ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፲፱


ክፍል ፲፱

በበጋ ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) አካባቢ በማንቺስተር ኒው ዮርክ በጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት የተሰጠ ራዕይ። በታሪኩ ውስጥ፣ ነቢዩ ይህን “ለማርቲን ሀሪስ በሰው ሳይሆን ዘለአለማዊ በሆነው በእግዚአብሔር የተስጠ ትእዛዝ” ብሎ አስተዋወቀ።

፩–፫፣ ክርስቶስ ሁሉም ስልጣን አለው፤ ፬–፭፣ ሰዎች ሁሉ ንሰሀ መግባት አለባቸው ወይም ይሰቃያሉ፤ ፮–፲፪፣ ዘለአለማዊ ቅጣት የእግዚአብሔር ቅጣት ነው፤ ፲፫–፳፣ ንስሀ ቢገቡ እንዳይሰቃዩ ክርስቶስ ለሰዎች ሁሉ ተሰቃየ፣ ፳፩–፳፰፣ የንስሀን ወንጌል ስበክ፤ ፳፱–፵፩፣ የምስራችን ቃል አውጅ።

እኔ አልፋና ዖሜጋ፣ ጌታ ክርስቶስ ነኝ፤ አዎን፣ መጀመሪያውና መጨረሻው እናም የአለም ቤዛ የሆንኩት እኔ ነኝ።

ነገሮችን ሁሉ ለእኔ ይገዙ ዘንድ ይህንንም በማድረግ፣ የእርሱ የሆንኩት አብ ለእኔ ያለውን ፈቃድ አከናውኛለሁ እናም ጨረሻለሁ

ሰይጣንን እና ስራዎቹን በአለም ፍጻሜ ለማፍረስ፣ እና እያንዳንዱን ሰው በተግባሩ መሰረት በመፍረድ በዚያ በሚኖሩት ላይ እንድፈርድባቸው ዘንድ ሀይልን እና የመጨረሻ ታላቅ የቅጣት ቀንን በመያዝ የአብን ፈቃድ አከናውናለሁ።

እናም እያንዳንዱ ሰው ንስሀ መግባት አለበት ወይም ይሰቃያል፤ እኔ እግዚአብሔር መጨረሻ የለኝምና።

ስለዚህ የማሳልፈውን ፍርድ አልሽርም፣ ነገር ግን፣ አዎን፣ በግራዬ ለሚሆኑት ዋይታ፣ ልቅሶ እና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።

ምንም እንኳን፣ ይህ ስቃይ ማብቂያ እንደሌለው ባይጻፍም፣ ነገር ግን ገደብ የለሽ ስቃይ ተብሎ ተጽፏል።

ዳግም፣ ዘለአለማዊ ኩነኔ ተብሎ ተጽፋል፤ ስለዚህ በአንድ ላይ ለስሜ ክብር በሰዎች ልጆች ልብ ላይ ይሰራ ዘንድ ከሌሎች የቅዱስ መጻሕፍት ጽሁፎች በበለጠ ግልጽ ነው።

ስለዚህ፣ ይህንን ሚስጥር ለአንተ እገልጽልኅለሁ፣ አንተም እንደ እኔ ኃዋርያቴ ታውቅ ዘንድ ስለሚገባ ነውና።

አንድ ሆናችሁ ወደ እረፍቴ ትገቡ ዘንድ ለዚህ ስራ ለተመረጣችሁት ለእናንተ እናገራለሁ።

ስለሆነም፣ እነሆ፣ የአምላክነት ሚስጥር እንዴት ታላቅ ነው! ስለሆነም፣ እነሆ፣ እኔ መጨረሻ የለኝም፣ እናም ከእጄ የሚሰጠው ቅጣት መጨረሻ የሌለው ቅጣት ነው፣ ስሜም መጨረሻ የሌለውም ነውና። ስለዚህ—

፲፩ ዘለአለማዊ ቅጣት የእግዚአብሔር ቅጣት ነው።

፲፪ መጨረሻ የሌለው ቅጣት የእግዚአብሔር ቅጣት ነው።

፲፫ ስለዚህ፣ ንስሀ እንድትገባ እና በስሜ ከአገልጋዬ ከጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ እጅ የተቀበልካቸውን ትእዛዛት እንድትጠብቅ አዝኃለሁ፤

፲፬ እናም እነዚህንም በኃያሉ ኃይሌ ነው የተቀበልከው፤

፲፭ ስለዚህ ንስሀ እንድትገባ አዝሀለሁ—ንስሀ ግባ አለበለዚያ በቁጣዬ እናም በንዴቴ እናም በአፌ በትር እመታሀለሁ እናም ስቃይህ መራር ይሆናል—ምን ያህል መራር እንደሆነ አታውቅም፣ ምን ያህል እንደሚጎዳህ እንደሆነ አታውቀውም፣ አዎን፣ ምን ያህል ለመሸከም እንደሚከብድ አታውቀውም።

፲፮ ስለሆነም፣ እነሆ፣ ንስሀ ከገቡ እንዳይሰቃዩ ዘንድ እኔ እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች ለሁሉም ተሰቃይቻለሁ

፲፯ ነገር ግን ንስሀ ካልገቡ እኔ እንደተሰቃየሁት መሰቃየት አለባቸው፤

፲፰ ይህም ስቃይ የሁሉም ታላቅ የሆንኩትን እኔን እግዚአብሔርን፣ ከስቃዩ የተነሳ እንድንቀጠቀጥ እናም ከእያንዳንዱ ቀዳዳ እንድደማ እናም በአካል እና በመንፈስ እንድሰቃይ እናም መራራውን ጽዋ እንዳልጠጣ እንድፈልግ እና እንድሸማቀቅ ያደረገኝን ነው።

፲፱ ሆኖም፣ ለአብ ክብር ይሁን፣ እናም ጠጥቼዋለሁ እናም ለሰዎች ልጆችም ዝግጅቴን ጨርሻለሁ

ሰለዚህ፣ ዳግም ንሰሀ እንድትገባ አዝሀለሁ፣ አለበለዚያም በኃያሉ ኃይሌ ትሁት አደርግሀለሁ፤ እናም ሰለዚህ ኃጢአትህን ተናዘዝ፣ አለበለዚያም የተናገርኩትን፣ አዎን፣ መንፈሴን ካንተ በወሰድኩበት ጊዜ በአነሰ ደረጃ የቀመስከውን፣ ቅጣቴን ትሰቃያለህ።

፳፩ እናም ከንሰሀ በቀር ምንም እንዳትሰብክ አዝሀለሁ፣ እናም በእኔ ጥበብ እስኪሆን ድረስ እነዚህን ነገሮች ለአለም እንዳታሳይ

፳፪ ስለሆነም፣ ስጋን አሁን መሸከም አይችሉም፣ ነገር ግን ወተትን መቀበል አለባቸው፤ ስለዚህ እንዳይጠፉ እነዚህን ነገሮች ማወቅ የለባቸውም።

፳፫ ከእኔ ተማር፣ እናም ቃላቴን አድምጥ፤ በመንፈሴ በትህትና ተጓዝ፣ እናም በእኔ ሰላምን ታገኛለህ።

፳፬ እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ፣ በአብ ፈቃድ መጥቻለሁ፣ እናም ፈቃዱንም አደርጋለሁ።

፳፭ እናም ዳግም፣ የባልንጀራህን ሚስትም ሆነ የባልንጀራህን ህይወት እንዳትመኝ አዝሀለሁ።

፳፮ እናም ዳግም የራስህንም ንብረት እንዳትመኝ፣ ነገር ግን በለጋስነት እውነትን እና የእግዚአብሔርን ቃል የያዘውን መፅሐፈ ሞርሞንን ለማሳተሚያ ይሆን ዘንድ እንድትሰጥ አዝሀለሁ—

፳፯ ይህ ለአህዛብ የተሰጠ፣ እንዲሁ በቅርቡ ላማናውያን የእነርሱ ቅሪት በሆኑት አይሁዳውያን ወንጌልን ያምኑ ዘንድ እናም የመጣውን መሲህ ይመጣል ብለው እንዳይጠብቁ ወደእነርሱ የሚሄደው ቃሌ ነው።

፳፰ እናም ዳግም፣ ድምጽህን አውጥተህ፣ እንዲሁም በልብህ አዎን በአለም ፊት፣ እንዲሁም በስውር፣ በአደባባይ እንዲሁም በግል በድምጽ እንድትጸልይ አዝሀለሁ።

፳፱ እናም የምስራችን ቃል ታውጃለህ፣ አዎን፣ በተራራዎችም ላይ፣ እናም በሁሉም ከፍታ ስፍራዎች ላይ፣ እናም ልታያቸው በተፈቀደልህ ህዝብ መካከል ሁሉ ታውጃለህ

እናም፣ በእኔ በመታመን፣ ክፋትን ለሚናገሩህ ክፋትን ባለመናገር በሙሉ ትህትና ታደርገዋለህ።

፴፩ እናም የተወሳሰበ የቤተክርስቲያን ትምህርቶችን አትናገር፣ ነገር ግን ንስሀን እናም በአዳኛችን እምነትንበጥምቀት እናም በእሳት አዎን እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ኃጢአት እንደሚሰረይ አውጅ።

፴፪ እነሆ፣ ይህንን ነገር በተመለከተ የምሰጥህ ይህ ትልቅ እና የመጨረሻ ትእዛዝ ነው፤ ምክንያቱም ይህ ለዕለት ተዕለት እርምጃህ እስከ ህይወትህ ፍጻሜ በቂ ነው።

፴፫ እናም ይህንን ምክር ችላ የምትል ከሆነ ስቃይን ትቀበላለህ፣ አዎን፣ በአንተ እና በንብረትህ ላይ ቢሆን እንኳን ጥፋትን ትቀበላለህ።

፴፬ የንብረትህን ክፍል፣ አዎን፣ የምድርህን ክፍል ቢሆንም እንኳን፣ እናም ለቤተሰብህ ከሚያስፈልግህ በቀር ሁሉንም ንብረትህን ሽጥ

፴፭ ከአሳታሚው ጋር የገባኸውን ውል እዳ ክፈል። ከባርነት ራስህን ነፃ አውጣ።

፴፮ ቤተሰብህን ለማየት ስትፈልግ ካልሆነ በስተቀር ቤትህን እና መኖሪያህን ተው

፴፯ እናም በነፃነት ለሁሉም ተናገር፤ አዎን፣ በከፍተኛ ድምጽ ቢሆንም እንኳን፣ ሆሳዕና፣ ሆሳዕና፣ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን! በማለት ስበክ፣ ምከር፣ እውነትን አውጅ።

፴፰ ዘወትር ጸልይ፣ እናም መንፈሴን በአንተ ላይ አፈሳለሁ—አዎን፣ የምድርን ሀብት እናም የሚጠፋን ነገር ሁሉ ብታገኝም እንኳን በረከትህ ከዚህ የበለጠ ታላቅ ይሆናል።

፴፱ እነሆ፣ ሳትደሰት እና ልብህን ለደስታ ሳታነሳሳ ይህን ማንበብ አትችልምን?

ወይም እውር መሪ የሚሮጠውን ያህል መሮጥ አትችልምን?

፵፩ ወይም በጥበብ ራስህን በፊቴ ዝቅ ማድረግ እና ትሁት ማድረግ ትችላለህ? አዎን፣ ወደ እኔ ወደ አዳኝህ ። አሜን።