ክፍል ፻፴፮
በዊንተር ኮርተርስ፣ በእስራኤል ስፍራ፣ በኦማሀ ኔሽን ውስጥ፣ በሚዙሪ ወንዝ ምዕራብ ዳርቻ ላይ፣ በካውንስል ብላፍ አየዋ አጠገብ በፕሬዘደንት ብሪገም ያንግ በኩል የተሰጠ የጌታ ቃል እና ፈቃድ።
፩–፲፮፣ የእስራኤል ስፍራ ለምዕራቡ ጉዞ እንዴት እንደሚደራጅ ተገልጿል፤ ፲፯–፳፯፣ ቅዱሳን በብዙዎቹ የወንጌል መሰረቶች እንዲኖሩ ታዘዙ፤ ፳፰–፴፫፣ ቅዱሳን ይዘምሩ፣ እልልታንም ያድርጉ፣ ይጸልዩ፣ እና ጥበብን ይማሩ፤ ፴፬–፵፪፣ ነቢያት የሚገደሉት ይከበሩ እና ጥፋተኞችም ይኮነኑ ዘንድ ነው።
፩ የእስራኤል ስፍራ ለምዕራቡ ጉዞአቸውን የተመልከተ የጌታ ቃል እና ፈቃድ፥
፪ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ሀቤተክርስቲያን ህዝብ ሁሉ፣ እና ከእነርሱ ጋር የሚጓዙት በቡድን የጌታ አምላካችንን ትእዛዛት እና ደንብ ለመከተል ቃል ኪዳን እና የተስፋ ቃል በመግባት ይደራጁ።
፫ ቡድኖችም ሀበአንድ መቶዎች አለቃዎች፣ በሀምሳዎች አለቃዎች፣ እና በአስሮች አለቃዎች፣ በሚመሯቸው ፕሬዘደንት እና ሁለት አማካሪዎች፣ በአስራ ሁለት ለሐዋርያት አመራር መሰረት ይደራጁ።
፬ እና ይህም ሀቃል ኪዳናችን ይሆናል፣ በጌታ ለስርዓቶች ሁሉ ሐእንሄዳለን።
፭ ሁሉም ቡድኖች የተጣመዱ እንስሣትን፣ ጋሪዎችን፣ የሚያስፈልጓቸውን፣ ልብሶችን፣ እና ሌላ ለጉዞ የሚያስፈልጉትን፣ ቢቻሉም፣ ራሳቸውን ያዘጋጁ።
፮ ቡድኖች ከተደራጁ በኋላ ለሚቀሩት ለመዘጋጀት ለመስራት በሚችሉት ይሂዱ።
፯ እያንዳንዱም ቡድን ከአለቆቻቸውና ከፕሬዘደንቶቻቸው ጋር በሚቀጥለው ጸደይ ምን ያህል ለመሄድ እንደሚችሉ ይወስኑ፤ ከዚያም ብቁ ሰውነት ያላቸው እና ችሎታ ያላቸው ሰዎች የተጠመዱ እንስሣሳትን፣ ዘሮችን፣ እና የማረሻ እቃዎችን ይዘው የጸደይ አትክልቶችን ለመትከል እንዲሄዱ ፈር ቀዳጆች የሚሆኑ ብቁ ቁጥሮችን ምረጡ።
፰ የባልቴት እና አባት የሌላቸው ለቅሶዎች ወደጌታ ጆሮዎች በህዝብ ላይ እንዳይመጣ፣ እያንዳድኑም ቡድን በንብረቶቻቸውን በተከፋፈሉበት መጠን፣ ሀድሆችን፣ ለባልቴቶች፣ ሐአባቶች የሌላቸውን፣ እና ወደ ጦር ሰራዊነት የሄዱትን ቤተሰቦችን በመውሰድ በእኩል ድርሻን ይሸከሙ።
፱ እያንዳንዱም ቡድን ለዚህ ዘመን ለሚቀሩትም ቤቶች፣ እና እህልን ለመትከልም መሬቶችን ያዘጋጁ፤ እና ይህም ህዝቦቹን በሚመለከት የጌታ ፈቃድ ነው።
፲ እያንዳንዱም ሰው የእራሱን ተፅዕኖ እና ንብረት ይህን ህዝቡ የፅዮንን ሀካስማ ጌታ ወደሚወስደው ስፍራ ለመውሰድ ይጠቀም።
፲፩ እና ይህን በንጹህ ልብ፣ በሙሉ ታማኝነት ብታደርጉ፣ ሀትባረካላችሁ፤ በመንጋዎቻችሁም፣ እና በመሬቶቻችሁ፣ እና በቤቶቻችሁ እና በቤተሰቦቻችሁ ትባረካላችሁ።
፲፪ አገልጋዮቼ ኤዝራ ቲ ቤንሰን እና ኢራስተስ ስኖው ቡድንን ያደራጁ።
፲፫ እና አገልጋዮቼ ኦርሰን ፕራት እና ዊልፈርድ ዉድረፍ ቡድንን ያደራጁ።
፲፬ ደግሞም፣ አገልጋዮቼ አማሳ ላይመን እና ጆርጅ ኤ ስሚዝ ቡድንን ያደራጁ።
፲፭ እና ፕሬዘደንቶችንና የመቶዎችን፣ የሀምሳዎች፣ እና የአስሮች አለቃዎችን ይመድቡ።
፲፮ እና የተመደቡትም ይሂዱ እና ወደ ሰላም ምድርም ለመሄድ ይዘጋጁ ዘንድ ይህን ፈቃዴን ለቅዱሳን ያስተምሩ።
፲፯ ሂዱ እና እንደ ነገርኳችሁም አድርጉ፣ እና ጠላቶቻችሁን አትፍሩ፤ ስራዬን ለማቆም ምንም ሀይል የላቸውምና።
፲፰ ፅዮንም በጊዜዬ ሀትድናለች።
፲፱ ማንም ሰው እራሱን ከፍ ለማድረግ ቢፈልግ እና ሀምክሬን ባይፈልግ፣ ምንም ሀይል አይኖረውም እና ሞኝነቱም ግልጽ ይደረጋሉ።
፳ ፈልጉ፤ እና የእርስ በርሳችሁን ቃል ኪዳኖች ሁሉ ሀጠብቁ፤ እና የወንድማችሁንም ለአትመኙ።
፳፩ የእግዚአብሔርን የአምላካችሁን ስም በከንቱ የመጥራትን ክፋት ከራሳችሁ ሀአስወግዱ፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ፣ የአባቶቻችሁ ለአምላክ፣ የአብርሐምና የይስሀቅና የያዕቆብ አምላክ ነኝና።
፳፪ የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ ምድር መርቼ ያወጣኋቸው ሀእኔ ነኝ፤ እና በመጨረሻዎቹም ቀናት እጆቼ የእስራኤልን ህዝብ ለለማዳን ተዘርግተዋል።
፳፫ እርስ በራስም ሀመጣላትን አቁሙ፤ እርስ በራስም ለክፋት መነጋገርን አቁሙ።
፳፬ ሀሰካርን አቁሙ፤ እና ቃላቶቻችሁም እርስ በራሳችሁ ለየሚያንጹ ይሁኑ።
፳፭ ከባልንጀራችሁ ከተበደራችሁ፣ ሀየተበረዳችሁን መልሱ፤ እና ለመክፈል ባትችሉም ወዲያው በመሄድ ለባንጀራችሁ ንገሩ፣ አለበለዚያም ይፈርድባችኋልና።
፳፮ ባልንጀሮቻችሁ ሀያጡትን ነገር ብታገኙ፣ ዳግሞም መልሳችሁ እስከምትሰጡም ድረስ በትጋት ፈልጉት።
፳፯ ጥበብ ያለው መጋቢም እንድትሆኑ ዘንድ፣ ያላችሁን ለመጠበቅ ሀትጉ ሁኑ፤ ይህም የጌታ አምላካችሁ የነጻ ስጦታ ነውና፣ እና እናንተም የእርሱ ለመጋቢ ናችሁና።
፳፰ ደስተኛ ብትሆኑ፣ ጌታን ሀበዝማሬ፣ በሙዚቃ፣ በእልልታ፣ እና በምስጋና ለጸሎት እና ሐበምስጋና አምልኩ።
፳፱ ሀየከፋችሁ ብትሆኑም፣ ነፍሶቻችሁ ለይደሰቱ ዘንድ፣ ጌታ አምላካችሁን በልመና ጥሩ።
፴ ጠላቶቻችሁን አትፍሩ፣ እነርሱ በእጆቼ ውስጥ ናቸው እና እንደፈቃዴም አደርግባቸዋለሁና።
፴፩ ለእነርሱ ያለኝን ሀክብር፣ እንዲሁም የፅዮንን ክብር፣ ለመቀበል ይዘጋጁ ዘንድ፣ ህዝቤ በሁሉም ነገሮች ለመሞከር አለባቸው፤ እና ሐመገሰፅን ለመቀበል የማይችል ለመንግስቴ ብቁ አይደለም።
፴፪ ደንቆሮውም አይኖቹ ይከፈቱ ዘንድ እና እንዲያይ፣ እና ጆሮዎቹም ተከፍተው ይሰማ ዘንድ፣ ራሱን ሀትሁት በማድረግ እና ጌታ አምላኩን በመጥራት ለጥበብን ይማር፤
፴፫ ትሁቱን እና የተዋረደውን አበራላቸው እና አምላክ የሌላቸውን እኮንን ዘንድ ሀመንፈሴን ልኬአለሁና።
፴፬ ወንድሞቻችሁ፣ እንዲሁም ያሰደዷችሁ ህዝብ፣ እናንተን እና ምስክሮቻችሁን ሀአስወግደዋል፤
፴፭ አሁንም በምጥ እንደተያዘች ሴት የሚያሳቅቃቸው ቀን፣ እንዲሁም የሀዘን ቀናት፣ ይመጣል፤ እና ወዲያው፣ አዎን፣ በጣም ፈጥነውም፣ ንስሀ ባይገቡ ሀዘናቸውም ታላቅ ይሆናል።
፴፮ ነቢያትንና ወደ እነርሱ የተላኩትን ገድለዋልና፤ እና ከምድር በእነርሱ ላይ የሚጮሁትንም ንጹህ ደም አፍሥሠዋል።
፴፯ ስለዚህ፣ በእነዚህ ነገሮች አትደነቁ፣ እናንት ሀንጹህ አይደላችሁምና፤ ክብሬን ለመቀበል ገና አትችሉም፤ ነገር ግን ከአዳም እስከ አብርሐም፣ ከአብርሐም እስከ ሙሴ፣ ከሙሴ እስከ ኢየሱስና ሐዋርያት፣ እና ከኢየሱስና ሐዋሪያቱ በሚያገለግሉኝ አገልጋዮቼ ለበመላእክቴ፣ እና ከሰማያት በድምጼ ስራዬን እንዲያመጣ በጠራሁት፣ እስከ ጆሴፍ ስሚዝ ሐየሰጠኋችሁን ቃላቴን ለማክበር ታማኝ ከሆናችሁ፣ ይህንንም ታዩታላችሁ፤
፴፰ ይህን መሰረትም መሰረተ፣ እና ታማኝም ነበር፤ እና ወደ እኔም ወሰድኩት።
፴፱ ብዙዎች በሞቱ ምክንያት ተደንቀው ነበር፤ ነገር ግን እንዲከብር እና ክፉዎችም ይኮነኑ ዘንድ ሀምስክሩን ለበደሙ ሐማተሙ አስፈላጊ ነበር።
፵ በዚህም የስሜን ምስክር በመተው ብቻ፣ ሀከጠላቶቻችሁ አላዳንኳችሁም?
፵፩ አሁን፣ ስለዚህ፣ ሀየቤተክርስቲያኔ ህዝብ ሆይ፣ አድምጡ፤ እና እናንት ሽማግሌዎችም አብራችሁ ስሙ፤ ለመንግስቴን ተቀብላችኋል።
፵፪ ፍርድ እንዳይመጣባችሁ እና እምነታችሁም እንዳይወድቅባችሁ፣ እና ጠላቶቻችሁ እንዳያሸንፋችሁ ዘንድ፣ ትእዛዛቴን ሁሉ በማክበር ትጉ ሁኑ። በዚህ ጊዜ ተጨማሪ አልገልፅም። አሜን እና አሜን።