ክፍል ፲፯
ሰኔ ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) በፈየት፣ ኒው ዮርክ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት የመፅሐፈ ሞርሞንን ታሪክ የተቀረጸበትን ሰሌዳዎች ከማየታቸው በፊት ለኦሊቨር ካውድሪ፣ ዴቪድ ዊትመር እና ማርቲን ሀሪስ የተሰጠ ራዕይ። ጆሴፍ ስሚዝ እና ጸሀፊው፣ ኦሊቨር ካውድሪ፣ ሶስት ልዩ ምስክሮች እንደሚመረጡ ከመፅሐፈ ሞርሞን ሰሌዳ ትርጉም ተገንዝበው ነበር (ኤተር ፭፥፪–፬፤ ፪ ኔፊ ፲፩፥፫፤ ፳፯፥፲፪ን ተመልከቱ)። ኦሊቨር ካውድሪ፣ ዴቪድ ዊትመር እና ማርቲን ሀሪስ በልዩ መሻት በመነሳሳት ሶስቱ ምስክሮች መሆንን ፈልገው ነበር። ነቢዩ ጌታን ጠየቀ፣ እናም ይህ ራዕይ በኡሪም እና ቱሚም አማካይነት የተሰጠ መልስ ነበር።
፩–፬፣ ሰሌዳዎቹ እና ሌሎች የተቀደሱ ነገሮችን ሶስቱ ምስክሮች በእምነት ይመለከታሉ፤ ፭–፱፣ ስለ መፅሐፈ ሞርሞን መለኮታዊነት ክርስቶስ ምስክርነቱን ሰጠ።
፩ እነሆ፣ በቃሌ ላይ መደገፍ አለባችሁ እላችኋለሁ፣ ዓላማም በተሞላበት ልብ ካደረጋችሁ፣ ሀሰሌዳዎቹን፣ እንዲሁም ጥሩርን፣ ለየላባንን ሰይፍ፣ ከጌታ ጋር ሐፊት ለፊት በተነጋገርንበት ጊዜ ለያሬድ መወንድም የተሰጡትን ሠኡሪም እና ቱሚም፣ እናም ረበቀይ ባህር ዳርቻ በምድረበዳ ለሌሒ የተሰጠውን ሰተዓምረኛ ጠቋሚ ሸትመለከታላችሁ።
፪ እናም እነርሱን የምትመለከቱት በእምነታችሁ፣ እንዲሁም ጥንታዊ ነቢያት በነበራቸው አይነት እምነት ነው።
፫ እምነት ካገኛችሁ እና በአይኖቻችሁ ካያችኋቸው በኋላ በእግዚአብሔር ሀይል ስለእነርሱ ሀትመሰክራላችሁ፤
፬ እናም አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ፣ እንዳይጠፋ ዘንድ፣ በዚህ ስራ ለሰው ልጆች የጽድቅ አላማዬን አመጣ ዘንድ ይህንን ታደርጋላችሁ።
፭ እናም አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ፣ እንደተመለከታቸው ሁሉ፤ እናንተም እንዲሁ እንደተመለክታችሁ ትመሰክራላችሁ፣ እናም እርሱም የተመለከታቸውም በእኔ ኃይል ነው፣ ምክንያቱም እምነት ስለነበረው ነበር።
፮ እና እርሱም ሀመፅሐፍን፣ እንዲሁም እኔ ያዘዝኩትን ለክፍል፣ ተርጉሟል፣ እናም ጌታ እና አምላካህ ህያው እንደሆነ ይህም እውነት ነው።
፯ ስለዚህ ልክ እንደ እርሱ አንድ አይነት ሀይል፣ እናም አንድ አይነት እምነት፣ እናም አንድ አይነት ስጦታ ተቀብላችኋል፤
፰ እናም የሰጠኋችሁን የመጨረሻ ትእዛዛቴን ከፈጸማችሁ የሲዖል ሀደጆችም አይቋቋማችሁም፣ ለጸጋዬ ለእናንተ በቂ ነውና፣ እናም በመጨራሻው ቀን ሐከፍ ትላላችሁ።
፱ እናም ለሰው ልጆች የጽድቅ አላማዬን አመጣ ዘንድ፣ እኔ ሀጌታችሁና አምላካችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ተናግሬዋለሁ። አሜን።