ክፍል ፳፭
ሐምሌ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ ፔንስልቫኒያ በጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት የተሰጠ ራዕይ። (የክፍል ፳፬ ርዕስን ተመልከቱ)። ይህ ራዕይ ጌታ ለነቢዩ ሚስት ለኤማ ስሚዝ ያለውን ፈቃድ ይገልጣል።
፩–፮፣ ኤማ ስሚዝ፣ ባለቤቷን ለመርዳት እና ለማጽናናት የተጠራች የተመረጠች ሴት ነች፤ ፯–፲፩፣ እንዲሁም ለመጻፍ፣ ቅዱሳን መጻህፍትን ለማብራራት እና መዝሙሮችን ለመምረጥ ተጠርታለች፤ ፲፪–፲፬፣ የጻድቃን መዝሙር ለጌታ ጸሎት ነው፤ ፲፭–፲፮፣ በዚህ ራዕይ ውስጥ ያሉት የታዛዥነት መሰረታዊ መርሆች በሁሉም ዘንድ ተፈጻሚዎች ናቸው።
፩ ለአንቺ እየተናገርኩ ሳለ፣ ልጄ ኤማ ስሚዝ፣ የጌታ አምላክሽን ድምጽ አድምጪ፤ እውነት እልሻለሁ፣ ወንጌሌን ሀየሚቀበሉ ሁሉ ለበመንግስቴ ወንድ እና ሴት ልጆች ናቸው።
፪ ፈቀዴን በተመለከተ ራእዬን እሰጥሻለሁ፤ ታማኝ ከሆንሽ እና ሀበምግባረ በጎነት መንገድ በፊቴ ለየምትጓዢ ከሆነ፣ ህይወትሽን እጠብቀዋለሁ እናም በፅዮን ሐርስትን ትቀበያለሽ።
፫ እነሆ፣ ሀኃጢአቶችሽ ተሰርየውልሻል፣ እናም እኔ ለየጠራሁሽ አንቺ የተመረጥሽ ሴት ነሽ።
፬ ስላላየሻቸው ነገሮች አታጉረምርሚ፣ ከአንቺ እና ከአለም ታግደዋል፣ ይህም ወደፊት በሚመጣው በእኔ ዘንድ ጥበብ ነው።
፭ የጥሪሽ ሀላፊነት ለባለቤትሽ ለአገልጋዬ ለጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ በመከራው ወቅት በአበረታች ቃላት፣ በትህትና መንፈስ፣ በመስጠት ሀመጽናኛው እንድትሆኚው ነው።
፮ እናም በሚሄድበት ጊዜ አብረሽው ትሄጂያለሽ፣ እናም አገልጋዬን ኦሊቨር ካውድሪን ወደፈቀድኩበት ስፍራ እልከው ዘንድ፣ የሚጽፍለት ሰው ሳይኖር ለእርሱም ጸሀፊም ትሆኛለሽ።
፯ ቅዱሳን መጻህፍትን ለማብራራት እናም መንፈሴ እንደሰጠሽ ቤተክርስቲያኗን ታበረታቺ ዘንድ፣ በእርሱም እጅ ሀትሾሚያለሽ።
፰ ሀእጁንም በራስሽ ላይ ይጭናል እናም መንፈስ ቅዱስን ትቀበያለሽ፣ እናም ጊዜሽ ለመጻፍ እና ብዙ ለመማር የተሰጠ ይሆናል።
፱ እናም ባለቤትሽ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለሚረዳሽ መፍርሀት የለብሽም፤ እንደ እምነታቸው፣ እንደ ፈቃዴ፣ ሁሉም ነገሮች ሀይገለጡላቸው ዘንድ፣ የእርሱ ለጥሪ ለእነርሱ ነው።
፲ እናም እውነት እልሻለሁ የዚህን ሀአለም ለነገሮች ወደጎን ትተያቸዋለሽ እናም የተሻሉ ነገሮችን ሐትሺያለሽ።
፲፩ እናም እንዲሁም፣ በቤተክርስቲያኔ ውስጥ መኖራቸው ይህም ስለሚያስደስተኝ፣ እንደሚሰጥሽም መጠን የተቀደሱ ሀመዝሙሮችን ትመርጪ ዘንድ ይሰጥሻል።
፲፪ ሀከልብ ከሆነ ለዝማሬ ነፍሴ ትደሰታለችና፣ አዎን የጻድቅን መዝሙር በእኔ ዘንድ ጸሎት ነው፣ በረከትንም በራሳቸው ላይ በማድረግ ይመለስላቸዋልና።
፲፫ ልብሽን አቅኚ እናም ተደሰቺ፣ እና ከገባሽውም ቃል ኪዳን ጋርም ተጣበቂ።
፲፬ ሀበትህትና መንፈስ ቀጥዪ፣ እናም ለከትዕቢትም ተጠበቁ። ነፍስሽ በባልሽ እናም በእርሱ ላይ በሚመጣው ክብር ሀሴትን ታድርግ።
፲፭ ዘወትር ትእዛዛቴን ጠብቂ፣ እናም ሀየጽድቅ ለአክሊልን ትቀበያለሽ። ይህንን ባታደርጊ፣ እኔ ወዳለሁበት ስፍራ መምጣት ሐአትችዪምና።
፲፮ እናም እውነት፣ እውነት እልሻለሁ፣ ለሁሉም የሆነው ይህ የእኔ ሀድምጽ ነው። አሜን።