ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፰


ክፍል ፰

ሚያዝያ ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ፣ ፔንስልቬንያ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት ለኦሊቨር ካውድሪ የተሰጠ ራዕይ። በመፅሐፈ ሞርሞን ትርጉም ሂደት በጸሀፊነት በማገልገል የነቢዩን ቃል እየጻፈ የቀጠለው ኦሊቨር፣ የትርጉም ስጦታ እንዲሰጠው ፈለገ። ጌታም ይህን እራይ በመስጠት ለልመናው መልስ ሰጠው።

፩–፭፣ ራዕይ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እማካኝነት ይመጣል፤ ፮–፲፪፣ የእግዚአብሔር የሚሥጥራት እውቀት እና የጥንት መዛግብትን የመተርጎም ኃይል የሚመጣው በእምነት ነው።

ኦሊቨር ካውድሪ፣ እውነት፣ እውነት፣ እልሀለሁ፣ ጌታ አምላክህንና ቤዛህ ህያው እንደሆነ፣ ጥንታዊ የሆኑትን በመንፈሴ መገለጥ የተነገሩትን የቅዱስ መጻህፍቴ ክፍል የሆኑትን የቆዩ መዛግብት ጽሁፎችን እውቀት እንደምትቀበል በማመን በታማኝ ልብ፣ በእምነት የጠየከውን ሁሉ እውቀት ትቀበላለህ።

አዎን፣ እነሆ፣ በአንተ ላይ በሚሆነው እና በልብህም በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በአዕምሮህ እና በልብህ እነግርሀለሁ

አሁን፣ እነሆ፣ ይህ የራዕይ መንፈስ ነው፤ እነሆ ይህም ሙሴ የእስራኤልን ልጆች በቀይ ባህር ውስጥ በደረቅ ምድር ያሻገረበት መንፈስ ነው።

ስለዚህ ይህ ያንተ ስጦታ ነው፣ ተጠቀምበት፣ እናም ከጠላቶችህ እጆች ስለሚያወጣህ የተባረክ ነህ፣ ይህ ባይሆን ኖሮ ይገድሉህ እንዲሁም ነፍስህንም ወደጥፋት ባመጡት ነበር።

አቤቱ፣ እነዚህን ቃላት አስታውስ፣ እናም ትእዛዛቴን ጠብቅ። ይህ ስጦታህ እንደሆነ አስታውስ።

ስጦታህ ይህ ብቻም አይደለም፤ የአሮን ስጦታ የሆነው ሌላም ስጦታ አለህ፤ እነሆ፣ ይህም ብዙ ነገሮችንም ነግሮኃል፤

እነሆ፣ ከእግዚአብሔር በስተቀር ይህንን የአሮንን ስጦታ ካንተ ጋር እንዲሆን የሚያደርግ ምንም ኃይል የለም።

ስለዚህ፣ አትጠራጠር፣ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነውና፤ እናም በእጅህም ትይዘዋለህ፣ እናም ድንቅም የሆነ ስራ ትሰራለህ፤ ከእጅህም ምንም አይነት ኃይል ሊወስደው አይችልም፣ የእግዚአብሔር ስራ ነውና።

እናም፣ ስለዚህ በእነዚህ መንገዶች እንድነግርህ የምትጠይቀኝን፣ ይህንንም እሰጥሀለሁ፣ እናም እርሱን በተመለከተ እውቀት ይኖርሀል።

ያለ እምነት ምንም ማድረግ እንደማትችል አስታውስ፤ ስለዚህ በእምነት ጠይቅ። በእነዚህም ነገሮች አትቀልድ፤ የማያስፈልጉህን ነገሮች አትጠይቅ

፲፩ የእግዚአብሔርን ሚስጥራት ታውቅ ዘንድ፣ እናም ተደብቀው ያሉትን የተቀደሱ ጥንታዊ መዛግብትን መተርጎም፣ እንዲሁም ከእነርሱም እውቀት ማግኘት ትችል ዘንድ ጠይቅ፤ እናም እንደ እምነትህ ይደረግልሀል።

፲፪ እነሆ፣ እኔ ነኝ የተናገርኩት፤ እናም ከመጀመሪያው ጀምሮ የተናገርኩህ እኔው ራሴው ነኝ። አሜን።