ክፍል ፷፫
በነሀሴ ፴፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ነቢዩ፣ ስድኒ ሪግደን፣ እና ኦሊቨር ካውድሪ በነሀሴ ፳፯ ከሚዙሪ ጉዞአቸው ወደ ከርትላንድ ደርሰው ነበር። የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ ይህን ራዕይ እንዲህ በማለት ገልጿል፥ “ቤተክርስቲያኗ አዲስ በሆነችበት በእነዚህ ቀናት፣ ደህንነታችንን በሚመለከት ከጌታ ቃልን ለማግኘት ታላቅ ጉጉት ነበር፤ እናም አሁን የፅዮን ምድርን በሚመለከት የጊዜው አሳሳቢጉዳይ ስለነበር፣ ስለ ቅዱሳን መሰባሰብ እና መሬቶችን ስለመገዛት እና ስለ ሌሎች ጉዳዮች ከጌታ ተጨማሪ መረጃዎችን ጠየቅሁ።”
፩–፮፣ በኃጢአተኞች ላይ የቁጣ ቀን ይመጣል፤ ፯–፲፪፣ ምልክቶች በእምነት አማካይነት ይመጣሉ፤ ፲፫–፲፱፣ በልባቸው የሚያመነዝሩ እምነትን ይክዳሉ እናም ወደ እሳቱ ባሕር ይጣላሉ፤ ፳፣ የታመኑ በክብር በተለወጠችው ምድር ውርሳቸውን ይቀበላሉ፤ ፳፩፣ በክብር የመለወጥ ተራራ ላይ የነበረው ሙሉ ታሪክ ገና አልተገለጡም፤ ፳፪–፳፫፣ ታዛዡ የመንግስትን ሚስጥራት ይቀበላል፤ ፳፬–፴፩፣ የፅዮን ውርሶች ይገዙ፤ ፴፪–፴፭፣ ጌታ ጦርነቶችን አውጇል፣ እናም ኃጢአተኛ ኃጢአተኛውን ይገድላል፤ ፴፮–፵፰፣ ቅዱሳን ወደ ፅዮን ይሰባሰባሉ እናም ይህን ለመገንባትም ገንዘብ ይስጡ፤ ፵፱–፶፬፣ ለታማኞቹ በትንሳኤ፣ እና በአንድ ሺህ ዘመን ዳግም ምፅአት በረከቶች ተረጋግጠውላቸዋል፤ ፶፭–፶፰፣ ይህም የማስጠንቀቂያ ቀን ነው፤ ፶፱–፷፮፣ ያለስልጣን በሚጠቀሙት ዘንድ የጌታ ስም በከንቱ ይጠራል።
፩ አድምጡ፣ እናንት ህዝብ ሆይ፣ እናም ልባችሁን ክፈቱ እናም ከሩቅም ስሙ፤ እናም፣ ራሳችሁን የጌታ ህዝብ ብላችሁ የምትጠሩትም ስሙ፣ እናም እናንተን በሚመለከት የጌታን ቃል እና ፍላጎት አድምጡ።
፪ አዎን፣ እውነትም እላለሁ፣ በኃጢአተኛው እና ሀበአመጸኛው ላይ የተቀጣጠለውንም የቁጣውን ቃል አድምጡ፤
፫ ለመውሰድ የሚፈልገውን ሀይወስዳል፣ እና ለማዳን የሚፈልገውንም በህይወት ያድናል፤
፬ እንደራሱ ፈቃድ እና ደስታም ይገነባል፤ እናም የፈለገውንም ያጠፋል፣ እናም ነፍስንም ወደ ገሀነም ይጥል ዘንድ ይቻለዋል።
፭ እነሆ፣ እኔ ጌታ ድምጼን አሰማለሁ፣ እና ይህም ይከበራል።
፮ ስለዚህ፣ በእውነት እላለሁ፣ ኃጢአተኛው ያድምጥ፣ እናም አመጸኛውም ይፍራ እናም ይንቀጥቀጥ፤ እናም የማያምኑትም ከንፈሮቻቸውን ይያዙ፣ እንደ ሀአውሎ ነፋስ ለየቁጣው ቀን ይመጣባቸዋልና፣ እናም ስጋ ለባሽ ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩኝም ሐያውቃሉ።
፯ እናም ምልክቶችን የሚሻ ሀምልክቶችን ያገኛል፣ ነገር ግን ለደህንነት አይሆንለትም።
፰ እውነት እላችኋለሁ፣ በመካከላችሁ ምልክቶችን የሚሹ አሉ፣ እናም እንደነዚህ አይነቶችም ከመጀመሪያ ጀምሮም ነበሩ።
፱ ነገር ግን፣ እነሆ፣ እምነት በምልክቶች አይመጣምና፣ ነገር ግን ምልክቶች የሚያምኑትን ይከተሏቸዋል።
፲ አዎን፣ ምልክቶች የሚመጡት ሀበእምነት ነው፣ በሰዎች ፈቃድ ወይም ፍላጎት ሳይሆን፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።
፲፩ አዎን፣ ምልክቶች ታላቅ ስራዎች ይሆኑ ዘንድ ሀበእምነት ይመጣሉ፣ ምክንያቱም ያለ እምነት ማንም ሰው እግዚአብሔርን ሊያስደስት አይችልምና፤ እናም እግዚአብሔር የተቆጣበት በእርሱም አይደሰትም፤ ስለዚህ፣ ለእንደእነዚህ አይነቶች፣ ለበቁጣ ሐከእርግማን በቀር፣ ምንም ምልክቶችን አያሳይም።
፲፪ ስለዚህ፣ እኔ ጌታ፣ በመካከላችሁ ለእምነት ምልክቶችን እና ድንቆችን ለሰዎች ጥቅም እና ለክብሬ ሳይሆን ለፈቃዳቸው በሚሹ ላይ አልተደሰትኩም።
፲፫ ይሁን እንጂ፣ ትእዛዛትን ሰጥቻለሁ፣ እናም ብዙዎችም ከትእዛዛቴ ፈቀቅ ብለዋል እናም አልጠበቋቸውም።
፲፬ በመካከላችሁም ሀዘማዊ እና ዘማዊት ነበሩ፤ አንዳንዶቹም ከእናንተ ተለይተዋል፣ እናም ከዚህ በኋላ የሚገለጡት ሌሎቹም ከእናንተ ጋር ቀርተዋል።
፲፭ እንደዚህ አይነቶቹ ይጠንቀቁ እናም ፈጥነውም ንስሀ ይግቡ፣ አለበለዚያም ፍርድ እንደ አጥማጅ ይመጣባቸዋል፣ እናም ሞኝነታቸውም በግልፅ ይታያል፣ እናም በህዝብ አይኖች ውስጥ ስራዎቻቸውም ይከተሏቸዋል።
፲፮ እናም፣ አስቀድሜ እንደተናገርሁ፣ በእውነት እንዲህ እላችኋላሁ፣ ሴትን ሀየተመለከተ እናም ለየተመኛትም፣ ወይም ማናቸውም በልባቸው ሐቢያመነዝሩ፣ መንፈስም አይኖራቸውም፣ ነገር ግን እምነትን ይክዳሉ እናም ይፈራሉ።
፲፯ ስለዚህ፣ እኔ ጌታ እንዳልኩት፣ ሀየሚፈሩና የማያምኑ፣ እናም ለየሐሰተኞችም ሁሉ፣ እናም ሀሰትን የሚወዱ እና ሐየሚዋሹ፣ እና የሴሰኞችም፣ እና የአስማተኞችም፣ እና ጣዖትንም የሚያመልኩ፣ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል መባሕር ነው፤ ይኸውም ሠሁለተኛው ሞት ነው።
፲፰ በእውነት አላለሁ፣ እነርሱ ሀበመጀመሪያው ትንሳኤ ስፍራ አይኖራቸውም።
፲፱ እናም አሁን እነሆ፣ እኔ ጌታ እንዲህ እላችኋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች በመካከላችሁ ስላሉ፣ ሀትጸድቁ ዘንድ አይቻላችሁም።
፳ ይሁን እንጂ፣ በእምነት ሀየጸናው እና ፈቃዴንም የሚያደርገው፣ እርሱ ያሸንፋል፣ እናም በክብር የመለወጥ ቀን ሲመጣም ለውርሱን ይቀበላል
፳፩ እንዲሁም፣ ሙሉ ታሪኩን ገና ያልተቀበላችሁትን፣ ለሐዋሪያቴ ሀበተራራው ላይ ባሳየሁት ስርዓት ለምድር ሐበክብር ስትለወጥም፣ ውርሱን ይቀበላል።
፳፪ እናም አሁን፣ በእውነት እላችኋላሁ፣ እንደተናገርኳችሁ ፈቃዴን አሳውቃችኋለሁ፣ እነሆ እንድታውቁትም አደርጋለሁ፣ ይህም በትእዛዝ አይደለም ምክንያቱም ትእዛዛቴን የማያከብሩ ብዙዎች አሉና።
፳፫ ነገር ግን ትእዛዛቴን ለሚጠብቀው ለእርሱ የመንግስቴን ሀሚስጥራት እሰጠዋለሁ፣ እና በእርሱም ውስጥ ለዘለአለም ሕይወት ለየሚፈልቅ ሐየህያው ውኃ ምንጭ ይሆናል።
፳፬ እናም አሁን፣ እነሆ ይህም ጌታ አምላካችሁ ለቅዱሳኑ ያለው ፍላጎት ይህ ነው፣ ቸነፈር የሚያመጣው ግራ መጋባት እንዳይኖር፣ በፍጥነት ሳይሆን፣ በፅዮን ምድር ራሳቸውን ይሰብስቡ።
፳፭ እነሆ፣ ሀየፅዮንን ምድር—እኔ ጌታ በእጆቼ ይዣታለሁ፤
፳፮ ይሁን እንጂ፣ እኔ ጌታም ሀየቄሣርን ለቄሣር አስረክቤአለሁ።
፳፯ ስለዚህ፣ እኔ ጌታ በአለም ትጠቀሙ ዘንድ፣ በአለምም የእኛ ነው የምትሉት እንዲኖራችሁ፣ እነርሱም በቁጣም እንዳይነሳሱባቸው፣ መሬቶች እንድትገዙ ፍቃዴ ነው።
፳፰ ሀሰይጣንም፣ ደምን እስከማፍሰስ ድረስም፣ እንዲያስቆጣቸው በልቦቻቸው ውስጥ ቁጣን ያነሳሳል።
፳፱ ስለዚህ፣ የፅዮን ምድርም በመግዛት ወይም በደም በስተቀር አይገኝም፣ አለበለዚያም ለእናንተ ምንም ውርስ የላችሁም።
፴ እና በመግዛትም ቢሆን፣ እነሆ የተባረካችሁ ናችሁ፤
፴፩ እናም በደምም ቢሆን፣ ደምን ለማፍሰስ ስለተከለከላችሁ፣ እነሆ፣ ጠላቶቻችሁ ያጠቋችኋል፣ እናም ከከተማ ወደ ከተማም፣ ከምኩራብ ወደ ምኩራብ ትቀጣላችሁ፣ እናም ውርስን ለመቀበል ጥቂቶች ብቻ ይቀራሉ።
፴፪ እኔ ጌታም በኃጢአተኞቹ ተቆጣሁ፤ መንፈሴንም ከምድር ኗሪዎች እከለክላለሁ።
፴፫ በቁጣዬም ማልሁ፣ እናም በምድርም ፊት ላይ ሀጦርነቶችን አወጅኩኝ፣ እናም ኃጢአተኛውም ኃጢአተኛውን ይገድላል፣ እናም ፍርሀትም በእያንዳንዱ ሰው ላይ ይመጣል፤
፴፬ እናም ሀቅዱሳንም ደግመው አያመልጡም፤ ይሁን እንጂ፣ እኔ ጌታ ከእነርሱ ጋር ነኝ፣ እና ከአባቴ ፊትም ከሰማይ ለእወርዳለሁ እናም ሐኃጢአተኞቹንም በማይጠፋ መእሳት አነዳቸዋለሁ።
፴፭ እናም እነሆ፣ ይህም ገና አይደለም፣ ነገር ግን በቅርቡ የሚሆን ነው።
፴፮ ስለዚህ፣ በምድር ላይ እነዚህን ነገሮች ሁሉ እኔ ጌታ በማወጄ ምክንያት፣ የእኔ ቅዱሳን ራሳቸውን በፅዮን ምድር መሰብሰባቸው ፍቃዴ ነው፤
፴፯ እናም እያንዳንዱ ሰው ሀፅድቅን በእጆቹ እና ታማኝነትን በወገቡ ይውሰድ፣ እናም የማስጠንቀቂያ ለድምፅም ወደ ምድር ኗሪዎች ይሰማ፤ እናም በቃል እና ፈጥኖ በመሄድ በስደት በኃጢአተኞች ላይ ሐክፉ ነገሮች እንደሚመጡ ይገለጹ።
፴፰ ስለዚህ፣ በከርትላንድ ውስጥ በዚህ እርሻ የሚኖሩት ደቀ መዛሙርቴ የስጋዊ ጉዳያቸውን ያዘጋጁ።
፴፱ አገልጋዬ ታይተስ ቢሊንግስ፣ በሚመጣው ጸደይ፣ ትእዛዝ እስከምሰጣቸው ድረስ ከማይሄዱት ለራሴ ከምጠብቃቸው በስተቀር በዚህ ስፍራ ከሚኖሩት ጋር፣ ወደ ፅዮን ምድር ለመጓዝ መዘጋጀት እንዲችል፣ ሀላፊነት ያለበትን መሬትን ይሽጥ።
፵ እናም የሚቀረውም ገንዝብ ሁሉ፣ ብዙም ይሁን ጥቂት ግድ የለኝም፣ ወደ ፅዮን ምድር እንዲቀበሉ ለሾምኳቸው ይላክ።
፵፩ እነሆም እኔ ጌታ፣ ለአገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ ወደ ፅዮን ምድር የሚሄዱትን፣ እና በዚህም የሚቀሩትን ደቀ መዛሙርቴን ሀለመለየት የሚያስችለውን ሀይል እሰጠዋለሁ።
፵፪ እናም አገልጋዬ ኒውል ኬ ውትኒ የግምጃ ቤቱን፣ ወይም በሌላ ቃላት፣ የግምጃ ቤቱን በትንሽ ወቅት እንደያዘ ይቀጥል።
፵፫ ይሁን እንጂ፣ ለመስጠት የሚችለውን ገንዘብ ሁሉ ወደ ፅዮን ምድር እንዲላክ ይስጥ።
፵፬ እነሆ፣ እነዚህ ነገሮች በእጆቹ ውስጥ ናቸው፣ በጥበብም ያድርጋቸው።
፵፭ በእውነትም እላለሁ፣ ለሚቀሩትም ደቀ መዛሙርት ወኪል እንዲሆንም ይሾም፣ እናም ለዚህ ሀይልም ይሾም፤
፵፮ እናም አሁን፣ ከአገልጋዬ ኦሊቨር ካውድሪ ጋር፣ እነዚህን ነገሮች በማብራራት፣ ፈጥኖም ቤተክርስቲያኖችን ይጎብኝ። እነሆ፣ ገንዘብን እንደመራሁት ማግኘቱ ፍቃዴ ነው።
፵፯ ሀታማኝ የሆነው እና የሚጸናውም አለምን ያሸንፋል።
፵፰ ወደ ፅዮን ምድር ሀብትን የላከው በዚህ አለም ሀውርስን ይቀበላል፣ እናም ስራዎቹ ይከተሉታል፣ እናም በሚመጣው አለምም ዋጋው ይሰጠዋል።
፵፱ አዎን፣ እናም፣ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ ሀየሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው፣ ጌታ ሲመጣም፣ እና አሮጌው ነገሮች ለአልፈው፣ እናም ሁሉም ነገሮች አዲስ ሲሆኑም፣ ከሞት ሐይነሳሉ እናም ከዚህም በኋላ መአይሞቱምና፣ እናም በቅዱስ ከተማውም ከጌታም ውርስን ይቀበላሉ።
፶ እናም ጌታ ሲመጣ የሚኖረው፣ እና ሀይማኖትን የጠበቀውም፣ እርሱ ሀየተባረከ ነው፤ ይሁን እንጂ በሰው እድሜ ለእንዲሞትም ተወሰኖለታል።
፶፩ ስለዚህ፣ ልጆች እድሜአቸው እስኪገፋ ድረስም ሀያድጋሉ፤ ሽማግሌዎችም ይሞታሉ፤ ነገር ግን በምድርም ትቢያ ውስጥ አያንቀላፉም፣ ነገር ግን በቅጽበት ዓይንም ለይለወጣሉ።
፶፪ ስለዚህ፣ ለዚህም ምክንያት ነው ሀዋሪያት ለአለም ስለሙታን ትንሳኤ የሰበኩት።
፶፫ እነዚህ ነገሮች ወደፊት መመልከት ያለባችሁ ነገሮች ናቸው፤ እናም፣ እንደ ጌታ አነጋገር፣ እናም በሚመጣው ጊዜም፣ እንዲሁም በሰው ልጅ ምፅዓት ቀን፣ አሁንም ሀቀርቧልና።
፶፬ እናም እስከዚያም ሰአት ድረስ በብልህ መካከል ሰነፎች ሀደናግል ይኖራሉ፤ እናም በዚያም ሰዓት ጻድቃን ከኃጢአተኞቹ ሁሉ የሚለዩበት ይመጣል፤ እናም በዚያም ቀን ኃጢአተኞቹን ለነቅለው እንዲያወጡ እና በማይጠፋው እሳት ውስጥ እንዲወረውሯቸው መላእክቴን እልካለሁ።
፶፭ እናም አሁን እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እኔ ጌታ በአገልጋዬ ሀስድኒ ሪግደን አልተደሰትኩም፤ በልቡም ራሱን ለከፍ ከፍ ያደርጋል፣ እናም ምክርንም አልተቀበለምና፣ ነገር ግን መንፈስንም አሳዝኗል፤
፶፮ ስለዚህ የእርሱ ሀፅሑፍ በጌታ ዘንድ ተቀባይነት የለውም፣ እናም ሌላም ይጻፍ፤ እናም ጌታ ይህን ካልተቀበለውም፣ እነሆ በሾምኩበት ሹመትም አይቆምም።
፶፯ እና ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በየዋህነት ኃጢአተኞችን ንስሀ እንዲገቡ ሀለማስጠንቀቅ በልቦቻቸው ፍላጎት ለያላቸው፣ በዚህ ሀይልም ይሾሙ።
፶፰ ይህም፣ የብዙ ቃላት ቀን ሳይሆን፣ የማስጠንቀቂያ ቀን ነውና። እኔ ጌታም በመጨረሻዎቹ ቀናት ውስጥ አይዘበትብኝምና።
፶፱ እነሆ፣ እኔም ከበላይ ነኝ፣ እናም በበታችም ሀይሌ ይኖራል። ከሁሉም በላይ፣ እና በሁሉም የምሰራ፣ እናም በሁሉም የምኖር ነኝ፣ እናም ሁሉንም ሀእመረምራለሁ፣ እናም ሁሉም ነገሮች ለእኔ ተገዢ የሚሆኑበትም ቀን ይመጣል።
፷ እነሆ፣ እኔ ሀአልፋና ኦሜጋ፣ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ነኝ።
፷፩ ስለዚህ፣ ሁሉም ሰዎች እንዴት ሀስሜን በከንፈሮቻቸው እንደሚይዙ ይጠንቀቁ—
፷፪ ምክንያቱም እነሆ፣ እውነት እላለሁ፣ የጌታን ስም በከንቱ የሚጠቀሙ፣ እናም ያለስልጣን የሚጠሩ፣ በዚህ እርግማን ውስጥ ያሉ ብዙዎች አሉ።
፷፫ ስለዚህ፣ ቤተክርስቲያን ለኃጢአታቸው ንስሀ ይግቡ፣ እናም እኔ ጌታ የእኔ አደርጋቸዋለሁ፤ አለበለዚያም ይቆረጣሉ።
፷፬ ከላይ የሚመጣውእርሱ ሀቅዱስ እንደሆነ፣ እናም በጥንቃቄ እና በመንፈስም ቁጥጥር ለመነገር እንዳለበትም አስታውሱ፤ እና በዚህም ውስጥ እርግማን የለም፣ እናም መንፈሱን የምትቀበሉት በጸሎት ሐበኩል ነው፤ ስለዚህ፣ ይህ ባይሆን በእርግማን ይቀራሉ።
፷፭ ሀበጸሎት በመንፈስ እንደተማሩት፣ አገልጋዮቼ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ እና ስድኒ ሪግደን ቤትን ይፈልጉባቸው።
፷፮ እነዚህ ሀከሁሉም ይልቅ የዘለአለም ለክብርን፣ አለበለዚያም ታላቅን እርግማን፣ ይቀበሉ ዘንድ፣ እነዚህንም ነገሮች በትዕግስት ማሸነፍ ይቻል ዘንድ ነውና። አሜን።