ክፍል ፻፲
በሚያዝያ ፫፣ ፲፰፻፴፮ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝና ለኦሊቨር ካውድሪ የተገለጡ ራዕዮች። ጊዜውም በሰንበት የስብሰባ ቀን ነበር። የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ እንደሚገልጸው፥ “በዚህ ቀን እና ረፋድ፣ የጌታን እራት በቅዱስ ጠረጴዛው ላይ ለማስተዳደር ልዩ መብት ከነበራቸው ከአስራ ሁለቱ በመቀበል ለቤተክርስቲያን ለማደል ሌሎቹን ፕሬዘደንቶች ረዳሁ። ይህን አገልግሎት ለወንድሞቼ ካከናወንኩ በኋላ፣ ወደ መስበኪያው ተመለስኩኝ፣ መጋረጃውን በመዝጋት እና ከኦሊቨር ካውድሪ ጋር በአክብሮት እና ጸጥተኛ ጸሎት አጎነበስኩኝ። ከጸሎት ከተነሳሁም በኋላ፣ የሚቀጥለው ራዕይ ለሁለታችን ተከፈተልን”።
፩–፲፣ ጌታ ያህዌህ በክብር መጣ እና የከርትላንድ ቤተመቅደስን እንደ ቤቱ ተቀበለ፤ ፲፩–፲፪፣ ሙሴ እና ኤልያስ እያንዳንዳቸው ተገለጡ እና ቁልፎቻቸውን እና የዘመን ፍጻሜዎቻቸውንም ሰጡ፤ ፲፫–፲፮፣ በሚልክያስ ቃል እንደተገባውም ኤልያስ ተመለሰ እና የዘመን ፍጻሜውን ቁልፎች ሰጠ።
፩ ሀመጋረጃው ከአዕምሮዎቻችን ተወገደ፣ እና የመረጃ ለአይኖቻችንም ተከፈቱ።
፪ ጌታን በመስበኪያው መደገፊያ ላይም በፊት ለፊታችን አየነው፤ እና ከእግሮቹም በታች የቡናማ ቢጫ ቀለም አይነት የነበረ ንጹህ ወርቅ የተነጠፈበት የሚመስል ስራ ነበር።
፫ ሀዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤ የራሱ ጠጕርም እንደ ንጹህ በረዶም ነጭ ነበሩ፤ ለፊቱም ከብርቱ የጸሀይ ብርሀን በላይ የሚያበራ ነበር፤ ሐድምፁም እንዲህ የሚል እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ፣ እንዲሁም መየያህዌህ ድምፅ ነበር፥
፬ እኔ ሀፊተኛውና ኋለኛው ነኝ፤ እኔ ለህያውም ነኝ፣ የተገደልኩትም እኔ ነኝ፤ እኔም በአብ ዘንድ ሐአማላጃችሁ ነኝ።
፭ እነሆ፣ ኃጢአታችሁ ሀተሰርየዋል፤ በፊቴም ንጹህ ናችሁ፤ ስለዚህም፣ ራሳችሁን አቅኑ እናም ተደሰቱ።
፮ የወንድሞቻችሁ ልብም ይደሰት፣ እና በሀይላቸው ይህን ሀቤት በስሜ የሰሩት የህዝቤም ልብ ሁሉ ይደሰት።
፯ እነሆ፣ ይህን ሀቤት ለተቀብዬዋለሁ፣ እና ስሜም በዚህ ይሆናል፤ እና በምህረትም ራሴን ለህዝቤ አሳያለሁና።
፰ አዎን፣ ህዝቤ ትእዛዛቴን ቢጠብቁ፣ እና ይህን ሀቅዱስ ቤት ለባያጎድፍ፣ ለአገልጋዮቼ ሐእገልጣለሁ፣ እና በራሴም ድምፅ አናገራቸዋለሁ።
፱ አዎን፣ በሚፈሱት ሀበረከቶች እና አገልጋዮቼ በዚህ ቤት ውስጥ በተቀበሉት ለመንፈሳዊ ስጦታዎች ምክንያት የሺዎች እና የአስር ሺዎች ልብ በእጅጉ ይደሰታሉ።
፲ እና የዚህ ቤት ዝናም በውጪ አገሮች ይስፋፋል፤ እና ይህም በህዝቤ ራሶች ላይ ሀየሚፈሰው የበረከት መጀመሪያም ነው። እንዲህም ይሁን። አሜን።
፲፩ ይህ ሀራዕይ ከተፈጸመ በኋላ፣ ሰማያት ዳግም ተከፈቱልን፤ እና ለሙሴ በፊታችን መጣ፣ እና ከምድር አራት ማዕዘናትን የእስራኤልን ሐመሰብሰቢያ እና መከሰሜን ምድር የአስሩን ነገዶች መምሪያ ሠቁልፎችን ሰጠን።
፲፪ ከዚህ በኋላ፣ ሀኤልያ መጣ፣ እና በእኛና በዘራችን ከእኛም በኋላ የሚመጡ ትውልዶች ሁሉ ይባረካሉ በማለት የአብርሐም ለወንጌል ሐየዘመን ፍጻሜን ሰጠን።
፲፫ ይህ ራዕይ ከተፈጸመ በኋላ፣ ሌላ ታላቅ እና የክብር ራዕይ ተከፈተልን፤ ሞትን ሳይቀምስ ወደሰማይ ሀየተወሰደው ነቢዩ ለኤልያስ በፊት ለፊታችን ቆመ፣ እናም አለ፥
፲፬ እነሆ፣ በሚልክያስ አንደበት በመመስከር ተነግሮ የነበረው ጊዜ በሙላት መጥቷል—ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ እርሱ [ኤልያስ] እንደሚላክ—
፲፭ ይህም፣ ምድር በእርግማን እንዳትመታ፣ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ሀለመመለስ እንዳለበት ተነግሮ የነበረው ጊዜ በሙላት መጥቷል።
፲፮ ስለዚህ፣ የዚህ የዘመን ፍጻሜ ቁልፎች በእጆቻችሁ ተሰጥተዋል፤ እና ይህም ታላቁና የሚያስፈራው የጌታ ሀቀን ቅርብ እንደሆነ፣ እንዲሁም በበር ላይ እንዳለም፣ ታውቃላችሁ።