ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፩


ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች

ክፍል ፩

በህዳር ፩፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በሀይረም ኦሀዮ በቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎች ልዮ ጉባዔ ወቅት በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት የተሰጠ ራዕይ። ከዚህ ጊዜ ቀደም ብሎ ብዙ ራእዮች ከጌታ ተሰጥተው ነበር፣ እናም እነዚህ ራዕዮች በመጽሐፍ መልክ ተጠርዘው እንዲታተሙ በጉባኤው ውሳኔ ከተሰጠባቸው ዋነኛ ሐሳቦች መካከል አንዱ ነበር። ይህ ክፍል በዚህ ዘመን የተሰጡትን ትምህርቶች፣ ቃልኪዳኖች፣ እና ትዛዛትን በተመለከተ የጌታን መግቢያ የያዘ ነው።

፩–፯፣ የማስጠንቀቂያው ድምጽ ለሁሉም ሰው ነው፤ ፰–፲፮፣ ክህደትና ክፋት ዳግም ምፅዓትን ይቀድማሉ፤ ፲፯–፳፫፣ ጆሴፍ ስሚዝ የጌታን እውነት እና ሀይል በምድር ዳግመኛ እንዲመልስ ተጠርቷል፤ ፳፬–፴፫፣ መፅሐፈ ሞርሞን መጥቷል እናም እውነተኛ ቤተክርስቲያን ተመስርታለች፤ ፴፬–፴፮፣ ሰላምም ከምድር ይወሰዳል፣ ፴፯–፴፱፣ እነዚህን ትዛዛት መርምሩ።

ከፍ ብሎ የሚኖረው እና አይኖቹንም በሁሉም ሰዎች ላይ የሆነው፣ የእርሱ ድምፅ አቤቱ እናንት የቤተክርስቲያኔ ሰዎች ሆይ አድምጡ ይላል፣ አዎን እውነት እላለሁ፥ እናንት በሩቅ ያላችሁ፣ በባህር ደሴቶች ላይ ያላችሁ ስሙ፣ በአንድነትም አድምጡ።

በእውነት የጌታ ድምጽ ለሁሉም ሰው ነውና፣ እናም ማንም አያመልጥም፤ እናም የማያይ አይንም ሆነ የማይሰማ ጆሮ፣ ወይም የማይጣስ ልብ አይኖርም።

እናም አመጸኞች በብዙ ሐዘን ይወጋሉ፤ ኃጢአታቸውም በቤቶች አናት ላይ ይነገራሉ፣ የሚስጥር ተግባሮቻውም ይገለጣሉ።

እናም በመጨረሻዎቹ ቀናት፣ እኔ በመረጥኳቸው ደቀመዛሙርቶቼ አንደበት፣ የማስጠንቀቂያው ድምጽ ለሁሉም ህዝብ ይሆናል።

እናም እነርሱም ወደፊት ይሄዳሉ፣ ማንም አያግዳቸውም፣ እኔ ጌታ አዝዣቸዋለሁና።

እነሆ አቤቱ! የምድር ነዋሪዎች፣ ለእናንተ እንዲያሳትሙት የሰጠዋችሁ ይህ የእኔ ስልጣን፣ እንዲሁም የአገልጋዮቼ ስልጣን፣ እናም ለመፅሐፈ ትእዛዛቴ መቅድም ነው።

ስለዚህ፣ ፍሩ እናም ተንቀጥቀጡ፣ አቤቱ! እናንት ሕዝቦች ሆይ፣ እኔ ጌታ በእነርሱ ያወጅኩት ይፈጸማልና

እናም እውነት እላችኋለሁ፣ ይህንን የምስራች ይዘው ወደ ምድር ነዋሪዎች የሚሄዱ፣ ለእነርሱ በምድርም ሆነ በሰማይ፣ የማያምኑትን እና አመጸኞችን የማሰር ኃይል ተሰጥቷቸዋል፤

አዎን፣ እውነት፣ የእግዚአብሔር ቁጣ በክፉዎች ላይ ያለልክ የሚወርድበት ቀን እስከሚመጣ ድረስ እንዲያስሯቸው—

ጌታ መጥቶ ለእያንዳንዱን ሰው እንደየስራው መጠን እስኪመልስ እና ሁሉም ሰው ለባልንጀራው በሰፈረበት መጠን እስከሚሰፍርበት ቀን ድረስ የማሰር ኃይል ተሰጥቷቸዋል።

፲፩ ስለዚህ የሚሰማ ሁሉ ይሰማ ዘንድ፣ የጌታ ድምጽ እስከ ምድር ዳርቻ ነው፥

፲፪ ለሚመጣው ተዘጋጁ ተዘጋጁ፤ ጌታ ተቃርቧልና፤

፲፫ እናም የጌታ ቁጣ ተቀጣጥሏል፣ እናም ሰይፉም በሰማይ ታጥቧል፣ እንዲሁም በምድር ነዋሪዎችም ላይ ይወርዳል።

፲፬ እናም የጌታ ክንድ ይገለጣል፤ የጌታን ድምጽ ሆነ ያገልጋዮቹን ድምጽ ከማይሰሙ፣ ለነቢያት እና ለኃዋሪያት ቃላት ትኩረት ከማይሰጡ ሰዎች መካከል የሚገለሉበት ቀን ይመጣል፣

፲፭ ከስርዓቴ እርቀዋል፣ እናም ዘለአለማዊ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና

፲፮ ጽድቁን ለመመስረት ጌታን አይፈልጉም፣ ነገር ግን ሁሉም ሰው በገዛ መንገዱ፣ እናም ቁሳቁሱ የጣኦት በሆነው፣ አምሳያውም የአለም በሆነው፣ አርጅቶም በባቢሎን በሚጠፋው፣ እንዲሁም በምትወድቀው በታላቂቷ ባቢሎን እንደ አምላኩ ምስል ይጓዛል።

፲፯ ስለዚህም እኔ ጌታ በምድር ነዎሪዎች ላይ የሚመጣውን መቅሰፍት በማወቄ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊን ጠራሁት እናም ከሰማይም ተናገርኩት እንዲሁም ትእዛዛትን ሰጠሁት፤

፲፰ እናም ደግሞ ይህንን የምስራች ለአለም እንዲያውጁ፣ እናም ይህን ሁሉ ያደረኩትም በነቢያቶች የተጻፈው ይፈጸም ዘንድ ለሌሎችም ትእዛዛትን ሰጥቻለሁ—

፲፱ የአለም ደካማ ነገሮች ወደፊትም ይወጣሉ ብርቱውን እና ጠንካራውን ይሰብራሉ፣ ሰው ባልጀራውን መምከር አይገባውም፣ በስጋ ክንድ መመካት አይኖርበትም—

ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው የአለም አዳኝ በሆነው በጌታ እግዚአብሔር ስም ይናገር ዘንድ፤

፳፩ ደግሞም እምነትም በምድር ይበዛ ዘንድ፤

፳፪ ዘለአለማዊ ቃልኪዳኔ ይመሰረት ዘንድ፤

፳፫ የወንጌሌ ሙላት በደካሞች እና በተራ ሰዎች አማካይነት በነገስታት እና በገዢዎች ፊት እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ይታወጅ ዘንድ ተሰጥቷቸዋል።

፳፬ እነሆ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ እኔም ተናግሬዋለሁ፤ እነዚህ ትእዛዛት ከእኔ ዘንድ ናቸው፣ በድክመታቸው፣ እንደቋንቋቸው ወደ መረዳት ይመቱ ዘንድ ለአገልጋዮቼ ተሰጥተዋቸዋል።

፳፭ እናም ስህተትን እስከፈጸሙ ድረስ ስተታቸውን እንዲታወቁ፤

፳፮ እናም ጥበብንም እስከፈለጉ ድረስ ያንኑ ይማሩ ዘንድ፤

፳፯ እናም ኃጢአትን እስከሰሩ ድረስ ንስሀ እንዲገቡ ይገሰጹ ዘንድ፤

፳፰ ትሁት እስከሆኑ ድረስ እንዲበረቱ እና ከላይም እንዲባረኩ፣ እንዲሁም ከጊዜ ወደ ጊዜ እውቀትንም ይቀበሉ ዘንድ ነው።

፳፱ እና አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊም ቢሆን የኔፋውያንን መዝገብ ከተቀበለ በኋላ፤ አዎን በእግዚአብሔር ምህረት፣ በእግዚአብሔር ኃይል መፅሐፈ ሞርሞንን የመተርጎም ኃይል ይኖረው ዘንድ ነው።

እናም ደግሞ እነዚህ ትእዛዛት የተሰጣቸው በምድር ገጽ ላይ ሁሉ ብቸኛ እውነተኛ እና ህያው የሆነችውን ቤተክርስቲያን፣ እኔም ጌታ በጣም የተደሰትኩባትን የእዚህችን ቤተክርስቲያን መሰረት የመጣል፣ እና ከጭለማ እና ከተደበቀችበት የማውጣት ኃይል ይኖራቸው ዘንድ ነው። እነዚህን ነገሮች ለቤትክርስቲያኗ ስናገር በጋራ እንጂ በተናጠል አይደለም—

፴፩ እኔ ጌታ ኃጢአትን በዝቅተኛ ደረጃ መመልከት አይቻለኝምና፤

፴፪ ሆኖም፣ ንስሀ የሚገባ እና የጌታን ትእዛዛት የሚጠብቅ ይቅርታን ይቀበላል፤

፴፫ እናም ንስሀ የማይገባ፣ የተቀበለውም ብርሀን ቢሆን እንኳን ከእርሱ ይወሰድበታልመንፈሴም ከሰው ጋር ዘወትር አይሆንምና፣ ይላል የሰራዊት ጌታ።

፴፬ እናም ደግሞ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አቤቱ የምድር ነዋሪዎች ሆይ፥ እኔ ጌታ እነዚህን ነገሮች ለስጋ ለባሽ ሁሉ ለማሳወቅ ፍቃደኛ ነኝ፤

፴፭ እኔም ለሰዎች አላደላም፣ እናም ቀኑ በፍጥነት እንደመጣ ሁሉም ሰው ያውቀው ዘንድ ፍቃዴ ነው፤ ሰላም ከምድር የሚወሰድበት፣ እና ዲያብሎስም በግዛቱም ላይ ኃይል የሚያገኝበት ሰዓት አልደረሰም ነገር ግን ተቃርቧል።

፴፮ እናም ደግሞ ጌታ በቅዱሳኑ ላይ ኃይል ይኖረዋል፣ እናም በመካከላቸውም ይነግሳል እናም በኢዱሜአ ወይም በአለም ላይ በፍርድ ይወርዳል።

፴፯ እነዚህን ትእዛዛት መርምሩ፣ የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና፣ እናም በውስጣቸው ያሉት ትንቢቶች እና የተስፋ ቃላት ሁሉ ይፈጸማሉ።

፴፰ እኔ ጌታ የተናገርኩትን፣ ተናግሬያለሁ፣ እናም አላመካኝም፤ ሰማያትና ምድር ቢያልፉም ቃሌ ግን አያልፍም፣ ነገር ግን ሁሉም ይፈጸማል፣ በእኔ ድምጽ ሆነ በአገልጋዮቼ ድምጽ፣ ያም አንድ ነው።

፴፱ ስለሆነም፣ እናም አስተውሉ፣ ጌታ አምላክ ነው፣ መንፈስም ይመሰክራል፣ እናም ምስክርነቱም እውነት ነው፣ እናም እውነት ከዘለአለም እስከ ዘለአለም ይኖራል። አሜን።