ክፍል ፻፳፮ በሐምሌ ፱፣ ፲፰፻፵፩ (እ.አ.አ.) በብሪገም ያንግ ቤት ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። በዚህ ጊዜ ብሪገም ያንግ የአስራ ሑለቱ ሐዋርያት ቡድን ፕሬዘደንት ነበር። ፩–፫፣ ብሪገም ያንግ ለአገልግሎቱ ተሞግሷል እና ወደፊትም ወደውጪ ከመጓዝ ፋታን አገኘ። ፩ ውድ እና ተወዳጅ ወንድም ሀብሪገም ያንግ፣ እውነት ጌታ እንዲህ ይልሀል፥ አገልጋዬ ብሪገም፣ እንዳለፉት ጊዜያት ቤተሰብህን እንድትተው አይጠበቅብህም፣ መስዋዕትህ በእኔ ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቷልና። ፪ ስለስሜም በጉዞዎችህ ከባድ ስራህን እና ሀአገልግሎትህን አይቻለሁ። ፫ ስለዚህ ቃሌን ወደውጪ እንድትልክ፣ እና ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለአለም ሀቤተሰብህን በልዩ ሁኔታ እንድትንከባከባቸው አዝሀለሁ። አሜን።