ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፷፰


ክፍል ፷፰

ህዳር ፩፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በሀይረም ኦሀዮ ውስጥ፣ ስለኦርሰን ሀይድ፣ ሉክ ኤስ ጆንሰን፣ ላይማን ኢ ጆንሰን፣ እና ውልያም ኢ መክለለን የጌታን ሀሳብ እንዲታወቅ በቀረበው ልመና መልስ አማካይነት በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ምንም እንኳን የዚህ ራዕይ ክፍል ለእነዚህ አራት ሽማግሌዎች የተሰጠ ቢሆንም፣ በውስጡ ያሉት አብዛኛዎቹ ለቤተክርስቲያኗ ሁሉ ተገቢ የሆኑ ናቸው። ይህ ራዕይ በ፲፰፻፴፭ (እ.አ.አ.) በትምህርት እና ቃል ኪዳን ቅጂ ውስጥ በታተመበት ጊዜ በጆሴፍ ስሚዝ አመራር ተስፋፍቶ ነበር።

፩–፭፣ ሽማግሌዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነሳስተው የተናገሩት ቅዱሳን መጻህፍት ናቸው፤ ፮–፲፪፣ ሽማግሌዎች ይስበኩ እናም ያጥምቁ፣ እናም በእውነት የሚያምኑትን ምልክቶች ይከተሏቸዋል፤ ፲፫–፳፬፣ ከአሮን ወንድ ልጆች መካከል በኩሩ በቀዳሚ አመራር ስር እንደ ኤጲስ ቆጶስ አመራር ያገለግላል (ይህም ማለት፣ እንደ ኤጲስ ቆጶስ የአመራር ቁልፎችን ይይዛል)፤ ፳፭–፳፰፣ ወላጆች ወንጌልን ለልጆቻቸው እንዲያስተምሩ ታዝዘዋል፤ ፳፱–፴፭፣ ቅዱሳን ሰንበትን ያክብሩ፣ በትጋት ይስሩ፣ እናም ይጸልዩ።

አገልጋዬ፣ ኦርሰን ሀይድ፣ በህያው እግዚአብሔር መንፈስ በኩል፣ ከህዝብ ወደ ህዝብ፣ ከምድር ወደ ምድር፣ በኃጢአተኞቹ ስብሰባዎች ውስጥ፣ በምኩራቦች ውስጥ፣ ምክንያቶችን በመስጠት እና ቅዱስ መጻህፍቶችን ሁሉ ለእነርሱ በማብራራት፣ ዘለአለማዊ ወንጌልን እንዲያውጅ በሹመት ተጠርቶ ነበር።

እናም፣ እነሆ፣ እና ተልዕኮአቸው እንዲሄዱ ለተወሰነላቸው፣ በክህነት ለተሾሙት ሁሉ ይህም ምሳሌ ነው—

እናም ይህም በመንፈስ ቅዱስ በመነሳሳት ለሚናገሩትም ምሳሌ ነው።

እናም በመንፈስ ቅዱስ ሲነሳሱ የሚናገሩት ማንኛውም ነገር ቅዱሳን መጻህፍት ይሆናሉ፣ የጌታ ፈቃድም ይሆናል፣ የጌታ አዕምሮም ይሆናል፣ የጌታ ቃል ይሆናል፣ የጌታ ድምጽ፣ እናም ለደህንነት የእግዚአብሔር ሀይልም ይሆናል።

እነሆ፣ አገልጋዮቼ ሆይ፣ ይህም ለእናንተ የተሰጠ የጌታ ቃል ኪዳን ነው።

ስለዚህ፣ ተደሰቱ፣ እናም አትፍሩ፣ እኔ ጌታ ከእናንተ ጋር ነኝና፣ እናም ከጎናችሁ እቆማለሁና፣ እና ስለ እኔም፣ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የህያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆንኩኝ፣ እስቀድሜም እንደነበርኩኝ፣ ህያውም እንደሆንኩኝ፣ እናም ዳግምም እንደምመጣ ትመሰክራላችሁ።

ይህም ለአንተ አገልጋዬ ኦርሰን ሀይድ፣ እናም ለአገልጋዬ ሉክ ጆንሰንም፣ እናም ለአገልጋዬ ላይመን ጆንሰንም፣ እና ለአገልጋዬ ውልያም ኢ መክለለንም፣ እናም ለቤተክርስቲያኔ ታማኝ ሽማግሌዎች ሁሉ የተሰጠ የጌታ ቃል ነው—

ወደአለም ሁሉ ሂዱ፣ ለእያንዳንዱም ፍጥረት፣ በሰጠኋችሁ ስልጣን እየሰራችሁ፣ በአብ፣ እና በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ወንጌልን ስበኩ

እናም የሚያምን እና የተጠመቀ ይድናል፣ እናም ያላመነ ግን ይፈረድበታል

እናም የሚያምነውም፣ እንደተጻፈው ይባረካል ምልክቶችም ይከተሉታል።

፲፩ እናም ለእናንተም የዘመኑን ምልክቶች፣ እናም የሰው ልጅ መምጫ ምልክቶች፣ ታውቁ ዘንድ ይሰጣችኋል፤

፲፪ እናም አብም የሚመሰክርላቸው ሁሉ፣ ለእናንተም እነርሱን ለዘለአለም የምታትሙባቸውን ሀይል ይሰጣችኋል። አሜን።

፲፫ እናም አሁን፣ ከቃል ኪዳኖች እና ከትእዛዛት በተጨማሪ ሌሎች ነገሮችን የሚመለከቱት፣ እነዚህ ናቸው—

፲፬ ጌታ በፈቀደ ጊዜ፣ እንደ መጀመሪያው ለማገልገል፣ ከዚህ በኋላ ለቤተክርስቲያኗ የሚሾሙ ሌሎች ኤጲስ ቆጶሳት አሉ፤

፲፭ ስለዚህ እነዚህም ብቁ የሆኑ ሊቀ ካህናት መሆን ይገባቸዋል፣ እናም፣ የአሮን እውነተኛ ተወላጆች ካለሆኑ በስተቀር፣ በመልከ ጼዴቅ ክህነት ቀዳሚ አመራር በኩልም ይሾማሉ።

፲፮ እናም እነርሱም የአሮን እውነተኛ ተወላጆች ሊሆኑ፣ ከአሮን ወንድ ልጆች በኩር ከሆኑ፣ ለኤጲስ ቆጶስ አመራርነት ህጋዊ መብት አላቸው፤

፲፯ በኩሩም በዚህ ክህነት የአመራር መብትን፣ እናም የዚህንም ቁልፎች ወይም ስልጣናት ይይዛልና።

፲፰ የአሮን እውነተኛ ተወላጅ እና በኩር ካልሆነ በስተቀር፣ ማንም ሰው ለዚህ ሀላፊነት፣ የዚህን ክህነት ቁልፎች ለመያዝ ህጋዊ መብት አይኖረውም።

፲፱ ነገር ግን፣ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ሊቀ ካህን በታናሾቹ ሀላፊነቶች ለማስተዳደር ስልጣን እንዳለው የአሮን እውነተኛ ተወላጅ እና በኩር በማይገኝበት ጊዜ፣ በመልከ ጼዴቅ ክህነት ቀዳሚ አመራር እጆች ስር ለዚህ ስልጣን ከተጠራ፣ እና ከተለየ እና ከተሾመ፣ በኤጲስ ቆጶስ ሀላፊነት ለማስተዳደር ይችላል።

እና፣ ደግሞም፣ የአሮን እውነተኛ ተወላጅም በዚህ ቀዳሚ አመራር መመረጥ፣ እና በብቃት መገኘት፣ እናም መቀባት፣ እናም በአመራሩ እጆች ስር መሾም አለባቸው፣ አለበለዚያ በክህነት ስልጣናቸው ለማስተዳደር ህጋዊ ስልጣን አይኖራቸውም።

፳፩ ነገር ግን፣ ከአባት ወደ ልጅ በሚወረሰው ክህነት መብትን በሚመለከት በታወጀው መሰረትም፣ ተወላጅነታቸውን በሚያረጋግጡበት ጊዜ፣ ወይም ከላይ በተጠቀሱት አመራር እጆች ስር በጌታ ራዕይ ካገኙ፣ መቀባታቸውን ለማረጋገጥ ይችላሉ።

፳፪ እና ደግሞም፣ ለዚህ አገልግሎት የተለየ፣ ማንም ኤጲስ ቆጶስ ወይም ሊቀ ካህን፣ በቤተክርስቲያኗ ቀዳሚ አመራር ፊት ካልሆነ በስተቀር፣ በወንጀል መኮነን ወይም ለፍርድ ሊቀርብ አይገባም፤

፳፫ እናም ጥርጣሬ በሌለው ምስክር በአመራሩ ፊት ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝ፣ ይፈረድበታል፤

፳፬ እናም ንስሀ ቢገባ፣ በቤተክርስቲያኗ ቃል ኪዳኖች እና ትእዛዛት መሰረት ይቅርታን ያገኛል።

፳፭ እና ደግሞም፣ ወላጆች በፅዮን፣ ወይም በተደራጁት ካስማዎቿ፣ ውስጥ ልጆች ኖሯቸው፣ ስምንት አመት ሲሆናቸው፣ ስለ ንስሀ፣ በህያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እምነት፣ እናም ስለ ጥምቀት እና እጆችን በመጫን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ስለመቀበል ትምህርትን ባያስተማሯቸውኃጢአቱ በወላጆች ራስ ላይ ይሆናል።

፳፮ ይህም ለፅዮን፣ ወይም በማንኛውም በተደራጁት ካስማዎቿ፣ ኗሪዎች ህግም ነውና።

፳፯ እናም ልጆቻቸውም ለኃጢአቶቻቸው ስርየት በስምንት አመታቸው ይጠመቁ፣ እናም የእጆችንም መጫን ይቀበሉ።

፳፰ እናም ልጆቻቸውን እንዲጸልዩም፣ እናም በጌታ ፊት በቅንነት እንዲራመዱም ያስተምሩ።

፳፱ እናም የፅዮን ኗሪዎችም የሰንበትን ቀን ያክብሩ፣ ይቀድሱትም።

እናም የፅዮን ኗሪዎችም፣ እንዲያገለግሉ እስከተጠሩ ድረስ፣ በሙሉ ታማኝነት አገልግሎታቸውንም ያስታውሱ፤ ስራ ፈት የሆነ እርሱ በጌታ ፊት ይታሰባልና።

፴፩ አሁን፣ እኔ ጌታ፣ በፅዮን ኗሪዎች አልተደሰትኩም፣ ስራ ፈቶች በመካከላቸው አሉና፤ እናም ልጆቻቸውም በኃጢአት ውስጥ እያደጉ ናቸውና፤ ለዘለአለማዊ ሀብትም በቅንነት አይሹም፣ ነገር ግን አይኖቻቸው በስግብግብነት ተሞልተዋል።

፴፪ እነዚህ ነገሮች መሆን አይገባቸውም፣ እናም ከመካከላቸው መወገድ አለባቸው፤ ስለዚህ፣ አገልጋዬ ኦሊቨር ካውድሪ እነዚህን አባባሎች ወደ ፅዮን ምድር ይውሰድ።

፴፫ እናም ትእዛዝም እሰጣቸዋለሁ—በትክክለኛው ጊዜ በጌታ ፊት ጸሎትን የማያከናውነው እርሱ፣ በህዝቤ ዳኛ ፊት ይታሰብ

፴፬ እነዚህ አባባሎች እውነተኛዎች እና የታመኑ ናቸው፤ ስለዚህ አትተላለፏቸው፣ ወይም አታጉድሏቸውም

፴፭ እነሆ፣ እኔ አልፋና ኦሜጋ ነኝ፣ እናም በቶሎ እመጣለሁ። አሜን።