ክፍል ፳፯
በነሀሴ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ ፔንስልቫኒይ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። የዳቦ እና ወይን ቅዱስ ቁርባን ሀይማኖታዊ አገልግሎት ለመስጠት ለማዘጋጀት፣ ጆሴፍ ወይን ያገኝ ዘንድ ሄደ። የሰማይ መልአክም ተገናኘው እናም ይህንን ራዕይ ተቀበለ፣ የዚህም ራዕይ አማካይ ክፍል በወቅቱ ሲጻፍ ቀሪው በቀጣዩ ወር መስከረም የተጻፈ ነበር። በአሁን ወቅት በቤተክርስቲያኗ የቅዱስ ቁርባን አገልግሎት ውስጥ በወይን ፋንታ ውሀ ጥቅም ላይ ውሏል።
፩–፬፣ በቅዱስ ቁርባን ወቅት በምሳሌነት መውሰድ ያለባቸው ተገለጡ፤ ፭–፲፬፣ ክርስቶስ እና ከሁሉም ዘመናት ያሉ ደቀመዛሙርቱ ቅዱስ ቁርባንን መውሰድ ይኖርባቸዋል፤ ፲፭–፲፰፣ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር እቃ ልበሱ።
፩ ሀፈጣን እና ኃያል የሆኑትን፣ የጌታህን፣ የአምላክህን እና የአዳኝህን የኢየሱስ ክርስቶስን ቃላት አድምጥ።
፪ ስለሆነም፣ እነሆ፣ በአባቴ ፊት ለእናንተ የሰዋሁትን አካሌን እናም ለኃጢአታችሁ ሀስርየት የፈሰሰውን ለደሜን እያስታወሳችሁ ሙሉ አይናችሁን ወደ ሐክብሬ ካደረጋችሁ፣ መቅዱስ ቁርባንን ስትወስዱ የምትበሉት ወይም የምትጠጡት ነገር ለውጥ አያመጣም።
፫ ስለዚህ፣ ወይንም ሆነ ጠንካራ መጠጥ ከጠላቶቻችሁ እንዳትገዙ ትእዛዝን እሰጣችኋለሁ፤
፬ ስለዚህ፣ በመካከላችሁ፣ አዎን በምድር ላይ በሚገነባው በዚህ በአባቴ መንግስት፣ አዲስ ካልተሰራ በስተቀር ምንም ነገር እንዳትወስዱ፤
፭ እነሆ፣ ይህ በእኔ ዘንድ ጥበብ ነው፤ ስለዚህ፣ ከእናንተ ጋር እና ወደ እናንት የዘለአለም ወንጌሌን ሙላት የያዘውን መፅሐፈ ሞርሞንን እንዲገልጥ ከላኩት፣ የኤፍሬምን ሀበትር ጽሁፍ ቁልፎች ከሰጠሁት ለከሞሮኒ ጋር በምድር ላይ የወይን ፍሬውን ሐየምጠጣበት ሰዓት ስለሚመጣ አትደነቁ፤
፮ እናም እንዲሁም አለም ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያት አንደበት የመጨረሻውን ቀን በተመለከተ የተነገሩትን የሁሉም ነገሮች ዳግም መመለስ ቁልፍ ከሰጠሁት ሀከኢልያ ጋር፤
፯ እናም ደግሞ፣ እርሱ ሀ(ኢልያ) የጎበኝው እና ልጅ እንደሚኖረው እና ስሙም ዮሐንስ እንዲሚሆን በኤልያስም መንፈስ እንደሚሞላ የተነገረለት የዘካሪያስ ልጅ ከሆነው ለዮሐንስም ጋር፤
፰ ይህም ዮሐንስ ለእናንተ ለአገልጋዮቼ፣ ለጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ እና ለኦሊቨር ካውድሪ እንደ ሀአሮን እንድትጠሩ እና ለእንድትሾሙ የተቀበላችሁትን የመጀመሪያውን ሐክህነትን እንድትቀበሉ የላክሁት ነው፤
፱ እናም እንዲሁም መላው ምድር በእርግማን እንዳይመታ የአባቶችን ልብ ወደልጆች፣ የልጆችን ልብ ወደአባቶች ሀእንዲመልስ የሚያስችለውን የኃይል ቁልፍ ከሰጠሁት ለኤልያስ፤
፲ እንዲሁም ሀቃል ኪዳኖቹ በጸኑባቸው ከአባቶቻችሁ ከዮሴፍና ያዕቆብና፣ ይስሀቅና፣ አብርሐም ጋር፣
፲፩ እንዲሁም የሁሉም አባት፣ የሁሉም ልዑል፣ በዘመናት ከሸመገለው ከሚካኤል ወይም ሀአዳም ጋር፣
፲፪ እናም ሀሐዋርያት ትሆኑ ዘንድ ለበሾምኳችሁ እና ባጸደቅኩላችሁእናም የስሜ ልዩ ሐምስክሮች እንድትሆኑ እና የአገልግሎታችሁን እናም ለእነርሱ የገለጥኩላቸውን ተመሳሳይ ነገሮች ቁልፍ እንድትይዙ በላኳቸው ከጴጥሮስ፣ እና ከያእቆብ፣ እና ዮሐንስ ጋር፤
፲፫ ለእነርሱም በሰማይ እና በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ ሀበአንድ በምጠቀልልበት ለበዘመናት ሙላት፣ የዚህን ሐየዘመነ ፍጻሜን መወንጌልንና የመንግስቴን ሠቁልፎች ረለመጨረሻው ጊዜ ሰከሰጠኋቸው ጋር፤
፲፬ እናም እንዲሁ አባቴ ከአለም ሀከሰጠኝ ሁሉ ጋር የምጠጣበት ሰዓት ስለሚመጣ አትደነቁ።
፲፭ ስለዚህ፣ ልባችሁን ከፍ አድርጋችሁ ተደሰቱ፣ ወገባችሁን አጥብቁ፣ ክፋውን ቀን ለመቃወም ሁሉንም ፈጽማችሁ ሀለመቆም እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ለየጦር እቃ ሁሉ ልበሱ።
፲፮ ስለዚህ ሀመላእክቴ እንዲሰጧችሁ ያደረኩትን፣ ወገባችሁን ለበእውነት ሐታጥቃችሁ፣ መየጽድቅንም ሠጥሩር ለብሳችሁ፣ ረበሰላም ወንጌል በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤
፲፯ የሚንበለበሉትን የክፉን ሀፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ በማንሳት፤
፲፰ እናም የመዳንንም ራስ ቁር፣ እናም በእናንተ ላይ የማፈሰውን የመንፈስንም ሰይፍ እናም የምገልጥላችሁን ቃሌን ያዙ፣ እናም የምትጠይቁኝንም ነገሮች በተመለከተም ተስማሙ፣ እስከምመጣም ድርስ ታማኝ ሁኑ፣ እናም እናንተም እኔ ወደአለሁበት ሀትሆኑትም ዘንድ ለትነጠቃላችሁ። አሜን።