቅርብ አስታውስ።
፲፫ ሀጾምህ ፍጹም እንዲሆን፣ ወይም በሌላ ቃል ለደስታህ እንዲሞላ፣ ምግብህን በአንድ ልብ ከማዘጋጀት በቀር በዚህ ቀን ሌላ ምንም ነገር አታድርግ።
፲፬ በእውነት፣ ይህ ጾም እና ጸሎት፣ ወይም በሌላ ቃል፣ መደሰት እና መጸለይ ነው።
፲፭ እነዚህን ነገሮች ሀበምስጋና፣ እና በፈቃደኛ ልብ እና ፊት፣ እናም ኃጢአትም ስለሆነ በብዙ ለመሳሳቅ ሳይሆን ሐበደስተኛ መልብና ፊት ካደረግህ—
፲፮ በእውነት እላለሁ፣ ይህን ነገር ካላደረግህ፣ የምድር ሙላት፣ እንዲሁም የዱር አራዊቶች እና የሰማይ አዕዋፋት፣ እናም በዛፍ ላይ የሚወጡት እና በምድር የሚራመዱ ሁሉ የአንተ ይሆናሉ፤
፲፯ አዎን፣ ቅጠላ ቅጠሎች፣ እናም ለምግብ ይሁን ለልብስ፣ ወይም ለቤትም፣ ወይም ለጋጣ፣ ወይም የመዝናኛ ስፍራዎች፣ ወይም ለአትክልት ስፍራ፣ ወይም ለወይን ስፍራም፣ የሚሆኑትን ከምድር የሚመጡት መልካም ነገሮች ሁሉ የአንተ ይሆናሉ፤
፲፰ አዎን፣ በጊዜአቸው ሀበምድር ላይ የሚያድጉት ነገሮች የተፈጠሩት ለሰው ጥቅም፣ አይንን እና ልብን ለማስደሰት ነውና፤
፲፱ አዎን፣ ለምግብ እና ለልብስ፣ ለጣዕም እና ሽታ፣ ሰውነትን ለማጠንከር እና ነፍስንም ለማደስ የተፈጠረ ነው።
፳ እናም እነዚህን ነገሮች ሁሉ ለሰው ስለሰጠ እግዚአብሔርን ያስደስተዋል፤ በብልጫ ወይም በግድ ሳይሆን፣ በጥበብ እንደዚህ እንዲጠቀሙባቸው ነውና የተፈጠሩት።
፳፩ በሁሉም ነገሮች ውስጥ የእርሱ እጅ እንዳለበት ሀካለመመስከር እና ትእዛዙን ካለማክበር በቀር፣ በምንም መንገድ ሰው እግዚአብሔርን ለአያስቀይመውም፣ ወይም በማንም ላይ ቁጣው አይቀጣጠልም።
፳፪ እነሆ፣ ይህም በህግ እና በነብያቱ መሰረት ነው፤ በዚህም ጉዳይ ደግማችሁ አትነትርኩኝ።
፳፫ ነገር ግን ሀየፅድቅን ስራ የሚሰራው ለደመወዙን፣ እንዲሁም በዚህ አለም ሐሰላም፣ እና በሚመጣው አለምም መዘለአለማዊ ህይወትን ይቀበላል።
፳፬ እኔ ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ፣ እና መንፈስም ይመሰክራል። አሜን።