ክፍል ፻፴
በሚያዝያ ፪፣ ፲፰፻፵፫ (እ.አ.አ.) በራመስ ኢለኖይ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጡ የመመሪያ ነገሮች።
፩–፫፣ አብና ወልድ ለሰዎች በግል ሊገለጡ ይችላሉ፤ ፬–፯፣ መላዕክት በሰለስቲያል አለም ውስጥ ይኖራሉ፤ ፰–፱፣ ሰለስቲያላዊ ምድር ታላቅ ኡሪምና ቱሚም ትሆናለች፤ ፲–፲፩፣ ወደ ሰለስቲያል አለም ለሚገቡት ሁሉ ነጭ ድንጋይ ተሰጥቷል፤ ፲፪–፲፯፣ የዳግም ምፅዓት ጊዜ ከነቢያት ተሰውሯል፤ ፲፰–፲፱፣ በዚህ ህይወት የተገኘው የመረዳት ችሎታ በትንሳኤ ጊዜ አብሮን ይነሳል፤ ፳–፳፩፣ ሁሉም በረከቶች ህግን በማክበር ይመጣሉ፤ ፳፪–፳፫፣ አብና ወልድ የስጋ እና አጥንት አካል አላቸው።
፩ አዳኛችን በሚገለጥበት ጊዜ እርሱ እንዳለ ሀእናየዋለን። እርሱም እንደ እኛው ለሰው እንደሆነም እናያለን።
፪ እና በዚህ በመካከላችን የሚገኘው ማህበራዊ ግንኙነት፣ አሁን የማናገኘውን ነገር ግን ሀዘለአለማዊ ክብር ተጨምሮበት፣ በዚያም እናገኘዋለን።
፫ ዮሐንስ ፲፬፥፳፫—በዚያ አንቀፅ ውስጥ ሀየአብ እና ለየወልድ መገለጥ፣ በተናጠል ሐየታዩበት ነው፤ እና አብ እና ወልድ በሰው ልብ ውስጥ መያድራሉ የሚለው አስተሳሰብ የድሮ የሀይማኖት ቡድኖች ሀሳብ ነው፣ እና ሀሰትም ነው።
፬ የእግዚአብሔር ሀጊዜ፣ የመላዕክት ጊዜ፣ የነቢያት ጊዜ፣ እና የሰው ጊዜ አቆጣጠር እንደየሚኖሩበት ፕላኔት መሰረት አይደለም?—የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ
፭ አዎን ብዬም እመልሳለሁ። ነገር ግን ከዚህ ምድር የሆኑ ወይም የነበሩ ካልሆኑ በስተቀር፣ የሚያገለግሉ ሀመላዕክት አይኖሩም።
፮ መላእክት ይህን ምድር በሚመስል ፕላኔት አይኖሩም።
፯ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት፣ በመስታወት እና ሀእሳት ለባህር አለም ላይ፣ ሁሉም ነገሮች ጥንት፣ አሁን፣ እና ወደ ፊት ለክብራቸው በሚገለጥበት፣ እና ይህም በጌታ ፊት በሚቀጥልበት ሁኔታ ይኖራሉ።
፰ እግዚአብሔር የሚኖርበት ስፍራ ታላቅ ሀኡሪምና ቱሚም ነው።
፱ ሀምድር፣ በተቀደሰበት እና ዘለአለማዊ ሁኔታ በጥራት ትሰራለች እና በውስጧም ለሚኖሩት እንደ ኡሪምና ቱሚም ትሆናለች፣ በዚህም የዝቅተኛውን መንግስት፣ ወይም የታችኛው ስርዓት መንግስታትን ሁሉ በሚመለከት ነገሮች ሁሉ በእዚያ ለሚኖሩበት ይገለጥላቸዋል፤ እና ይህች ምድርም የክርስቶስ ትሆናለች።
፲ ከዚያም በራዕይ ፪፥፲፯ ውስጥ የተጠቀሰው ነጭ ድንጋይም አንድ ለሚቀበለው ለእያንዳንዱ ሰው የመንግስት ከፍተኛውን ስርዓትን የሚመለከቱ ነገሮችን እንዲያውቁባቸው የሚደረግበት ኡሪምና ቱሚም ይሆናል፤
፲፩ እና ወደ ሰለስቲያል መንግስት ለሚመጡትም ከሚቀበሉት በስተቀር ማንም የማያውቀው አዲስ ሀስም የሚጻፍበት ለነጭ ድንጋይ ለእያንዳንዱ ተሰጥቷል። አዲሱ ስምም እንደቁልፍ የሆነ ቃል ነው።
፲፪ የሰው ልጅ ከመምጣቱ በፊት ብዙ ደም መፋሰስን የሚያስከትሉ ሀችግሮች የሚጀምሩት ለበደቡብ ኬሮላይና እንደሆነ በጌታ አምላክ ስም እተነብያለሁ።
፲፫ ይህም ምናልባት በባሪያ ጥያቄ ይነሳ ይሆናል። በታህሳስ ፳፭፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) ስለዚህ ርዕስ በቅንነት እየጸለይኩ ሳለሁ፣ ይህን ድምፅ አወጀልኝ።
፲፬ በአንድ ወቅት የሰውን ልጅ ሀየምጻት ጊዜ ለማወቅ በቅንነት ስጸልይ ነበር፣ ድምፅም የሚከተለውን ሲደጋግም የሰማሁት፥
፲፭ ልጄ ጆሴፍ፣ ሰማንያ አምስት አመት እስኪሆንህ ብትኖር፣ የሰውን ልጅ ፊት ለማየት ትችላለህ፤ ስለዚህ ይህ ይብቃህ፣ እናም በዚህም ጉዳይ ከዚህ በላይ አታስቸግረኝ።
፲፮ ይህ የተጠቀሰው ምጽአት ስለአንድ ሺህ ዘመን መጀመሪያ ይሁን ወይም ከዚህ በፊት የሆነ መገለጥ ወይም መሞት እንዳለብኝ እና በዚህም ፊቱን የማይ እንደሆነም ለመወሰን ባለመቻል እንደዚህም ተትቼ ነበር።
፲፯ የሰው ልጅ መምጫ ከዚህ ጊዜ በፊት ቀድሞም እንደማይሆን አምናለሁ።
፲፰ በዚህ ህይወት የምናገኘው ማንኛውም ሀየመረዳት ችሎታ መሰረታዊ መርህ፣ ይህም ለከሞት ስንነሳ አብሮን ይነሳል።
፲፱ እና አንድ ሰው ሀበትጋቱ እና ለበታዛዥነቱ ከሌላው ሰው በላይ ተጨማሪ ሐእውቀትን እና የመረዳት ችሎታን በዚህ ህይወት ቢያገኘ፣ በሚመጣው አለምም ውስጥ በበለጠ መየተሻለ ሁኔታ ይኖረዋል።
፳ ይህ አለም ከመመስረቱ ሀአስቀድሞ ሁሉም ለበረከቶች የሚመረኮዙበት በሰማያት ውስጥ ሊሻር የማይችል የታወጀ ሐህግ አለ—
፳፩ እና የትኛውንም በረከት ከእግዚአብሔር ስናገኝ፣ ሁሉም ነገር በተመረኮዘበት ለዚያ ህግ ታዛዥ በመሆን ነው።
፳፪ ሀአብ እንደ ሰው ሊዳሰስ እና ሊጨበጥ የሚችል የስጋ እና አጥንት ለአካል አለው፤ ወልድም ደግሞ እንዲሁ ነው፣ ነገር ግን ሐመንፈስ ቅዱስ የስጋ እና አጥንት አካል የለውም፣ ነገር ግን የመንፈስ አካል ነው። ይህ ባይሆን ኖሮ፣ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ለመኖር ባልቻለ ነበር።
፳፫ ሰው ሀመንፈስ ቅዱስን ሊቀበል ይችላል፤ እና በላዩም ሊወርድበትና አብሮትም ላይቆይ ይችላል።