ክፍል ፶
በግንቦት ፱፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ፣ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ እንደሚገልጸው፣ አንዳንድ ሽማግሌዎች እንዴት የተለያዩ መናፍስት ራሳቸውን በአለም ላይ እንደሚገልጹ እንዳልገባቸው፣ እናም ስለዚህ ጉዳይ ባደረገው ልዩ ጥያቄ ምክንያትም ይህ ራዕይ እንደተሰጠ ገለጸ። መንፈሳዊ አጋጣሚዎች የሚባሉት በአባላቱ መካከል አዲስ አልነበሩም፣ አንዳንዶችም ራዕዮችንና መግለጦንች ተቀብለናል ይሉም ነበር።
፩–፭፣ ብዙ የሀሰት መናፍስት በምድር ውስጥ ይገኛሉ፤ ፮–፱፣ ለግብዞች እና ከቤተክርስቲያኗ ለሚቆረጡት ወዮላቸው፤ ፲–፲፬፣ ሽማግሌዎች ወንጌሉን በመንፈስ ይስበኩ፤ ፲፭–፳፪፣ ሰባኪዎቹ እና ሰሚዎቹም በመንፈስ መታነጽ ያስፈልጋቸዋል፤ ፳፫–፳፭፣ የማያንጸውም ከእግዚአብሔርም የሚመጣ አይደለም፤ ፳፮–፳፰፣ ታማኞች የሁሉም ነገሮች ባለቤቶች ናቸው፤ ፳፱–፴፮፣ የንጹህ ሰዎች ጸሎቶችም መልስ ያገኛሉ፤ ፴፯–፵፮፣ ክርስቶስ መልካም እረኛ እና የእስራኤል አለት ነው።
፩ የቤተክርስቲያኔ ሽማግሌዎች ሆይ፣ አድምጡ፣ እና ለሕያው አምላክም ድምፅ ጆሮአችሁን ስጡ፤ እናም በምድር ውስጥ ስላሉት መናፍስት፣ እና ቤተክርስቲያኗን እንደሚነካው እና እንደተስማማችሁት ስለጠየቃችሁኝ የሚሰጣችሁን የጥበብ ቃላት አድምጡ።
፪ እነሆ፣ እውነት እንዲህ እላችኋለሁ፣ አለምን የሚያታልሉ፣ በምድር ውስጥ የሚሄዱ፣ ብዙ የሀሰት መናፍስት የሆኑ መናፍስት አሉ።
፫ እናም ሰይጣን፣ እንዲጥላችሁም፣ ሊያታልላችሁ ፈልጓል።
፬ እነሆ፣ እኔ ጌታ እናንተን ተመልክቼአለሁ፣ እናም በስሜ በምትታወቀው ቤተክርስቲያን ውስጥም አፀያፊነቶችን ተመልክቻለሁ።
፭ ነገር ግን፣ በህይወትም ይሁን በሞት፣ ታማኝ የሆኑ እና የሚጸኑ የተባረኩ ናቸው፣ ዘለአለማዊ ህይወትን ይወርሳሉና።
፮ ነገር ግን ለሚያስቱ እና ለግብዞችም ወዮላቸው፣ ምክንያቱም፣ ጌታ እንዲህ ይላል፣ ወደ ፍርድ አመጣቸዋለሁና።
፯ እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ መካከል፣ አንዳንዶችን በማታለል ለጠላት ሀይል የሰጡ ግብዞች አሉ፤ ነገር ግን እነሆ እነዚህም ደግመው ሊመለሱ ይችላሉ፤
፰ ግብዞቹ ግን፣ በዚህ ህይወትም ይሁን በሞት፣ እንደፈቃዴ ይታወቃሉ እናም ይቆረጣሉ፤ እናም ከቤተክርስቲያኔ ለተቆረጡ ለእነርሱ ወዮላቸው፣ በአለም ተሸንፈዋልና።
፱ ስለዚህ፣ በፊቴ እውነት እና ፅድቅ ያልሆነውን እንዳያደርግ እያንዳንዱ ሰው ይጠንቀቅ።
፲ እናም አሁን፣ በመንፈስ ወደ ቤተክርስቲያኑ ሽማግሌዎች፣ ኑ ይላል ጌታ፣ እና ይገባችሁ ዘንድ እንወቃቀስ፤
፲፩ ሰው እርስ በርሱ እንደሚወቃቀስም ፊት ለፊት እንወቃቀስ።
፲፪ አሁን፣ አንድ ሰው ሲወቃቀስ ሰውም ይረዳዋል፣ ምክንያቱም እንደ ሰው ይወቃቀሳልና፣ እንዲሁም እኔ ጌታ፣ ይገባችሁ ዘንድ ከእናንተ ጋር እወቃቀሳለሁ።
፲፫ ስለዚህም፣ እኔ ጌታ ይህን እጠይቃችኋለሁ—ስለምን ነበር የተሾማችሁት?
፲፬ በመንፈስ፣ እንዲሁም እውነትን ለማስተማር በተላከው አፅናኝ፣ ወንጌሌን ትሰብኩ ዘንድ ነው።
፲፭ እና ከዚያም የማይገባችሁን መናፍስት ተቀብላችሁ፣ እናም ከእግዚአብሔር እንደሆኑም በማስመሰል እነዚህን ትቀበላላችሁ፤ እናም በዚህስ ትጸደቃላችሁን?
፲፮ እነሆ ይህን ጥያቄ ራሳችሁ ትመልሳላችሁ፤ ይሁን እንጂ፣ ምህረት አደርግላችኋለሁ፤ ከዚህ በኋላ በእናንተ መካከል ደካማ የሆነ ብርቱም ይሆናል።
፲፯ እውነት እላችኋለሁ፣ በእኔ ተሹሞ እና፣ በእውነት መንፈስ በኩል፣ በአፅናኙ የእውነትን ቃል ለመስበክ እንዲሄድ የታዘዘ፣ በእውነት መንፈስ ይሰብካልን ወይስ በሌላ ዘዴ?
፲፰ እናም በሌላ ዘዴ ከሆነ ከእግዚአብሔር አይደለም።
፲፱ እና ደግሞም፣ የእውነትንስ ቃል የተቀበለው፣ በእውነት መንፈስ ነው ወይስ በሌላ ዘዴ?
፳ በሌላ ዘዴ ከሆነ ከእግዚአብሔር አይደለም።
፳፩ ስለዚህ፣ ቃልን በእውነት መንፈስ የተቀበለው በእውነት መንፈስ ተሰብኮለት እንደተቀበለው፣ የማይገባችሁ እናም የማታውቁት ለምንድን ነው?
፳፪ በዚህም ምክንያት፣ የሚሰብከው እና የሚቀበለውም እርስ በርሳቸው ይግባባሉ፣ እና ይተናነጻሉ እና አብረውም ይደሰታሉ።
፳፫ እና ያለማነጽ ያልሆነውም ከእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም፣ እና ከጭለማ ነው።
፳፬ ከእግዚአብሔር የሆነው ብርሀን ነው፤ እና ብርሀንን ተቀብሎ በእግዚአብሔር የሚቀጥል፣ ተጨማሪ ብርሀንን ይቀበላል፤ እናም ብርሀኑም ፍጹም እስከሆነው ቀን ድረስም እየጨመረ ይበራል።
፳፭ እና ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እናም ይህን የምለውም እውነቱን ታውቁ ዘንድ፣ ከመካከላችሁም ጭለማን ታስወግዱ ዘንድ ነው፤
፳፮ ምንም እንኳን እርሱ ታናሽ እና የሁሉ አገልጋይ ቢሆንም፣ በእግዚአብሔር የተሾመ እና የተላከ፣ እርሱ ታላቅ ይሆን ዘንድ ተመርጧል።
፳፯ በመሆኑም፣ እርሱ የሁሉም ነገሮች ባለቤት ነው፤ በሰማይ እናም በምድር በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ አብ ፈቃድ የተላኩ ነገሮች ሁሉ፣ ህይወት እና ብርሀን፣ መንፈስ እና ሀይል፣ ለእርሱ ተገዢ ናቸውና።
፳፰ ነገር ግን ከሁሉም ኃጢአት የጸዳ እና የነጻ ካልሆነ በስተቀር ማንም ሰው የሁሉም ነገሮች ባለቤት ሊሆን አይችልም።
፳፱ እና ከሁሉም ኃጢአቶች ከጸዳችሁ እና ከነጻችሁ፤ የምትሹትን ሁሉ በኢየሱስ ስም ትጠይቃላችሁ እናም ይህም ይከናወናል።
፴ ነገር ግን ይህን እወቁ፣ የጠየቃችሁት ይሰጣችኋል፤ እናም የመሪነት ሀላፊነት ሲሰጣችሁም፣ መናፍስትም ይገዙላችኋል።
፴፩ በመሆኑም፣ እንዲህም ይሆናል፣ የማትረዱትን መንፈስ ስታዩ፣ እና መንፈሱንም ካልተቀበላችሁ፣ አብን በኢየሱስ ስም ጠይቁ፤ እና ያን መንፈስ እርሱ ካልሰጣችሁ፣ ከዚያም ከእግዚአብሔር እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።
፴፪ እና ለእናንተም በዚያ መንፈስ ላይም ሀይል ይሰጣችኋል፤ እና ያ መንፈስ ከእግዚአብሔር እንዳልሆነም በታላቅ ድምጽ ታሳውቁታላችሁ፣
፴፫ በመንፈሱም እንዳትሸንፉ፣ በስድብ ቃል ሳይሆን፣ ወይም በዚያም እንዳትያዙ፣ በኩራት ወይም በደስታ ሳይሆን፣ ከእግዚአብሔር እንዳልሆነ ታሳውቁታላችሁ።
፴፬ ከእግዚአብሔር የተቀበለውም፣ ከእግዚአብሔር እንደተቀበለው ይቁጠረው፤ እናም ለመቀበልም በእግዚአብሔር ብቁ ሆኖ ስለተቆጠረም ይደሰት።
፴፭ እናም በማድመጥ እናም የተቀበላችሁትን እነዚህን ነገሮች—እናም ከአብ መንግስቱን፣ እና ከእርሱ ያልተመደቡትን ነገሮች ለማሸነፍ ሀይል ተሰጥቷችኋል—እናም ከዚህም በኋላ የምትቀበሏቸውን በማድረግ፣
፴፮ እናም እነሆ፣ በእውነትም እንዲህ እላችኋላሁ፣ በአገልጋዬ አንደበት የተሰጡትን እነዚህን ቃላቴን አሁን የምታደምጡ ሁሉ የተባረካችሁ ናችሁ፣ ለኃጢአቶቻችሁ ምህረት ተሰጥቷችኋልና።
፴፯ የተደሰትኩበት አገልጋዬ፣ ጆሴፍ ዌክፊልድ እና አገልጋዬ ፓርሊ ፒ ፕራት ከቤተክርስቲያናቱ መካከል ይሂዱ እናም በምክር ቃላትም ያጠናክሯቸው፤
፴፰ እናም አገልጋዬ ጆን ኮርል፣ ወይም ለዚህ ሀላፊነት የተሾሙት አገልጋዮቼ ሁሉ፣ በወይን ስፍራ ወስጥ ያገልግሉ፤ እና ሀላፊነት የሰጠኋቸውን ነገሮች ያከናውኑ ዘንድ ማንም ሰው አያደናቅፋቸው—
፴፱ ስለዚህ፣ በዚህ ነገር አገልጋዬ ኤድዋርድ ፓርትሪጅ ትክክል አይደለም፤ ይህም ቢሆን ንስሀ ይግባ እናም ይቅርታን ይቀበላል።
፵ እነሆ፣ እናንት ህጻናት ናችሁ እና ሁሉንም ነገሮች አሁን ትሸከሙ ዘንድ አትችሉም፤ በጸጋ እና በእውነት እውቀትም ማደግ አለባችሁ።
፵፩ እናንት አትፍሩ፣ ህጻናት፣ የእኔ ናችሁና፣ እናም እኔ አለምን አሸንፌዋለሁ፣ እና እናንተም ከአባቴ ዘንድ የተሰጣችሁ ናችሁ፤
፵፪ አባቴ ከሰጠኝ ማንኛቸውም አይጠፋም።
፵፫ እናም አብ እና እኔ አንድ ነን። እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ ነው፤ እና እኔን ከተቀበላችሁ፣ እናንተ በእኔ አላችሁ እና እኔም በእናንተ አለሁ።
፵፬ ስለዚህ፣ እኔ በመሀከላችሁ ነኝ፣ እና እኔም መልካሙ እረኛ፣ እና የእስራኤል ድንጋይ ነኝ። በዚህ አለት ላይ የተመሰረተም አይወድቅም።
፵፭ እና ድምጼን የምትሰሙበትና እና የምታዩኝ፣ እና እኔ እንደሆንኩኝም የምታውቁበት ቀን ይመጣል።