ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፶፱


ክፍል ፶፱

በነሀሴ ፯፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) በጃክሰን የግዛት ክፍል ሚዙሪ፣ በፅዮን ውስጥ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ከዚህ ራዕዩ በፊትም፣ ህዝቡ በዚያን ጊዜ ስለተሰበሰቡበት የፅዮን መሬት ነቢዩ በግልፅ ጻፈ። ምድሩም ጌታ እንዳዘዘው ተቀድሶ ነበር፣ እናም ወደፊት ቤተመቅደስ የሚሰራበት ስፍራም ተመርቆ ነበር። ይህ ራዕይ በተቀበለበት ቀን፣ የጆሴፍ ናይት ቀዳማዊ ባለቤት ፖሊ ናይት ሞተች፣ እርሷም በ ፅዮን የሞተች የመጀመሪያ የቤተክርስቲያኗ አባል ነበረች። የመጀመሪያ አባላት ይህን ራዕይ “ቅዱሳን ሰንበትን የሚጠብቁበት እና እንዴት እንደሚጾሙና እንደሚጸልዩ የሚያስተምር” ነው ብለው ይናገሩበት ነበር።

፩–፬፣ በፅዮን ውስጥ የሚገኙት ታማኝ ቅዱሳን ይባረካሉ፤ ፭–፰፣ ጌታን በማፍቀር እና በማገልገል ትእዛዛቱን ያክብሩ፤ ፱–፲፱፣ የጌታን ቀን ቅዱስ አድርጎ በመጠበቅ፣ ቅዱሳን በስጋ እና በመንፈስ ተባርከዋል፤ ፳–፳፬፣ ጻድቃኑም በዚህ አለም ሰላም እና በሚመጣው አለም ዘለአለማዊ ህይወት ቃል ተገብቶላቸዋል።

እነሆ፣ ጌታም እንዲህ ይላል፣ እንዳዘዝኳቸው ሙሉ አይናቸውን ወደ ክብሬ አድርገው ወደዚህ አገር የመጡት የተባረኩ ናቸው።

በህይወት ያሉት ምድርን ይወርሳሉ፣ እና የሞቱትም ከሁሉም ድካሞቻቸው ያርፋሉ፣ እናም ስራዎቻቸው ይከተሏቸዋል፤ እናም ባዘጋጀሁላቸው በአባቴም ቤቶች ውስጥ አክሊልን ይቀበላሉ።

አዎን፣ ወንጌሌን በማክበር በፅዮን ምድር ላይ እግሮቻቸውን ያሳረፉትም የተባረኩ ናቸው፤ ምክንያቱም፤ የምድር መልካም ነገሮች የእነርሱ ደመወዛቸው ይሆናልና፣ እና ምድርም በጥንካሬዋ መልካምን ውጤት ታመጣለች።

ከላይ በሚመጡም በረከቶችም፣ አዎን፣ እናም በፊቴ ታማኝ እና ትጉሆች ለሆኑትም፣ ጥቂት ባልሆኑ ትእዛዛት፣ እናም በጊዜአቸውም ራዕይና አክሊልን ይቀበላሉ።

ስለዚህ፣ እንዲህ በማለት ትእዛዛትን እሰጣቸዋለሁ፥ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በሙሉ ሀይልህ፣ አዕምሮህ፣ እና ጉልበትህ ውደድ፤ እናም በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም አገልግለው

ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ። አትስረቅ፤ ወይም አታመንዝር፣ ወይም አትግደል፣ ወይም እንደዚህ አይነት ነገሮችን አታድርግ።

ጌታ አምላክህን በሁሉም ነገሮች አመስግን

የተሰበረ ልብን እና የተዋረደ መንፈስን መስዋዕት አድርገህ ለጌታ አምላካህ በፅድቅ አቅርብ።

ከአለም ነገሮች ራስህን ንጹህ እና ነውር የሌለበት ለማድረግ ወደ ጸሎት ቤት ሂድ፣ እናም በቅዱስ ቀኔም ቅዱስ ስርዓቶችህን አቅርብ፤

በእውነት ከስራህ እንድታርፍ እናም ለልዑልም አምልኮህን እንድትሰጥ ይህ ቀን ተሰጥቶሀልና፤

፲፩ ነገር ግን፣ በሁሉም ቀናት እና በሁሉም ጊዜያት ስእለትህም በፅድቅ ይቅረብ።

፲፪ በዚህ በጌታ ቀን ግን፣ በወንድሞችህ እና በጌታህ ፊት ኃጢአትህን በመናዘዝ፣ መስዋዕትህን እና ቅዱስ ቁርባንህን ለልዑልህ ለማቅርብ አስታውስ።

፲፫ ጾምህ ፍጹም እንዲሆን፣ ወይም በሌላ ቃል ደስታህ እንዲሞላ፣ ምግብህን በአንድ ልብ ከማዘጋጀት በቀር በዚህ ቀን ሌላ ምንም ነገር አታድርግ።

፲፬ በእውነት፣ ይህ ጾም እና ጸሎት፣ ወይም በሌላ ቃል፣ መደሰት እና መጸለይ ነው።

፲፭ እነዚህን ነገሮች በምስጋና፣ እና በፈቃደኛ ልብ እና ፊት፣ እናም ኃጢአትም ስለሆነ በብዙ መሳሳቅ ሳይሆን በደስተኛ ልብና ፊት ካደረግህ—

፲፮ በእውነት እላለሁ፣ ይህን ነገር ካላደረግህ፣ የምድር ሙላት፣ እንዲሁም የዱር አራዊቶች እና የሰማይ አዕዋፋት፣ እናም በዛፍ ላይ የሚወጡት እና በምድር የሚራመዱ ሁሉ የአንተ ይሆናሉ፤

፲፯ አዎን፣ ቅጠላ ቅጠሎች፣ እናም ለምግብ ይሁን ለልብስ፣ ወይም ለቤትም፣ ወይም ለጋጣ፣ ወይም የመዝናኛ ስፍራዎች፣ ወይም ለአትክልት ስፍራ፣ ወይም ለወይን ስፍራም፣ የሚሆኑትን ከምድር የሚመጡት መልካም ነገሮች ሁሉ የአንተ ይሆናሉ፤

፲፰ አዎን፣ በጊዜአቸው በምድር ላይ የሚያድጉት ነገሮች የተፈጠሩት ለሰው ጥቅም፣ አይንን እና ልብን ለማስደሰት ነውና፤

፲፱ አዎን፣ ለምግብ እና ለልብስ፣ ለጣዕም እና ሽታ፣ ሰውነትን ለማጠንከር እና ነፍስንም ለማደስ የተፈጠረ ነው።

እናም እነዚህን ነገሮች ሁሉ ለሰው ስለሰጠ እግዚአብሔርን ያስደስተዋል፤ በብልጫ ወይም በግድ ሳይሆን፣ በጥበብ እንደዚህ እንዲጠቀሙባቸው ነውና የተፈጠሩት።

፳፩ በሁሉም ነገሮች ውስጥ የእርሱ እጅ እንዳለበት ካለመመስከር እና ትእዛዙን ካለማክበር በቀር፣ በምንም መንገድ ሰው እግዚአብሔርን አያስቀይመውም፣ ወይም በማንም ላይ ቁጣው አይቀጣጠልም።

፳፪ እነሆ፣ ይህም በህግ እና በነብያቱ መሰረት ነው፤ በዚህም ጉዳይ ደግማችሁ አትነትርኩኝ።

፳፫ ነገር ግን የፅድቅን ስራ የሚሰራው ደመወዙን፣ እንዲሁም በዚህ አለም ሰላም፣ እና በሚመጣው አለምም ዘለአለማዊ ህይወትን ይቀበላል።

፳፬ እኔ ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ፣ እና መንፈስም ይመሰክራል። አሜን።