ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፬


ክፍል ፬

የካቲት ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ ፔንስልቬንያ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ለአባቱ ለጆሴፍ ስሚዝ ቀዳማዊ የተሰጠ ራዕይ።

፩–፬፣ የጌታን አገልጋዮች የጀግና አገልግሎት ያድናቸዋል፤ ፭–፮፣ አምላካዊ ባህሪያት ላገልግሎቱ ብቁ ያደርጋቸዋል፤ ፯፣ የእግዚአብሔር ነገሮች መሻት አለባቸው።

፩ አሁን እነሆ፣ በሰዎች ልጆች መካከል ድንቅ ስራ ሊመጣ ነው።

፪ ስለዚህ እናንት በእግዚአብሔር አገልግሎት ውስጥ መሳተፍ የጀመራችሁ፤ በመጨረሻው ቀን በእግዚአብሔር ፊት ያለወቀሳ ትቆሙ ዘንድ፣ በሙሉ ልባችሁ፤ ኃይላችሁ፣ አዕምሮአችሁ እና ጉልበታችሁ እንደምታገለግሉት አረጋግጡ።

፫ ስለዚህ፣ እግዚአብሔርን ለማገልገል ፈቃድ ካላችሁ ወደስራው ተጠርታችኋል፤

፬ ስለሆነም እነሆ እርሻው ነጥቷል አዝመራውም ዝግጁ ነው፤ እናም አስተውሉ፣ በጥንካሬው የሚያጭድ እንዳይጠፋ ዘንድ በጎተራው ይከምራል፣ ነገር ግን ለነፍሱ ደህንነትን ያመጣል፤

፭ እናም እምነት፣ ተስፋ፣ ለጋስነትና ፍቅር፣ ሙሉ አይኑን ወደ እግዚአብሔር ክብር ከማድረግ ጋር ለስራ ብቁ ያደርጉታል።

፮ እምነት፣ ምግባረ በጎነት፣ ዕውቀት፣ ራስን መግዛት፣ ትዕግስት፣ ወንድማዊ ደግነት፣ አምላካዊነት፣ ልግስና፣ ትህትና፣ ትጋትን አስታውሱ።

፯ ለምኑ፣ እናም ይሰጣችኋል፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል። አሜን።