ክፍል ፴፰
ጥር ፪፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) በፈየት፣ ኒው ዮርክ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት የተሰጠ ራዕይ። ወቅቱ የቤተክርስቲያን ጉባዔ የሚካሄድበት ነበር።
፩–፮፣ ክርስቶስ ሁሉን ነገሮች ፈጠረ፤ ፯–፰፣ እርሱም በቅርብ በሚያዩት በቅዱሳኑ መካከል ነው፤ ፱–፲፪፣ ሁሉም ስጋ በእርሱ ፊት በስባሽ ነው፤ ፲፫–፳፪፣ ለጊዜአዊ እና ለዘለአለም የሚሆን የቃል ኪዳን ምድርን ለጻድቃኖቹ አስቀምጧል፤ ፳፫–፳፯፣ ቅዱሳን አንድ እንዲሆኑ እና እርስ በራሳቸው እንደ ወንድም እንዲተያዩ ታዘዋል፤ ፳፰–፳፱፣ የጦርነቶች ትንቢቶች ተነግረዋል፤ ፴–፴፫፣ ቅዱሳን ከላይ ስልጣን ይሰጣቸዋል እናም በሁሉም ህዞቦች መካከልም ይሄዳሉ፤ ፴፬–፵፪፣ ቤተክርስቲያኗ ድሆችን እና የተቸገሩን እንድትንከባከብ እና ዘለአለማዊ ሀብትን እንድሻ ታዛለች።
፩ ጌታ አምላካቹ፣ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ታላቁ ሀእኔ ነኝ፣ አልፋ እና ኦሜጋ፣ ለየመጀመሪያው እና የመጨረሻው፣ አለም ከመፈጠሩ ሐአስቀድሞ መበከፍታና በተቀደሰ ስፍራ ዘለአለማዊነትን እና ሁሉን የሰማይ ሱራፌላዊ ሠሰራዊትን የተመለከተው እንዲህ ይላል፤
፪ ሁሉንም ነገሮች ሀየሚያውቀው እንዲህ ይላል፣ ምክንያቱም ለሁሉም ነገሮች በአይኖቼ ፊት ናቸውና፤
፫ የተናገርኩትም እኔ ነኝ፣ እናም አለም በእኔ ሀሆነ፣ እናም ሁሉም ነገሮች በእኔ መጡ።
፬ የሔኖክን ሀፅዮን ወደ እቅፌ የወሰድኩ እኔው ነኝ፤ እናም እውነት፣ እላለሁ፣ በስሜ ለየሚያምኑ ሁሉ፣ እኔ ክርስቶስ በመሆኔ፣ በስሜ፣ ባፈሰስኩት ሐደም ምክንያት በአብ ፊት አማልጃቸዋለሁ።
፭ ነገር ግን እነሆ፣ በምድር ዳርቻ በሚመጣው እስከ ታላቁ ሀፍርድ ቀን ድረስ የቀሩትን ለኃጢአተኞች በጨለማ ሐሰንሰለት ውስጥ አስቀምጫቸዋለሁ።
፮ እናም ድምጼን የማይሰማው እና ግን ልባቸውን የሚያደነድኑት ጥፋተኞች እንዲሁ እንዲቀመጡ አደርጋለሁ፣ እናም ወዮላቸው ጥፋታቸው ይሆናል።
፯ ነገር ግን እነሆ፣ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ሀአይኖቼም በእናንተ ላይ ናቸው። እኔም ለበመካከላችሁ ነኝ እናም እናንተም አታዩኝም፤
፰ ነገር ግን ሀየምታዩኝም ቀን በቶሎ ይመጣል፣ እናም እኔም እንደሆንኩ ታውቃላችሁ፤ የጨለማም መጋረጃም ይገፈፋል፣ እናም ለያልነጻ እርሱ ቀኑን ሐአይቋቋምም።
፱ ስለዚህ፣ ወገባችሁን ታጠቁ እናም ተዘጋጁ። እነሆ፣ ሀመንግስትም የእናንተ ናት፣ እናም ጠላትም አይቋቋማችሁም።
፲ እውነት እላችኋለሁ፣ ሀንጹሐን ናችሁ፣ ነገር ግን ሁላችሁም አይደላችሁም፤ እናም ከእናንተ ሌላ ለየተደሰትኩበት ማንም የለም፤
፲፩ በፊቴ ሁሉም ሀስጋ በስባሽ ነው፤ እናም በምድር ላይ፣ በሰው ልጆች መካከል፣ እና በሁሉም የሰማይ ሰራዊት ፊት ለየጭለማው ሀይል እያሸነፈ ነው—
፲፪ ይህም ዝምታ እንዲነግስ አደረገ፣ እናም ዘለአለማዊውም ሁሉ ሀተጎድቷል፣ እናም ለመላእክትም ሐገለባውን ሰብስበው መእንዲያቃጠሉ ምድርን ሠየሚሰበስቡበትን ታላቁን ትእዛዝ እየጠበቁ ናቸው፤ እናም፣ እነሆ ጠላትም ተባብሯል።
፲፫ እናም አሁን በጊዜ ሂደትም ሀጥፋታችሁ እንዲፈጸም፣ እልፍኝ ውስጥ ተቀምጦ የነበረውን አንድ ሚስጥርም አሳያችኋለሁ፣ እናም እናንተም አላወቃችሁትም፤
፲፬ ነገር ግን ይህን ለእናንተ እናገረዋለሁ፣ እና እናንተም የተባረካችሁት በኃጢአታችሁ ወይም በልባችሁ አለማመን ምክንያት አይደለም፤ አንዳንዶቻችሁ በፊቴ ጥፋተኞች ብትሆኑም፣ ነገር ግን ለድክመታችሁ ምህረትን አደርጋለሁ።
፲፭ ስለዚህ፣ ከአሁን ጊዜ ጀምሮ ሀብርቱዎች ሁኑ፤ ለአትፍሩ፣ መንግስተ ሰማይ የእናንተ ናትና።
፲፮ እናም ለደህንነታችሁ ትእዛዝን እሰጣችኋለሁ፣ ጸሎታችሁንም ሰምቻለሁና፣ እናም ሀድሆችም በፊቴ አጉረምርመዋል፣ እናም ለባለጠጎችንም የሰራኋቸው እኔው ነኝ፣ ስጋ ለባሽ ሁሉ የእኔ ነው፣ እኔም ለማንም ሐአላደላም።
፲፯ እናም ምድርን ባለጸጋ እንድትሆን አድርጌአለሁ፣ እናም እነሆ ሀየእግሬ መረገጫ ናት፣ ስለዚህም ዳግምም እቆምባታለሁ።
፲፰ እናም ጌታ በሚመጣበት ጊዜ እርግማን የሌለበትን ማር እና ወተት የሚፈስበትን እንዲሁም የቃል ኪዳንን ምድር፣ ከሁሉም በላይ ታላቅ የሆኑትን ሀብቶች፣ እሰጣችሁ ዘንድ እጄን እዘረጋለሁ እናም ይህም ይሆን ዘንድ ፍቃዴ ነው።
፲፱ እናም በሙሉ ልባችሁ የምትሹ ቢሆን የምትወርሱት ምድር እንዲሆን እስጣችኋለሁ።
፳ እናም ይህም ከእናንተ ጋር ቃልኪዳኔ ይሆናል፣ ለዘለአለም፣ ምድርም እስከቆመች ድረስ፣ ይህ ለእናንተ ሀውርስ ምድር እናም ለልጆቻችሁም የውርስ ይሆንላችኋል፣ እናም ደግሞም ለዘለአለም ዳግም ላያልፍ የእናንተ ይሆናል።
፳፩ ነገር ግን፣ እውነት እላችኋለሁ በዚያን ጊዜ ሀንጉስም ሆነ ገዢ አይኖራችሁም፣ እኔ ንጉሳችሁ እሆናለሁ እናም እጠብቃችኋለሁና።
፳፪ ስለዚህ፣ ድምጼን ስሙና ሀተከተሉኝ፣ እናም ለነፃ ህዝብም ትሆናላችሁ፣ እናም እኔ በምመጣበት ጊዜ ከእኔ ህግ በስተቀር ሌሎች ሕጎች አይኖሯችሁም፣ ሐህግን የምሰጣችሁ እኔ ነኝና፣ እናም እጄንስ ምን ያግደዋል?
፳፫ ነገር ግን፣ እላችኋለሁ፣ በሾምኳችሁ ስልጣን መሰረት እርስ በርስ ሀተማማሩ።
፳፬ እናም እያንዳንዱ ሰው ወንድሙን ሀእንደራሱ ይመልከት፣ እናም በፊቴ ለመልካምነትን አና ሐቅድስናን ተለማመዱ።
፳፭ እናም ዳግም እላችኋለሁ፣ ሁሉም ሰው ወንድሙን እንደራሱ ይመልከት።
፳፮ ከእናንተ መካከል አስራ ሁለት ልጆች ኖሮት፣ እነርሱም በታዛዥነት እያገለገሉት፣ እናም ለአንዱ፥ ያማረ ልብሰ ለብሰህ እዚህም ተቀመጥ፤ ለሌላኛውም፥ ብጣሽ ልብስ ለብሰህ እዚህ ተቀመጥ በማለት በእነርሱ ላይ አድሎን የሚያደርግ ማን ሰው በመካከላችሁ አለ—እናም ልጆቹን ተመልክቶ እኔ ፍትሀዊ ነኝ የሚል ማን ነው?
፳፯ እነሆ፣ ይህን ለእናንተ እንደምሳሌ ሰጠኋችሁ፣ እናም እኔም እንዲሁ ነኝና። እንዲህ እላችኋለሁ፣ ሀአንድ ሁኑ፤ እናም አንድ ካልሆናችሁ የእኔ አይደላችሁም።
፳፰ እናም ዳግም፣ ጠላትም በተሰውረ ስፍራ ሆኖ ሀሕይወታችሁን ይፈልጋል እላችኋለሁ።
፳፱ ሩቅም ከሆኑ ሀገሮች ሀጦርነትን ትሰማላችሁ፣ እናም ሩቅ ባሉ ሀገራትም ታላቅ ጦርነት በቅርቡም ይሆናል ትላላችሁ፣ ነገር ግን በምድራችሁ የሚገኙትን ህዝብ ልብ አታውቁም።
፴ በጸሎቶቻችሁ ምክንያት እነዚህ ነገሮችን እነግራችኋለሁ፤ ስለዚህ በልባችሁ ሀጥበብን ለአከማቹ፣ አለበለዚያ የሰዎች ኃጢአት መሬትን በሚነቀንቅ እና ከፍ ባለ ድምጽ በጆሮቻችሁ በመናገር፣ በኃጢአታቸው እነዚህ ነገሮች እንዲገለጡ ያደርጉላችኋል፤ ነገር ግን ከተዘጋጃችሁ ፍርሀት አይኖራችሁም።
፴፩ እናም የጠላትን ኃይል ታመልጡ ዘንድ፣ እናም ሀእንከን የሌላችሁ እና ያልነቀፉ ጻድቅ ህዝብ በመሆን ትሰበሰቡ ዘንድ—
፴፪ ሰለዚህ፣ በዚህም ምክንያት ወደ ሀኦሀዮ እንድትሄዱ ትእዛዛትን ሰጠኋችሁ፤ በዚያም ለህጌን እሰጣችኋለሁ፤ እና በዚያም ከላይ የሚመጣ ኃይል ሐትቀበላላችሁ።
፴፫ እናም ከዚያም ስፍራ፣ ፍቃዴ የሆነላቸው በሁሉም ህዝብ መካከል ሀይሄዳሉ፣ እና ምን እንደሚያደርጉም ይነገራቸዋል፤ ያስቀመጥቁት ታላቅም ስራ አለኝና፣ እስራኤልም ለትድናለችና፣ እና ወደምፈልግበትም ስፍራ እመራቸዋለሁ፣ እናም እጄን ምንም ኃይል ሐአያግደውም።
፴፬ እናም አሁን፣ በዚህ ስፍራ ለምትገኘው ቤተክርስቲያን የተወሰኑ ሰዎች በመካከላቸው እንዲሾሙ ትእዛዝን እሰጣለሁ፣ በቤተክርስቲያኗም ሀድምጽ ይሾማሉ፤
፴፭ ድሆችን እና ችግረኞችን ይንከባከባሉ፣ እንዳይሰቃዩም ሀበሚያስፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ ያገልግሏቸዋል፤ ወደ አዘዝኳቸውም ስፍራ እልካቸዋለሁ፤
፴፮ እናም የዚህች ቤተክርስቲያን ንብረት ጉዳይ ማስተዳደርም የእነርሱ ስራ ይሆናል።
፴፯ እናም ሊሸጥ የማይቻል የእርሻ ስፍራዎች ያሏቸው፣ መልካም እንደመሰላቸው ያከራዩት ወይም እንዲተዉ ያድርጉ።
፴፰ ሁሉም ነገሮች ተጠብቀው ያሉ መሆናቸውን አረጋግጡ፤ እናም ሰዎች ከላይ ሀመንፈሳዊ ስጦታ ሲሰጣቸውና ወደፊትም ሲላኩ፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በቤተክርስቲያኗ እቅፍ ውስጥ ይሰበሰባሉ።
፴፱ እናም አብ ሊሰጣችሁ የፈቀደውን ሀሀብት ከፈለጋችሁ፣ ከሁሉም ሰዎች በላይ ባለጠጋም ትሆናላችሁ፣ የዘለአለም ሀብትም ይኖራችኋልና፤ እናም እሰጣቸው ዘንድ የምድር ለሀብት ሁሉ የእኔ ነው፤ ነገር ግን ሐከኩራት ተጠበቁ፣ አለበለዚያም እንደ ጥንቶቹ መኔፋውያን ትሆናላችሁ።
፵ እናም ደግሞም፣ እላችኋለሁ፣ እያንዳንዱ ሰው፣ ሽማግሌው፣ ካህኑ፣ መምህሩ፣ እንዲሁም አባል ያዘዝኩትን፣ ባለው ሀይል ሁሉ እየተጓዘ ሀበእጆቹ ስራዎች፣ እንዲዘጋጅ እና እንዲያከናውን ትእዛዛትን እሰጣችኋለሁ።
፵፩ እናም እያንዳንዱ ሰው ለባልጀራው በደግነት እና በትህትና ሆኖ፣ ሀስብከታችሁም ለየማስጠንቀቂያ ድምጽ ይሁን።
፵፪ እናም ከኃጢአተኞችም መካከል ሀውጡ። ራሳችሁን አድኑ። የጌታን ዕቃ የምትሸከሙ ንፁሀን ሁኑ። እንዲህም ይሁን። አሜን።