ምዕራፍ ፰
[የካቲት ፲፰፴፩ (እ.አ.አ.)]
ማቱሳላ ተነበየ—ኖህና ልጆቹ ወንጌልን ሰበኩ—ታላቅ ጥፋት በዛ—ወደ ንስሀ መጠራትም አልተሰማም—እግዚአብሔርም ሰጋዎችን በሙሉ በጥፋት ውሀ ለማጥፋት አወጀ።
፩ ሄኖክም የኖረበት ቀናት ሁሉ አራት መቶ ሰላሳ ዓመት ነበሩ።
፪ እንዲህም ሆነ የሔኖክ ልጅ ሀማቱሳላም የጌታ ቃል ኪዳን ይሟላ ዘንድ አልተወሰደም ነበር፤ በእውነትም ኖህ የወገቡ ፍሬ እንደሚሆን ቃል ገብቶለት ነበርና።
፫ እንዲህም ሆነ ማቱሳላም ከወገቡ (በኖህ በኩል) የአለም መንግስታት ሁሉ እንደሚመጡም ተነበየ፣ እና በራሱም ላይ ክብርን ወሰደ።
፬ እና በምድር ላይ ታላቅ ርሀብ መጣ፣ እና ጌታም ምድርን በታላቅ ርግማን ረገመው፣ እና በዚያም ብዙ ኗሪዎቹም ሞቱ።
፭ እንዲህም ሆነ ማቱሳላም መቶ ሰማንያ ሰባት ዓመት ኖረ፣ ላሜሕንም ወለደ፤
፮ ማቱሳላም ላሜሕን ከወለደ በኋላ የኖረው ሰባት መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤
፯ ማቱሳላም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ዘጠኝ ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
፰ ላሜሕም መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ኖረ፣ ልጅንም ወለደ፣
፱ ስሙንም እግዚአብሔር ሀበረገማት ምድር ከተግባራችንና ከእጅ ሥራችን ይህ ያሳርፈናል ሲል ለኖኅ ብሎ ጠራው።
፲ ላሜሕም ኖኅን ከወለደ በኋላ የኖረው አምስት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ።
፲፩ ላሜሕ የኖረበት ዘመን ሁሉ ሰባት መቶ ሰባ ሰባት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
፲፪ ኖህም በአራት መቶ ሀምሳ አመቱ ያፌትን ሀወለደ፤ እና ከአርባ ሁለት አመት በኋላ ለሴምን ከያፌት እናት ወለደ፣ እናም በአምስት መቶ አመቱም ሐካምንን ወለደ።
፲፫ ሀኖህና ልጆቹም ጌታን ለአደመጡ፣ እና ምክሩንም ተቀበሉ፣ እና የእግዚአብሐርም ሐልጆች ተብለው ተጠሩ።
፲፬ እነዚህ ወንዶች በምድር ገፅ ላይ እየተባዙ ሄዱ፣ እና ሴት ልጆችም ለእነርሱ ተወለዱላቸው፣ የሰው ሀወንዶችም እነዚህ ሴት ልጆች ቆንጆ እንደሆኑ አዩ፣ እና እንደፍላጎታቸውም እነዚህን ሚስቶቻቸው አደረጓቸው።
፲፭ ጌታም ለኖህ እንዲህ አለው፥ የወንድ ልጆችህ ሴት ልጆች ራሳቸውን ሀሸጠዋል፤ እነሆ፣ ቁጣዬ በሰው ልጆች ላይ ተቀጣጥላለች፣ ድምጼን አያደምጡምና።
፲፮ እንዲህም ሆነ ኖህም ተነበየ፣ እናም የእግዚአብሔርን ነገሮች፣ እንዲሁም በመጀመሪያው እንደነበረው፣ አስተማረ።
፲፯ ጌታም ለኖህ እንዲህ አለው፥ መንፈሴ ከሰው ጋር ሁልጊዜም ሀአይቆይም፣ እርሱ ሁሉም ለስጋ መሞት እንዳለበት ያውቃልና፤ ነገር ግን እድሜው አንድ መቶ ሀያ ይሆናል፤ እና ሰዎች ንስሀ ካልገቡ፣ ሐጎርፉን እልክባቸዋለሁ።
፲፰ በዚያም ቀናት ሀግዙፍ ሰዎች በምድር ላይ ነበሩ፣ እና ኖህን ለመግደልም ፈለጉ፤ ነገር ግን ጌታ ከኖህ ጋር ነበር፣ እና የጌታ ለሀይልም እርሱ ላይ አርፎ ነበር።
፲፱ ጌታ ሀበስርዓቱም ለኖኅን ሐሾመው፣ እና፣ ለሔኖክ እንደተሰጠው፣ ወደ ሰው ልጆች እንዲሄድ እና ወንጌሉን መእንዲሰብክ አዘዘው።
፳ እንዲህም ሆነ ኖህ የሰው ልጆች ሀንስሀ እንዲገቡ ጠራቸው፤ ነገር ግን የእርሱን ቃላትን አላደመጡም።
፳፩ ደግሞም፣ ከሰሙትም በኋላ፣ ወደ ፊቱ መጥተው እንዲህ አሉ፥ እነሆ፣ እኛ የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ የሰውን ሴት ልጆች ለራሳችን አልወሰድንም? እና ሀእየበላን እየጠጣን፣ እና እያገባንና በጋብቻ እየሠጠን አይደለንምን? ሚስቶቻችንም ልጆችን ወልደውልናል፣ እና እነዚህም እንደ ቀደሙት ሰዎች የታወቁ ጠንካራ ሰዎች ናቸው። እና የኖህን ቃላት አላደመጡም።
፳፪ እግዚአብሔርም የሰዎች ሀጥፋት በምድር ላይ የበዛ እንደሆነ አየ፤ እና የእያንዳንዱ ሰው የልቡ ለሀሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ ሆነ።
፳፫ እንዲህም ሆነ፣ ኖህም ለህዝቡ ሀመስበክን እንዲህ በማለት ቀጠለ፥ አድምጡ፣ እና የቃላቶቼን ምክር ተቀበሉ፤
፳፬ እንደ አባቶቻችሁም ሀእመኑ ለኃጢአታችሁም ንስሀ ግቡ እና በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለተጠመቁ፣ እና ሁሉንም ነገሮችን ሐይገለፅላችሁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ትችላላችሁ፤ እና ይህን ካላደረጋችሁ፣ የጥፋት ውሀ ይመጣባችኋል፤ ይህም ቢሆንም አላደመጡትም።
፳፭ ኖህም በዚህ ተጸጸተ፣ እናም በምድር ላይ እግዚአብሔር ሰውን በመፍጠሩ ልቡ ተጨነቀ፣ እና ይህም ልቡን እጅግ አሳዘነው።
፳፮ ጌታም እንዲህ አለ፥ የፈጠርሁትን የሰው፣ ሰውና እንስሣት፣ ተንቀሳቃሾች ፍጡራን እስከ ሰማይ ወፎች፣ ከምድር ገፅ ሀአጠፋለሁ፣ ስለፈጠርኳቸው እና ስለሰራኋቸው ኖህ ተጸጽቷልና፤ እና ህይወቱን ለማጥፋትም ስለሚፈልጉ እኔን ጠርቶኛል።
፳፯ እንዲሁም ኖህ በጌታ አይኖች ውስጥ ሀፀጋን አገኘ፤ በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ ለፍጹምና ከበደል የራቀ ሰው ነበር፤ እና ሶስቱ ልጆቹ ሴም፣ ካምንና ያፌት እንዳደረጉት፣ ሐአካሄዱንም ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ።
፳፰ ምድርም በእግዚአብሔር ፊት በክፉ ሥራ ሀረከሰች፣ እናም በአመጽም ተሞልታለች።
፳፱ እግዚአብሔር ምድርን ተመለከተ፣ እና እነሆ ረክሳ ሁሉም ስጋዎች ለባሽ አካሄዱን በምድር ላይ አበላሽቶ ነበርና።
፴ እግዚአብሔርም ኖህን እንዲህ አለው፥ የስጋ ለባሽ ሁሉ መጨረሻ በፊቴ መጥቷል፣ ምድርም በአመፅ ተሞልታለችና፣ እናም እነሆ ስጋን ሁሉ ከምድር ውስጥ ሀአጠፋለሁ።