ክፍል ፷፮
ጥቅምት ፳፱፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በሂራም ኦሀዮ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ውልያም ኢ መክለለን ለነበሩት አምስት ጥያቄዎች መልስ በነቢዩ በኩል በሚስጥር እንዲመልስለት ጌታን ጠይቆ ነበር፣ እነዚህም ለጆሴፍ ስሚዝ የታወቁ አልነበሩም። በመክለለን ጥያቄ፣ ነቢዩ ጌታን ጠየቀ እና ይህን ራዕይ ተቀበለ።
፩–፬፣ የወንጌሉ ሙሉነት ዘለአለማዊው ቃል ኪዳን ነው፤ ፭–፰፣ ሽማግሌዎች ይስበኩ፣ ይመስክሩ፣ እናም ከህዝብም ጋር ይወያዩ፤ ፱–፲፫፣ ታማኝ የወንጌል አገልግሎትም የዘለአለም ህይወትን ውርስ ያረጋግጣል።
፩ እነሆ፣ ጌታ ለአገልጋዬ ውልያም መክለለን እንዲህ ይላል—ከኃጢአቶችህ ዞር እስካልህ ድረስ፣ እና እውነቴን እስከተቀበልህ ድረስ የተባርክ ነህ፣ እንዲሁም በስሜ ሀየሚያምኑት ሁሉ፣ ይላል ጌታ ቤዛህ፣ የአለም አዳኝ።
፪ እውነት እልሀለሁ፣ ሀዘለአለማዊ ቃል ኪዳኔን፣ እንዲሁም በነቢያት እና ሐዋርያት በቀደሙት ቀናት እንደተጻፈው፣ ለህይወት እንዲኖራቸው እና በመጨረሻዎቹም ቀናት የሚገለጡትን ክብሮች ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ፣ ወደሰው ልጆች የተላከውን የወንጌሌን ሙሉነት በመቀበልህ የተባረክህ ነህ።
፫ በእውነትም እልሀለሁ፣ አገልጋዬ ውልያም ሆይ፣ አንተ፣ በሁሉም ባይሆን፣ ንጹህ ነህ፤ ስለዚህ በፊቴ ለማያስደስቱኝ ነገሮች ንስሀ ግባ፣ ጌታ እነዚህን ሀያሳይሀልና።
፬ እናም አሁን፣ በእውነትም፣ እኔ ጌታ ስለአንተ በመመልከት ያለኝን ፈቃዴን፣ ወይም አንተን በተመልከተ ፈቃዴን አሳይህ ዘንድ እሻለሁ።
፭ እነሆ፣ በእውነትም እልሀለሁ፣ ከስፍራ ወደ ስፍራ፣ እና ከከተማ ወደ ከተማ፣ አዎን፣ ባልታወጁበት አካባቢዎች ውስጥ ሁሉ ወንጌሌን ሀታውጅ ዘንድ ፍቃዴ ነው።
፮ በዚህ ስፍራ ለብዙ ቀናት አትቆይ፤ ወደ ፅዮን አገርም ገና አትሂድ፣ ነገር ግን፣ ለመላክ የምትችለውን ላክ፤ አለበለዚያም፣ ስለ ንብረቶችህ አታስብ።
፯ ወደ ምስራቅ ባሉ ምድሮችም ሀተጓዝ፣ በእያንዳንዱም ስፍራዎች፣ ለእያንዳንዱም ሰው እናም በየምኩራቦቻቸው፣ ከህዝብ ጋር እየተወያየህ፣ ለምስክርነትህን ስጥ።
፰ አገልጋዬ ሳሙኤል ኤች ስሚዝም አብሮህ ይሂድ፣ እናም አትተወው፣ እናም አስተምረውም፤ እናም ታማኝ የሆነውም እርሱ በሁሉም ስፍራ ሀጠንካራ ይሆናል፤ እና እኔ ጌታም ከአንተ ጋር እሄዳለሁ።
፱ በታመሙትም ላይ ሀእጆችህን ጫን፣ ለይድኑማል። እኔ ጌታ እስከምልክህ ድረስም አትመለስ። በስቃይህም ትእግስተኛ ሁን። ሐለምን፣ እናም ይሰጥሀል፤ አንኳኳ፣ ይከፈትልህማል።
፲ ብኩንነትን አትሻ። ከፅድቅ ያልሆኑውን ሁሉ ተው። የተፈተንህበትን ሀአመንዝራትን አትፈጽም።
፲፩ እነዚህ ያዘዝኩህን ሀጠብቅ፣ እውነት እና ታማኝ ናቸውና፤ እናም ሀላፊነትህን ታጎላለህ፣ እናም የዘለአለም ደስታ ለመዝሙሮች በራሳቸው ላይ ሆኖ ብዙ ህዝብን ወደ ሐፅዮን ትገፋለህ።
፲፪ እስከመጨረሻውም በእነዚህ ነገሮች ሀፅና፣ እናም በጸጋ እና በእውነት በተሞላው በአባቴም ቀኝ በኩልም የዘለአለም ህይወት ለአክሊል ይኖርሀል።
፲፫ በእውነትም፣ እንዲህ ይላል ጌታ ሀእግዚአብሔርህ፣ ቤዛህ፣ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ። አሜን።