ክፍል ፻፴፫
በህዳር ፫፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) በሀይረም ኦሀዮ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ይህን ራዕይ በማስተዋወቅ የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ እንደሚገልጸው፥ “በዚህ ጊዜ ሽማግሌዎች ወንጌሉን ለምድር ነዋሪዎች ስለመስበክ፣ እና መሰብሰብን በሚመለከት ብዙ ነገሮችን ለማወቅ ፈልገው ነበር፤ እና በእውነት ብርሀን ለመራመድ፣ እና ከበላይም ለመመራት፣ በህዳር ፫፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ ጌታን ጠየቅሁ እና ይህን አስፈላጊ ራዕይ ተቀበልኩ።” ይህም ክፍል በትምህርት እና ቃል ኪዳን መፅሐፍ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ተጨማሪ ሆኖ ነበር እና በኋላም የክፍል ቁጥር ተመደበለት።
፩–፮፣ ቅዱሳን ለዳግም ምፅዓት እንዲዘጋጁ ታዝዘዋል፤ ፯–፲፮፣ ሁሉም ሰዎች ከባቢሎን እንዲሸሹ፣ ወደ ፅዮን እንዲመጡ፣ እና ለጌታም ታላቅ ቀን እንዲዘጋጁ ታዝዘዋል፤ ፲፯–፴፭፣ እርሱ በፅዮን ተራራ ላይ ይቆማል፣ ክፍለ አህጉራትም አንድ ምድር ይሆናሉ፣ እና የጠፉት የእስራኤል ነገዶች ይመለሳሉ፤ ፴፮–፵፣ ወንጌሉ በአለም እንዲሰበክ በጆሴፍ ስሚዝ በኩል ዳግሞ ተመልሷል፤ ፵፩–፶፩፣ ጌታ በክፉዎች ላይ ለበቀል ይወርዳል፤ ፶፪–፶፮፣ የቤዛነቱም አመት ይሆናል፤ ፶፯–፸፬፣ ወንጌል ቅዱሳንን ለማዳን እና ክፉዎችንም ያጠፉ ዘንድ ተልኳል።
፩ የቤተክርስቲያኔ ህዝብ ሆይ፣ አድምጡ፣ ይላል ጌታ አምላ ካችሁ፣ እና እናንተን በሚመለከት የጌታን ቃል ስሙ—
፪ ወደ ሀቤተመቅደሱ በድንገት የሚመጣው ጌታ፤ አዎን፣ እግዚአብሔርን በእርሱ ህዝብ ላይ፣ እና በመካከላችሁ ላሉ ኃጢአተኞች ላይ ሁሉ ለለፍርድ እርግማን ይዞ በምድር ላይ የሚወርደው ጌታን አድምጡ።
፫ እግዚአብሔር የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ሀይገልጣልና፣ እና በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካቸውን ለመድኃኒት ያያሉ።
፬ ስለዚህ ህዝቤ ሆይ፣ ተዘጋጁ፣ ተዘጋጁ፤ ራሳችሁን ቀድሱ፤ የቤተክርስቲያኔ ህዝብ ሆይ፣ እንድትቆዩ ያልታዘዛችሁት ሁሉ አብራችሁ በፅዮን ምድር ውስጥ ተሰብሰቡ።
፭ ሀከባቢሎንም ውጡ። የጌታን ዕቃ የምትሸከሙ ለንፁሀን ሁኑ።
፮ የክብር ስብሰባችሁን ጥሩ፣ እና አንዳችሁ ከሌላችሁ በየጊዜው ሀተነጋገሩ። እና እያንዳንዱም ሰው የጌታን ስም ይጥራ።
፯ አዎን፣ ደግሞም እውነት እላችኋለሁ፣ የጌታ ድምፅ ለእናንተ የሚሆንበት ጊዜ መጥቷል፥ ከባቢሎን ውጡ፤ ሀከአራቱ ነፋሳት፣ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከሀገሮች መካከል ለተሰብስባችሁ ውጡ።
፰ መጀመሪያ ወደ ሀአህዛብ እና ከዚያም ወደ ለአይሁድ፣ ሁሉንም ሀገሮች እንዲጠሯቸው የቤተክርስቲያኔን ሽማግሌዎች ወደ ራቅ ሀገሮች፣ ወደ ባህር ሐደሴቶች መላኳቸው፤ ወደ ባዕድ ሀገሮችም ላኳቸው።
፱ እናም እነሆ እና አስተውሉ፣ ይህም ጩኸታቸው እና ለሁሉም ህዝብ የጌታ ድምፅ ነው፥ የህዝቤ ድንበር ይሰፋ ዘንድ፣ እና ሀካስማዎቿም ይጠናከሩ ዘንድ፣ እና ፅዮንም በአካባቢው ባሉ ሀገራት ትጎለብት ዘንድ ወደ ለፅዮን ምድር ሂዱ።
፲ አዎን፣ ከሁሉም ህዝብ መካከል ጩኸቱ ይውጣ፥ ንቁ፣ እና ተነሱ እና ሙሽራውንም ለመገናኘት ሂዱ፤ እነሆ እና አስተውሉ፣ ሀሙሽራው ይመጣል፣ ትቀበሉትም ዘንድ ውጡ። ለጌታ ለታላቅ ቀንም ራሳችሁን አዘጋጁ።
፲፩ ቀኒቱንና ሰዓቲቱን ሀአታውቁምና እንግዲህ ለንቁ።
፲፪ ከአህዛብ ሀመካከል ያሉትም ወደ ለፅዮን ይሽሹ።
፲፫ እና ሀየይሁዳ የሆኑትም ወደጌታ ለቤት ሐተራራዎች ወደ መኢየሩሳሌም ይሽሹ።
፲፬ ከሀገሮች መካከል፣ እንዲሁም ከባቢሎን፣ መንፈሳዊ ባቢሎን ከሆነው ከክፋት መካከል ውጡ።
፲፭ ነገር ግን በእውነት ጌታ እንዲህ ይላል፣ ሽሸታችሁ ሀበችኮላ አይሁን፣ ነገር ግን ሁሉም ነገሮች በፊታችሁ ይዘጋጁ፤ እና የሚሄደውም፣ ድንገተኛ ጥፋትም እንዳይደርስበት ወደኋላ ለአይመልከት።
፲፮ የምድር ነዋሪዎች ሁሉ፣ ሀአድምጡ እና ስሙ። የቤተክርስቲያኔ ሽማግሌዎች የሆናችሁ በአንድነት አብራችሁ አድምጡ፣ እና የጌታንም ድምፅ ስሙ፤ ሁሉንም ሰዎች ይጣራልና፣ እና በየትኛውም ስፍራ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ለንስሀ ይገቡ ዘንድያዝዛቸዋል።
፲፯ እነሆም፣ ጌታ አምላክ በሰማያት መካከል እንዲህ በማለት በመጮህ መልአክ ሀልኳል፥ የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ እና ጥርጊያውንም ለቀና አድርጉ፣ ሐየመምጣቱም ጊዜ ቀርቦአልና—
፲፰ ሀበጉ ለበፅዮን ተራራ ሲቆም፣ እና ከእርሱም ጋር የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው ሐመቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።
፲፱ ስለዚህ፣ ሀለሙሽራው ለምጻት ተዘጋጁ፤ ሂዱ፣ ከእርሱም ጋር ለመገናኘት ሂዱ።
፳ እነሆም፣ በደብረ ዘይት ተራራና በታላቋ ባህር ላይ፣ እንዲሁም በታላቁ ጥልቅ፣ እና በባህር ደሴት ላይ፣ እና በፅዮን ምድር ላይ ሀይቆማል።
፳፩ እና ሀበፅዮንም ሆኖ ድምፁን ለከፍ አድርጎ ይጮኻል፣ እና ከኢየሩሳሌምም ይናገራል፣ እና ድምጹም በሁሉም ህዝብ መካከል ይሰማል፤
፳፪ ይህም ተራሮችን ሀበሚሰብር፣ እና ሸለቆዎችን እንደሚለያይ በሚያደርግ እንደ ብዙ ውሀዎች ለድምፅና እንደ ታላቅ ሐነጐድጓድ ድምፅ ይሰማል።
፳፫ ታላቁን ጥልቅ ያዝዘዋል፣ እና ይህም ወደ ሰሜን አገሮችም ይገፋል፣ እና ሀደሴቶችም አንድ ምድር ይሆናሉ፤
፳፬ እና ሀየኢየሩሳሌም ምድር እና የፅዮን ምድር ወደስፍራቸው ይመለሳሉ፣ እና ምድርም ለከመከፋፈልዋ ቀን አስቀድሞ እንደነበረችበትም አይነት ትሆናለች።
፳፭ እና ጌታ፣ እንዲሁም አዳኝ፣ በህዝቡ መካከል ይቆማል፣ እና ስጋ ለባሽ ሁሉ መካከል ሀይነግሳል።
፳፮ እና ሀበሰሜን ሀገሮች ያሉትም ጌታን ያስታውሳሉ፤ እና ነቢያቶቻቸውም ድምጹን ይሰማሉ፣ እና ራሳቸውን ከዚህም በኋላ የሚታገሱ አይሆኑም፤ እና ድንጋይን ይመታሉ፣ እና በፊታቸውም በረዶዎች ይፈሳሉ።
፳፯ እና ሀአውራ መንገድም በታላቁ ጥልቅ መካከል ይዘረጋል።
፳፰ ጠላቶቻቸውም ለእነርሱ እንደ አደን ይሆናሉ፣
፳፱ እና ፍሬ በማያፈራ ሀበረሀ ውስጥም የህይወት ውሀ ምንጭ ይፈልቃል፤ እና በጸሀይ የደረቀውም መሬት ዳግም የተጠማ ምድር አይሆንም።
፴ እና የከበረ ሀብታቸውንም ወደ አገልጋዬ ሀኤፍሬም ልጆች ያመጣሉ።
፴፩ እና የዘለአለም ሀኮረብቶች ድንበሮችም በፊታቸው ይንቀጠቀጣሉ።
፴፪ እና በዚያ፣ እንዲሁም በፅዮን ውስጥ፣ ይወድቃሉ እና በጌታ አገልጋዮች እጆችም፣ እንዲሁም በኤፍሬም ልጆች፣ የክብር አክሊል ይጎነጸፋሉ።
፴፫ እና እነርሱም በዘለአለም የደስታ ሀመዝሙር ይሞላሉ።
፴፬ እነሆ፣ ይህም በእስራኤል ሀጎሳዎች ላይ የዘለአለማዊው እግዚአብሔር በረከት፣ እና ለበኤፍሬም እና በባልንጀሮቹ ራስ ላይ ዋጋ ያለው በረከት ነው።
፴፭ እና ሀየይሁዳ ጎሳ ለሆኑትም፣ ከስቃያቸው በኋላ ለበቅድስና በጌታ ፊት፣ በቀን እና በማታ፣ ለዘለአለም፣ በፊቱ እንዲኖሩ ይቀደሳሉ።
፴፮ አሁንም፣ በእውነት ጌታ እንዲህ ይላል፣ የምድር ነዋሪዎች ሆይ፣ እነዚህ ነገሮች በእናንተ መካከል የታወቁ ይሆኑ ዘንድ የዘለአለም ሀወንጌል ያለው፣ ለአንዳንዶች የታየ እና ለሰውም ይህን የሰጠ፣ እና በምድር ላይ ለሚኖሩት ለብዙዎች የሚታየው ለመልአክ ከሰማይ መካከል እንዲበር ልኬአለሁ።
፴፯ እና ይህም ሀወንጌል ለለእያንዳንዱ ሕዝብ፣ ለነገድ፣ ቋንቋ፣ እና ወገንም ሁሉ ሐይሰበካል።
፴፰ እና የእግዚአብሔርም አገልጋዮች በታላቅ ድምፅ፥ የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት በማለት ይሄዳሉ፤
፴፱ እና ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውኃንም ምንጮች ለሠራው ሀስገዱለት—
፵ በቀን እና በማታ የጌታን ስም በመጥራት፥ ሰማያትን ሀቀድደህ ብትወርድስ፣ ተራሮችም በፊትህ ቢናወጡስ በማለትም።
፵፩ እናም በራሳቸው ላይ መልስ ይሰጣል፤ የጌታ መገኘት እሳት እንደሚያቀልጥ እሳት፣ እና ውኃንም ሀእንደሚያፈላ እሳት ይሆናል።
፵፪ ጌታ ሆይ፣ ስምህ ለጠላቶችህ ይገለጥ ዘንድ፣ እና አሕዛብም በፊትህ ይንቀጠቀጡ ዘንድ ትወርዳለህ—
፵፫ ያልጠበቁትን የሚያስፈራውን ነገር ባደረግህም ጊዜ፤
፵፬ አዎን፣ ወረድህ፣ እና ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ፣ የሚደሰተውንና ጽድቅን የሚያደርገውን በመንገዶችህም የሚያስቡህን ሀትገናኛቸዋለህ።
፵፭ እግዚአብሔር ሆይ፣ ሰዎች ከጥንት ጀምሮ ሀለሚጠብቁህ ለከምትሠራላቸው ከአንተ በቀር ሌላ አምላክን አልሰሙም፣ በጆሮአቸውም አልተቀበሉም፣ ዓይንም አላየችም።
፵፮ እና እንዲህም ይባላል፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ የወረደው፣ ልብሱም የቀላ፣ ከባሶራ ሀየሚመጣ አለባበሱም ያማረ፣ በጕልበቱስ ጽናት የሚራመድ ይህ ለማን ነው?
፵፯ እርሱም ይላል፥ በጽድቅ የምናገር ለማዳንም የምበረታ እኔ ነኝ።
፵፰ እና ጌታም በልብሱ ሀቀይ፣ እና ልብሱም ወይን በመጥመቂያ እንደሚረግጥ ሰው ልብስ ይሆናል።
፵፱ እና ከፊቱም ክብር ታላቅነት የተነሳ ሀጸሀይ በእፍረት ፊቱን ይሸፍናል፣ እና ጨረቃም ብርሀኗን ትከለክላለች፣ እና ከዋክብትም ከስፍራቸው ይወረወራሉ።
፶ እና ድምጹም ይሰማል፥ ወይን መጭመቂያን ብቻዬን ሀረግጫለሁ፥ እና በሁሉም ህዝብ ላይ ፍርድ አምጥቻለሁ፤ እና ማንም ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤
፶፩ በቍጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፣ ደማቸውም በልብሴ ላይ ሀተረጭቶአል፣ ልብሴንም ሁሉ አሣድፌአለሁ፤ ይህም በልቤ የነበረው የምበቀልበት ቀን ነውና።
፶፪ አሁንም የምቤዥበትም ዓመት ደርሶአል፤ እና የጌታቸውን አፍቃሪ ደግነትን እና በመልካምነቱም መሰረት፣ እናም በአፍቃሪ ደግነቱ መሰረት፣ በእነርሱ ላይ ስላፈሰሰው ሁሉ ለዘለአለም ይናገራሉ።
፶፫ ሀበጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ። የፊቱን መልአክ አዳናቸው፤ ለበፍቅሩና በርኅራኄውም ሐተቤዣቸው፣ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው፤
፶፬ አዎን፣ እና ሀሔኖክ ደግሞም፣ እና ከእርሱም ጋር የነበሩት፤ ከእርሱ በፊት የነበሩት ነቢያት፤ እና ለኖህም ደግሞ፣ እና ከእርሱም በፊት የነበሩት፤ እና ሐሙሴም፣ እና ከእርሱ በፊት የነበሩት፤
፶፭ ከሙሴ እስከ ኤልያስ፣ እና ከኤልያስ ሀበትንሳኤው ከክርስቶስ ጋር እስከ ነበረው ዮሐንስ፣ እና ቅዱስ ሐዋርያት፣ ከአብርሐም፣ ይስሀቅ፣ እና ያዕቆብ ጋር በበጉ ፊት ይሆናሉ።
፶፮ ሀየቅዱሳን ለመቃብሮችም ሐይከፈታሉ፤ እና መበፅዮን ተራራ ላይ፣ እና በቅዱስቲቱ ከተማ ሠአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ላይ ሲቆምም፣ እነርሱም ይመጣሉ እና በበጉም ረቀኝ ይቆማሉ፤ እና በቀን እና በማታ ለዘለአለም ሰየበጉን ሸመዝሙሮች ይዘምራሉ።
፶፯ እና ለዚህም ምክንያት ሰዎች የሚገለጡትን ሀክብሮች ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ፣ ጌታ ለየወንጌሉን ሙላት፣ ዘለአለማዊ ቃልኪዳኑን፣ በግልጽ እና በቀላል ምክንያቱን ላከ—
፶፰ በምድር ላይ ለሚመጡት ነገሮች ሀደካማዎችን ለማዘጋጀት፣ እና ጥበበኞችን በሚያሳፍሩበት ቀን ለጌታ መልእክት፣ እና ለአነስተኛው ብርቱ ሕዝብ ይሆናል፣ እና ሐሁለቱ አሥሩን ሺህ ያሸሻሉ።
፶፱ እና በመንፈሱ ኃይል ጌታ በአለም ደካማ ነገሮች አህዛብን ሀይወቃል።
፷ እና ለዚህም ምክንያት እነዚህ ትእዛዛት ተሰጥተው ነበር፤ በተሰጧቸውም ቀን ከአለም ይሰውሯቸው ዘንድ ታዝዛው ነበር፣ ነገር ግን አሁን ወደ ሁሉም ሀስጋ ለባሾች ለይሂዱ—
፷፩ እና ይህም ሁሉንም ስጋ ለባሽ በሚገዛው በጌታ አዕምሮ እና ፈቃድ መሰረት ነው።
፷፪ እና ሀንስሀ ለሚገባው እና በጌታ ፊት ራሱን ለለሚቀድስም ሐየዘለአለም ህይወትን ይሰጣል።
፷፫ እና የጌታን ድምፅ ሀለማያደምጡም፣ ከህዝብ መካከል ለይቆረጡ ዘንድ፣ በነቢዩ ሙሴ የተጻፈውም ይፈጸማል።
፷፬ እና በነቢዩ ሀሚልክያስ እንደተጻፈውም፥ እነሆ፣ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ለቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፤ የሚመጣውም ቀን ሐያቃጥላቸዋልና፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
፷፭ ስለዚህ፣ ይህም ለእነርሱ የጌታ መልስ ይሆናል፥
፷፮ በዚያም ቀን ወደ ራሴ ስመጣ፣ በመካከላችሁ ማንም ሀአልተቀበለኝም፣ እና ተሰድዳችሁም ነበር።
፷፯ በጠራሁስ ጊዜ የሚመልስ ማንም አልነበረም፤ ነገር ግን መታደግ እንዳልችል ሀእጄ አጭር አልሆነችም፣ ወይስ ለማዳን ለኃይል የለኝም።
፷፰ እነሆ፣ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን ሀአደርቃለሁ። ወንዞችንም ምድረበዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ዓሦቻቸውም ይገማሉ በጥማትም ይሞታሉ።
፷፱ ሰማያትን ጥቍረት አለብሳቸዋለሁ፥ መጋረጃቸውንም ማቅ አደርጋለሁ።
፸ እና ሀይህ ከእጄ ይሆንባችኋል—በኀዘን ትተኛላችሁ።
፸፩ እነሆ እና አስተውሉ፣ የሚያድናችሁ ማንም የለም፤ ከሰማያት ስጠራችሁ ድምጼን አልታዘዛችሁበትምና፤ በአገልጋዮቼ አላመናችሁም፣ እና ወደ እናንተም ሀሲላኩ አልተቀበሏቸውም።
፸፪ ስለዚህ፣ ምስክሩን ሀያትማሉ እና ህግንም ያስራሉ፣ እና ወደ ድቅድቅ ጭለማም ትጣላላችሁ።
፸፫ እነዚህም በድቅድቅ ጨለማ ይሄዳሉ፣ በዚያ ሀልቅሶ፣ ሀዘንና፣ ጥርስ ማፏጨት ይሆናል።
፸፬ እነሆ ጌታ አምላካችሁ ይህን ተናግሯል። አሜን።