ምዕራፍ ፭
[ሰኔ–ጥቅምት ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.)]
አዳምና ሔዋን ልጆችን ወለዱ—አዳም መሥዋዕት አቀረበ፣ እግዚአብሔርንም አገለገለ—ቃየንና አቤል ተወለዱ—ቃየን አመጸ፣ ሰይጣንንም ከእግዚአብሔር በላይ ወደደ፣ እናም የጥፋት ልጅ ሆነ—ገዳይነትና ክፉነት ተስፋፋ—ወንጌሉም ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ የተሰበከ ነው።
፩ እንዲህም ሆነ እኔ እግዚአብሔር አምላክ እነርሱን ካስወጣኋቸው በኋላ አዳም መሬቱን ማረስ ጀመረ፣ እና በዱር እንስሣቱም ላይ ሀስልጣን ነበረው፣ እናም እኔ ጌታ እንዳዘዝኩት እንጀራውን በፊቱ ወዝ በላ። እናም ሚስቱ ሔዋንም ከእርሱ ጋር አብራው ሰራች።
፪ አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፣ እርሷም ወንድና ሀሴት ልጆችን ለወለደች፣ እና እነርሱም በምድር ላይ ሐበዙም ተባዙም።
፫ እናም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የአዳም ወንድና ሀሴት ልጆች ሁለት በሁለት በምድር ላይ ተከፋፈሉ፣ እናም መሬቱን ማረስ፣ መንጋዎችን መጠበቅ፣ እናም ወንድና ሴት ልጆችን መውለድ ጀመሩ።
፬ አዳምና ሚስቱ ሔዋን የጌታን ስም ጠሩ፣ እናም ሀከዔድን ገነት አካባቢም የጌታን ድምጽ እያናገራቸው ሰሙ፣ እና አላዩትም ነበር፤ ከእርሱ ለፊት ተዘግተው ነበርና።
፭ እግዚአብሔር አምላካቸውን ሀእንዲያመልኩ፣ እናም ከመንጋዎቻቸው መካከል ለበመጀመሪያ የተወለደውን ለጌታ መሥዋዕት እንዲያቀርቡም ትእዛዛትን ሰጣቸው። እና አዳምም ለእግዚአብሔር ትእዛዛት ሐታዛዥ ነበር።
፮ ከብዙ ቀናት በኋለ የአምላክ ሀመልአክ ወደ አዳም መጥቶ እንዲህ አለው፥ ለጌታ ለመሥዋዕት ለምን ታቀርባለህ? አዳምም እንዲህ አለው፥ እግዚአብሔር ስላዘዘኝ እንጂ፣ ለምን እንደሆነ አላውቅም።
፯ ከዚያም መልአኩ እንዲህ ብሎ ተናገረ፣ ይህ ነገር ሀበጸጋና በእውነት የተሞላው የአብ አንድያ ልጅ ለመስዋዕት ሐአምሳል ነው።
፰ ስለዚህ፣ የምታደርጋቸውን ነገሮች በሙሉ በወልድ ሀስም አድርግ፣ እና ለንስሀ ግባ እና በወልድም ስም እግዚአብሔርን ለዘለአለም ሐጥራ።
፱ እናም በእዚያ ቀን ስለአብና ወልድ የሚመሰክረው ሀመንፈስ ቅዱስ አዳም ላይ በማረፍ እንዲህ አለ፥ እኔ ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ እናም እስከዘለአለም ድረስ የአብ ለአንድያ ልጅ ነኝ፣ እንደ ሐወደቅህም አንተና ፍላጎት ያላቸው የሰው ዘሮች ሁሉ መለመዳን ይችላሉ።
፲ በዚያም ቀን አዳም እግዚአብሔርን ባረከ እናም ሀተሞላ፣ እና በምድር ላይ ስላሉት ቤተሰቦች ሁሉ እንዲህ ብሎ ለመተንበይ ጀመረ፥ የእግዚአብሔር ስም ይባረክ፣ በጥፋቴ ምክንያት አይኖቼ ተከፈተዋልና፣ እና በዚህ ህይወትም ሐደስታ ይኖረኛል፣ እንደገና መበስጋዬም እግዚአብሔርን አያለሁ።
፲፩ እና ሚስቱ ሀሔዋንም እነዚህን ነገሮች በሙሉ ሰማች እና በደስታ እንዲህ አለች፥ ባናጠፋ ኖሮ ለዘርም አይኖረንም ነበር፣ እና መልካምና ክፉን፣ እናም የመዳንን ደስታ፣ እናም ለታዛዡ ሁሉ እግዚአብሔር የሚሰጠውን ዘለአለማዊ ህይወትን አናውቅም ነበር።
፲፪ እና አዳምና ሔዋን የእግዚአብሔርን ስም ባረኩ፣ እና ሁሉንም ነገሮች ለሴቶችና ለወንዶች ልጆቻቸው ሀአሳወቁ።
፲፫ እናም ሀሰይጣን ከመካከላቸው መጥቶ እንዲህ አለ፣ እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፣ እናም እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፥ ይህን አትመኑ፤ እና ይህንንም ለአላመኑም፣ እና ሰይጣንን ከእግዚአብሔር በላይ ሐወደዱ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሰዎችም መስጋዊ፣ ስሜትዊና ዲያብሎሳዊ መሆን ጀመሩ።
፲፬ እና እግዚአብሔር አምላክም በሁሉም ስፍራ ሰዎችን ሀበመንፈስ ቅዱስ ጠራቸውና ንስሀ እንዲገቡም አዘዛቸው።
፲፭ በወልድ ሀያመኑትና ለኃጢአታቸው ንስሀ የገቡት ሁሉ ለይድናሉ፤ እናም የማያምኑትና ንስሀ የማይገቡት ሁሉ ሐይፈረድባቸዋል፤ እና በፅኑ ትእዛዝም ቃላት ከእግዚአብሔር አንደበት ሄዱ፤ ስለዚህ መሟላት አለባቸው።
፲፮ እና አዳምና ሚስቱ ሔዋን የእግዚአብሔርን ስም መጥራት አላቆሙም። አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፣ ሀቃየንንም ወለደች። እርስዋም ወንድን ከእግዚአብሔር አገኘሁ፤ ስለዚህ እርሱም ቃላቶቹን የማይቃወም ይሆናል አለች። ነገር ግን እነሆ፣ ቃየን እንዲህም በማለት አላደመጠም፥ ጌታ ማን ነው ማወቅ የሚያስፈልገኝ?
፲፯ ደግማም ፀንሳ ወንድሙን ሀአቤልን ወለደች። እና አቤልም የእግዚአብሔርን ድምፅ ለአደመጠ። አቤልም በግ ጠባቂ ነበር፣ ነገር ግን ቃየን ምድርን የሚያርስ ነበረ።
፲፰ እና ቃየን ሰይጣንን ከእግዚአብሔር በላይ ሀወደደ። እና ሰይጣን እንዲህ በማለት አዘዘው፥ ለጌታ መስዋዕት ለአቅርብ።
፲፱ እናም ከጊዜም በኋላ እንዲህ ሆነ ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቀረበ።
፳ እና አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኵራትና ከስቡ አቀረበ። እና እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ ሀመስዋዕቱ ተመለከተ፤
፳፩ ነገር ግን ወደቃየንና ወደ ሀመሥዋዕቱ አልተመለከተም። አሁን ሰይጣን ይህን አወቀ፣ እና ይህም አስደስተው። እና ቃየን እጅግ ተናደደ፣ ፊቱም ጠቆረ።
፳፪ እናም እግዚአብሔር ለቃየን እንዲህ አለው፥ ለምን ተናደድህ? ለምንስ ፊትህ ጠቆረ?
፳፫ መልካም ብታደርግ፣ ሀተቀባይ ትሆናለህ። እና መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች፣ እና ሰይጣንም ይፈልግሀል፤ እና ትእዛዛቴን ካላደመጥህ በስተቀር፣ አሳልፌ እሰጥሀለሁ፣ እና በአንተም ላይ እንደ ፈቃዱ ይሆንብሀል። አንተም ገዢው ትሆናለህ።
፳፬ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሀሰት አባት ትሆናለህ፤ ሀጥፋት ተብለህም ትጠራለህ፤ ከአለም በፊት ነበርክና።
፳፭ ወደፊት በሚመጣውም ጊዜ እንዲህ ይባላል—እነዚህ ሀጸያፎች ከቃየን የመጡ ናቸው፤ ከእግዚአብሔር የመጣውን ታላቅ ምክር አስወግዷልና፤ እና ንስሀ ካልገባህ በስተቀር፣ ይህ በአንተ ላይ የማደርግብህ እርግማን ነው።
፳፮ እናም ቃየንም በጣም ተናደደ፣ እና የአምላክንና በጌታ ፊት በቅድስና የሚሄደው ወንድሙ የአቤልን ድምጽም ከዚህ በኋላ አላደመጠም።
፳፯ እናም አዳምና ሚስቱ በቃየንና በወንድሞቹ ምክንያት በጌታ ፊት አለቀሱ።
፳፰ እና እንዲህ ሆነ ቃየንም ከወንድሞቹ ሴት ልጆች አንዷን አገባ፣ እና ሰይጣንን ከእግዚአብሔር በላይ ሀወደዱ።
፳፱ እና ሰይጣን ለቃየን እንዲህ አለው፥ በጉሮሮህ ማልልኝ፣ እናም ይህን ከነገርህ በእርግጥ ትሞታለህ፤ እና ወንድሞችህ እንዳይናገሩት በጭንቅላታቸውና በህያው እግዚአብሔር እንዲምሉ አድረግ፤ ይህን ከነገሩም በእርግጥ ይሞታሉና፤ እናም ይህም አባትህ እንዳያውቀው ነው፤ እናም በዚህ ቀን አቤል ወንድምህን በእጅህ ላይ እሰጥሀለሁ።
፴ እና ሰይጣንም እንደ ትእዛዙ እንደሚያደርግም ለቃየን ማለለት። እና እነዚህ ነገሮች ሁሉ የተደረጉት በሚስጥር ነበር።
፴፩ እናም ቃየን አለ፥ በእውነት እኔ ሀበመግደል ትርፍ አገኝ ዘንድ፣ በእርግጥም የዚህ ታላቅ ሚስጥር ጌታ ማኸን ነኝ። ስለዚህ ቃየንም ጌታ ለማኸን ተብሎ ተጠራ፣ እናም በጥፋቱም ከበረ።
፴፪ እናም ቃየን ወደ ሜዳ ወጣ፣ እናም ቃየን ከወንድሙ አቤል ጋር ተነጋገረ። እናም እንዲህ ሆነ በሜዳው ላይ እያሉ፣ በሜዳም ሳሉ ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፣ ገደለውም።
፴፫ እና ባደረገውም ሀክብር ተሰምቶት እንዲህ አለ፥ ነጻ ነኝ፣ በእርገጥም የወንድሜ መንጋዎች በእጆቼ ወደቁ።
፴፬ እግዚአብሔርም ቃየንን አለው፥ ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? እርሱም አለ፥ አላውቅም፤ የወንድሜ ሀጠባቂው እኔ ነኝን?
፴፭ ጌታም እንዲህ አለ፤ ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮሃል።
፴፮ አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች ምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ።
፴፯ ምድርንም ባረስህ ጊዜ እንግዲህ ኃይልዋን አትሰጥህም፤ በምድርም ላይ ሀኰብላይና ተቅበዝባዥ ትሆናለህ።
፴፰ ቃየንም እግዚአብሔርን አለው፥ ሰይጣን በወንድሜ መንጋዎች ምክንያት ሀፈተነኝ። ደግሞም ተናድጄ ነበር፤ አንተም የእኔን ሳይሆን የእርሱን መስዋዕት ተቀብለህ ነበርና፤ ቅጣቴም ልሸከማት የማልችላት ታላቅ ናት።
፴፱ እነሆ ዛሬ ከጌታ ፊት አሳደድኸኝ፤ ከፊትህም እሰወራለሁ፤ በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ እሆናለሁ፤ እንዲህ ይሆናል የሚያገኘኝም ሁሉ በጥፋቴ ምክንያት ይገድለኛል፣ እነዚህ ነገሮች ከአምላክ ሊሸሸጉ አይችሉምና።
፵ እኔ ጌታም እንዲህ አልኩት፥ የገደለህ ሁሉ ሰባት እጥፍ ይበቀልበታል። እና እኔ ጌታም ያገኙት ሁሉ እንዳይገድሉት፣ በቃየን ላይ ሀምልክት አደረግሁለት።
፵፩ እናም ቃየንም ከእግዚአብሔር ሀፊት ወጥቶ ሄደ፣ እናም ከሚስቱና ከብዙ ወንድሞቹ ጋር ከዔደን በስተምስራቅ በምትገኘው በኖድ ምድር ተቀመጠ።
፵፪ ቃየንም ሚስቱን አወቀ፤ ፀነሰችም፣ ሔኖህንም ወለደች፣ እናም እርሱም ብዙ ወንድና ሴት ልጆችን ወለደ። ሀከተማም ሠራ፣ የከተማይቱንም ስም በልጁ ስም ሔኖህ አላት።
፵፫ ሄኖሕም ጋይዳድን ወለደ፤ እናም ሌሎች ወንድና ሴት ልጆች ወለደ። ጋይዳድም ሜኤልን ወለደ፣ እና ሌሎች ወንድና ሴት ልጆችን ወለደ። እናም ሜኤልም ማቱሳላን ወለደ፣ እናም ሌሎች ወንድና ሴት ልጆች ወልደ። እናም ማቱሳላም ላሜህን ወለደ።
፵፬ ላሜሕም ለራሱ ሁለት ሚስቶችን አገባ፤ የአንዲቱ ስም ዓዳ፣ የሁለተኛይቱ ስም ሴላ ነበረ።
፵፭ ዓዳም ያባልን ወለደች፤ እርሱም በድንኳን የሚቀመጡት የዘላኖች አባት ነበረ፤ የወንድሙም ስም ዩባል ነበረ፤ እርሱም በገናንና መለከትን ለሚይዙ አባት ነበረ።
፵፮ ሴላም ደግሞ ከናስና ከብረት የሚቀጠቀጥ ዕቃን የሚሠራውን ቱባል ቃየንን ወለደች። የቱባልቃይንም እኅት ናዕማ ነበረች።
፵፯ ላሜሕም ለሚስቶቹ ለዓዳና ለሴላ አላቸው፥ እናንት የላሜሕ ሚስቶች ቃሌን ስሙ፣ ነገሬንም አድምጡ፤ እኔ ጕልማሳውን ለቍስሌ፣ ብላቴናውንም ለመወጋቴ ገድዬዋለሁና።
፵፰ ቃየንን ሰባት እጥፍ ይበቀሉታል፣ በእውነትም ላሜሕን ግን ሀሰባ ሰባት እጥፍ ይበቀሉታል፤
፵፱ ላሜህ እንደ ቃየን ከሰይጣን ጋር ሀቃል ኪዳን ገብቶ ሰይጣን ለቃየን ለሰጠው ታላቅ ሚስጥር ጌታ በመሆን ጌታ ማኸን ሆኖአልና፤ እናም የሔኖክ ልጅ ጋይዳድም የእነርሱን ሚስጥር በማወቁ፣ ለአዳም ልጆች ይህን መግለፅ ጀመረ፤
፶ ስለዚህ ቃየን ወንድሙን አቤልን ሃብት ለማግኘት እንዳደረገው ሳይሆን፣ ላሜሕ በቃለ መሀላው ምክንያት ተናዶ ነበር የገደለው።
፶፩ ከቃየን ቀናት ጀምሮ፣ ሀየሚስጥር ሴራ ነበር፣ ስራቸውም በጭለማ ውስጥ ነበር፣ እና እያንዳንዱም ወንድሙን ያውቅ ነበር።
፶፪ ስለዚህ እግዚአብሔርም ላሜሕን፣ ቤቱን፣ እናም ከሰይጣን ጋር ቃል የገቡትን ሁሉ ረገማቸው፤ ትእዛዛትን አላከበሩምና፣ ይህም እግዚአብሔርን አላስደሰተውም፣ እነርሱንም አላገለገላቸውም፣ እና ስራቸውም ጸያፎች ነበሩ፣ እና በሰዎች ሀወንድ ልጆች ሁሉ መካከልም መሰራጨት ጀመረ። እና ይህም በሰዎች ልጆች መካከል ነበር።
፶፫ እናም ላሜህ ለሚስቶቹ ሚስጥሩን ስለነገራቸው፣ እና ስለአመጹበትና ለሌሎችም ስለነገሩበት፣ እና ርህራሄ ስላልነበራቸው፣ ከሰዎች ሴት ልጆች መካከል እነዚህን ነገሮች አይነጋገሩባቸውም።
፶፬ ስለዚህ ላሜህ ተጠልቶ ነበር፣ እና አስወጡትም፣ እና እንዳይሞትም፣ ከሰዎች ልጆች መካከል አይመጣም ነበር።
፶፭ እንደዚህም ሀየጭለማ ስራዎች በሰው ልጆች ሁሉ መካከል መሳካት ጀመሩ።
፶፮ እግዚአብሔርም ምድርን በከባድ እርግማን ረገማት፣ እና በመጥፎዎችም፣ በፈጠራቸው የሰዎች ልጆች ሁሉ ተናድዶ ነበር፤
፶፯ እነርሱም ድምጹን አያደምጡም፣ ወይም አለም ከመፈጠሯ በፊት ተዘጋጅቶ የነበረው፣ በመካከለኛው ዘመን ይመጣል ብሎ በተገለጠላቸው ሀበአንድያ ልጅ አያምኑም ነበርና።
፶፰ እንደዚህም ሀወንጌሉ ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ ከእግዚአብሔር ፊት በተላኩት በቅዱስ ለመላእክት፣ እና በድምጹ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ሐስጦታ በመገለፅ ይሰበክ ጀመር።
፶፱ እንደዚህም ሁሉም ነገሮች በቅዱስ ስርአቶች ለአዳም ተረጋግጠውለታል፣ እና ወንጌልም ተሰብኳል፣ እናም በአለም ውስጥ ይሆን ዘንድ ታውጇል፤ እናም እንደዚህም ነበር። አሜን።