ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፴፮


ክፍል ፻፴፮

በዊንተር ኮርተርስ፣ በእስራኤል ስፍራ፣ በኦማሀ ኔሽን ውስጥ፣ በሚዙሪ ወንዝ ምዕራብ ዳርቻ ላይ፣ በካውንስል ብላፍ አየዋ አጠገብ በፕሬዘደንት ብሪገም ያንግ በኩል የተሰጠ የጌታ ቃል እና ፈቃድ።

፩–፲፮፣ የእስራኤል ስፍራ ለምዕራቡ ጉዞ እንዴት እንደሚደራጅ ተገልጿል፤ ፲፯–፳፯፣ ቅዱሳን በብዙዎቹ የወንጌል መሰረቶች እንዲኖሩ ታዘዙ፤ ፳፰–፴፫፣ ቅዱሳን ይዘምሩ፣ እልልታንም ያድርጉ፣ ይጸልዩ፣ እና ጥበብን ይማሩ፤ ፴፬–፵፪፣ ነቢያት የሚገደሉት ይከበሩ እና ጥፋተኞችም ይኮነኑ ዘንድ ነው።

የእስራኤል ስፍራ ለምዕራቡ ጉዞአቸውን የተመልከተ የጌታ ቃል እና ፈቃድ፥

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ህዝብ ሁሉ፣ እና ከእነርሱ ጋር የሚጓዙት በቡድን የጌታ አምላካችንን ትእዛዛት እና ደንብ ለመከተል ቃል ኪዳን እና የተስፋ ቃል በመግባት ይደራጁ።

ቡድኖችም በአንድ መቶዎች አለቃዎች፣ በሀምሳዎች አለቃዎች፣ እና በአስሮች አለቃዎች፣ በሚመሯቸው ፕሬዘደንት እና ሁለት አማካሪዎች፣ በአስራ ሁለት ሐዋርያት አመራር መሰረት ይደራጁ።

እና ይህም ቃል ኪዳናችን ይሆናል፣ በጌታ ስርዓቶች ሁሉ እንሄዳለን

ሁሉም ቡድኖች የተጣመዱ እንስሣትን፣ ጋሪዎችን፣ የሚያስፈልጓቸውን፣ ልብሶችን፣ እና ሌላ ለጉዞ የሚያስፈልጉትን፣ ቢቻሉም፣ ራሳቸውን ያዘጋጁ።

ቡድኖች ከተደራጁ በኋላ ለሚቀሩት ለመዘጋጀት ለመስራት በሚችሉት ይሂዱ።

እያንዳንዱም ቡድን ከአለቆቻቸውና ከፕሬዘደንቶቻቸው ጋር በሚቀጥለው ጸደይ ምን ያህል ለመሄድ እንደሚችሉ ይወስኑ፤ ከዚያም ብቁ ሰውነት ያላቸው እና ችሎታ ያላቸው ሰዎች የተጠመዱ እንስሣሳትን፣ ዘሮችን፣ እና የማረሻ እቃዎችን ይዘው የጸደይ አትክልቶችን ለመትከል እንዲሄዱ ፈር ቀዳጆች የሚሆኑ ብቁ ቁጥሮችን ምረጡ።

የባልቴት እና አባት የሌላቸው ለቅሶዎች ወደጌታ ጆሮዎች በህዝብ ላይ እንዳይመጣ፣ እያንዳድኑም ቡድን በንብረቶቻቸውን በተከፋፈሉበት መጠን፣ ድሆችንባልቴቶችአባቶች የሌላቸውን፣ እና ወደ ጦር ሰራዊነት የሄዱትን ቤተሰቦችን በመውሰድ በእኩል ድርሻን ይሸከሙ።

እያንዳንዱም ቡድን ለዚህ ዘመን ለሚቀሩትም ቤቶች፣ እና እህልን ለመትከልም መሬቶችን ያዘጋጁ፤ እና ይህም ህዝቦቹን በሚመለከት የጌታ ፈቃድ ነው።

እያንዳንዱም ሰው የእራሱን ተፅዕኖ እና ንብረት ይህን ህዝቡ የፅዮንን ካስማ ጌታ ወደሚወስደው ስፍራ ለመውሰድ ይጠቀም።

፲፩ እና ይህን በንጹህ ልብ፣ በሙሉ ታማኝነት ብታደርጉ፣ ትባረካላችሁ፤ በመንጋዎቻችሁም፣ እና በመሬቶቻችሁ፣ እና በቤቶቻችሁ እና በቤተሰቦቻችሁ ትባረካላችሁ።

፲፪ አገልጋዮቼ ኤዝራ ቲ ቤንሰን እና ኢራስተስ ስኖው ቡድንን ያደራጁ።

፲፫ እና አገልጋዮቼ ኦርሰን ፕራት እና ዊልፈርድ ዉድረፍ ቡድንን ያደራጁ።

፲፬ ደግሞም፣ አገልጋዮቼ አማሳ ላይመን እና ጆርጅ ኤ ስሚዝ ቡድንን ያደራጁ።

፲፭ እና ፕሬዘደንቶችንና የመቶዎችን፣ የሀምሳዎች፣ እና የአስሮች አለቃዎችን ይመድቡ።

፲፮ እና የተመደቡትም ይሂዱ እና ወደ ሰላም ምድርም ለመሄድ ይዘጋጁ ዘንድ ይህን ፈቃዴን ለቅዱሳን ያስተምሩ።

፲፯ ሂዱ እና እንደ ነገርኳችሁም አድርጉ፣ እና ጠላቶቻችሁን አትፍሩ፤ ስራዬን ለማቆም ምንም ሀይል የላቸውምና።

፲፰ ፅዮንም በጊዜዬ ትድናለች

፲፱ ማንም ሰው እራሱን ከፍ ለማድረግ ቢፈልግ እና ምክሬን ባይፈልግ፣ ምንም ሀይል አይኖረውም እና ሞኝነቱም ግልጽ ይደረጋሉ።

ፈልጉ፤ እና የእርስ በርሳችሁን ቃል ኪዳኖች ሁሉ ጠብቁ፤ እና የወንድማችሁንም አትመኙ

፳፩ የእግዚአብሔርን የአምላካችሁን ስም በከንቱ የመጥራትን ክፋት ከራሳችሁ አስወግዱ፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ፣ የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሐምና የይስሀቅና የያዕቆብ አምላክ ነኝና።

፳፪ የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ ምድር መርቼ ያወጣኋቸው እኔ ነኝ፤ እና በመጨረሻዎቹም ቀናት እጆቼ የእስራኤልን ህዝብ ለማዳን ተዘርግተዋል።

፳፫ እርስ በራስም መጣላትን አቁሙ፤ እርስ በራስም ክፋት መነጋገርን አቁሙ።

፳፬ ሰካርን አቁሙ፤ እና ቃላቶቻችሁም እርስ በራሳችሁ የሚያንጹ ይሁኑ።

፳፭ ከባልንጀራችሁ ከተበደራችሁ፣ የተበረዳችሁን መልሱ፤ እና ለመክፈል ባትችሉም ወዲያው በመሄድ ለባንጀራችሁ ንገሩ፣ አለበለዚያም ይፈርድባችኋልና።

፳፮ ባልንጀሮቻችሁ ያጡትን ነገር ብታገኙ፣ ዳግሞም መልሳችሁ እስከምትሰጡም ድረስ በትጋት ፈልጉት።

፳፯ ጥበብ ያለው መጋቢም እንድትሆኑ ዘንድ፣ ያላችሁን ለመጠበቅ ትጉ ሁኑ፤ ይህም የጌታ አምላካችሁ የነጻ ስጦታ ነውና፣ እና እናንተም የእርሱ መጋቢ ናችሁና።

፳፰ ደስተኛ ብትሆኑ፣ ጌታን በዝማሬ፣ በሙዚቃ፣ በእልልታ፣ እና በምስጋና ጸሎት እና በምስጋና አምልኩ።

፳፱ የከፋችሁ ብትሆኑም፣ ነፍሶቻችሁ ይደሰቱ ዘንድ፣ ጌታ አምላካችሁን በልመና ጥሩ።

ጠላቶቻችሁን አትፍሩ፣ እነርሱ በእጆቼ ውስጥ ናቸው እና እንደፈቃዴም አደርግባቸዋለሁና።

፴፩ ለእነርሱ ያለኝን ክብር፣ እንዲሁም የፅዮንን ክብር፣ ለመቀበል ይዘጋጁ ዘንድ፣ ህዝቤ በሁሉም ነገሮች መሞከር አለባቸው፤ እና መገሰፅን ለመቀበል የማይችል ለመንግስቴ ብቁ አይደለም።

፴፪ ደንቆሮውም አይኖቹ ይከፈቱ ዘንድ እና እንዲያይ፣ እና ጆሮዎቹም ተከፍተው ይሰማ ዘንድ፣ ራሱን ትሁት በማድረግ እና ጌታ አምላኩን በመጥራት ጥበብን ይማር፤

፴፫ ትሁቱን እና የተዋረደውን አበራላቸው እና አምላክ የሌላቸውን እኮንን ዘንድ መንፈሴን ልኬአለሁና።

፴፬ ወንድሞቻችሁ፣ እንዲሁም ያሰደዷችሁ ህዝብ፣ እናንተን እና ምስክሮቻችሁን አስወግደዋል

፴፭ አሁንም በምጥ እንደተያዘች ሴት የሚያሳቅቃቸው ቀን፣ እንዲሁም የሀዘን ቀናት፣ ይመጣል፤ እና ወዲያው፣ አዎን፣ በጣም ፈጥነውም፣ ንስሀ ባይገቡ ሀዘናቸውም ታላቅ ይሆናል።

፴፮ ነቢያትንና ወደ እነርሱ የተላኩትን ገድለዋልና፤ እና ከምድር በእነርሱ ላይ የሚጮሁትንም ንጹህ ደም አፍሥሠዋል።

፴፯ ስለዚህ፣ በእነዚህ ነገሮች አትደነቁ፣ እናንት ንጹህ አይደላችሁምና፤ ክብሬን ለመቀበል ገና አትችሉም፤ ነገር ግን ከአዳም እስከ አብርሐም፣ ከአብርሐም እስከ ሙሴ፣ ከሙሴ እስከ ኢየሱስና ሐዋርያት፣ እና ከኢየሱስና ሐዋሪያቱ በሚያገለግሉኝ አገልጋዮቼ በመላእክቴ፣ እና ከሰማያት በድምጼ ስራዬን እንዲያመጣ በጠራሁት፣ እስከ ጆሴፍ ስሚዝ የሰጠኋችሁን ቃላቴን ለማክበር ታማኝ ከሆናችሁ፣ ይህንንም ታዩታላችሁ፤

፴፰ ይህን መሰረትም መሰረተ፣ እና ታማኝም ነበር፤ እና ወደ እኔም ወሰድኩት።

፴፱ ብዙዎች በሞቱ ምክንያት ተደንቀው ነበር፤ ነገር ግን እንዲከብር እና ክፉዎችም ይኮነኑ ዘንድ ምስክሩን በደሙ ማተሙ አስፈላጊ ነበር።

በዚህም የስሜን ምስክር በመተው ብቻ፣ ከጠላቶቻችሁ አላዳንኳችሁም?

፵፩ አሁን፣ ስለዚህ፣ የቤተክርስቲያኔ ህዝብ ሆይ፣ አድምጡ፤ እና እናንት ሽማግሌዎችም አብራችሁ ስሙ፤ መንግስቴን ተቀብላችኋል።

፵፪ ፍርድ እንዳይመጣባችሁ እና እምነታችሁም እንዳይወድቅባችሁ፣ እና ጠላቶቻችሁ እንዳያሸንፋችሁ ዘንድ፣ ትእዛዛቴን ሁሉ በማክበር ትጉ ሁኑ። በዚህ ጊዜ ተጨማሪ አልገልፅም። አሜን እና አሜን።