ክፍል ፻፫
በየካቲት ፳፬፣ ፲፰፻፴፬ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ይህ ራዕይ ፓርሊ ፒ ፕራት እና ላይመን ዋይት ስለእርዳታ እና በጃክሰን የግዛት ክፍል ውስጥ ወደሚገኘው መሬታቸው ቅዱሳንን ስለመመለስ ከነቢዩ ጋር ለመመካከር ከሚዙሪ ወደ ከርትላንድ ከደረሱ በኋላ የተቀበሉት ነበር።
፩–፬፣ ለምን ጌታ የጃክሰን የግዛት ክፍል ቅዱሳን እንዲሰደዱ እንደፈቀደ፤ ፭–፲፣ ትእዛዛትን ከጠበቁ ቅዱሳን ያሸንፋሉ፤ ፲፩–፳፣ የፅዮን ቤዛነት በሀይል ይመጣል፣ ጌታም በህዝቦቹ ፊት ይሄዳል፤ ፳፩–፳፰፣ ቅዱሳን በፅዮን ይሰብሰቡ፣ እና ህይወታቸውን የሚያጡትም ደግመው ያገኙታል፤ ፳፱–፵፣ የተለያዩ ወንድሞች የፅዮንን ሰፈር እንዲያደራጁና ወደ ፅዮን እንዲሄዱ ተጠሩ፤ ታማኝ ከሆኑም ውጤታማ እንደሚሆኑ የተስፋ ቃል ተሰጥቷቸዋል።
፩ ባልንጀሮቼ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እነሆ፣ በፅዮን ምድር የተበተኑትን ወንድሞቻችሁን ደህንነት እና ሀቤዛነት በሚመለከት ያላችሁን ሀላፊነት እንዴት ለእንድትፈፅሙ ታውቁ ዘንድ ራዕይና ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤
፪ ቁጣዬን በጊዜዬ ያለልክ በማወርድባቸው በጠላቶቼ እጆች ሀእየተሰደዱ እና እየተመቱት ስላሉት።
፫ የጥፋታቸውንም መስፈሪያ ሀይሞሉ ዘንድ፣ ጽዋቸውም ሙሉ ይሆን ዘንድ፣ እስከአሁን ፈቅጄላቸዋለሁና፤
፬ እና በስሜ ራሳቸውን የሚጠሩትም ለጥቂት ዘመን በከፍተኛ እና አሳዛኝ ተግሳፅ ሀይገሰጹ ዘንድ፣ ምክንያቱም አብረውም የሰጠኋቸውን አስተሳሰብና ትእዛዛት ለአላዳመጡምና።
፭ ነገር ግን እውነት እላችኋለሁ፣ እኔ ጌታ አምላካቸው የምሰጣቸውን ሀምክር ከዚህ ሰአት ጀምረው የሚያደምጡ ቢሆን፣ ህዝቤ ሊቀበሉ የሚችሉትን አዋጅ አውጃለሁ።
፮ እነሆ፣ ስላወጅኩት፣ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ጠላቶቼን ማሸነፍ ይጀምራሉ።
፯ እና እኔ ጌታ የምናገራቸውን ቃላት ለመከተል ሀቢያደምጡ፣ የአለም ለመንግስታት ከእግሮቼ በታች እስከሚገዙ እና ምድርንም ለዘለአለም ሐየራሳቸው እንዲያደርጓት መለቅዱሳን ሠእስከምትሰጥ ድረስ ማሸነፍን አያቆሙም።
፰ ነገር ግን ትእዛዛቴን ሀእስካላከበሩ እና ቃላቴንም እስካልተከተሉ ድረስ፣ የአለም መንግስታት ያሸንፏቸዋል።
፱ ለአለም ሀብርሀንና ለሰዎች አዳኝ ይሆኑ ዘንድ ተመርጠው ነበርና፤
፲ እና የሰዎች አዳኞች እስካልሆናችሁ ድረስ፣ ጣዕሙን እንዳጣ ሀጨው ትሆናላችሁ፣ እና ከዚያን ጊዜ በኋላ ከንቱ ትሆናላችሁ፣ ደግሞም ትጣላላችሁ፣ እናም በሰዎችም እግር ትረገጣላችሁ።
፲፩ ነገር ግን እውነት እላችኋለሁ፣ የተበተኑት ወንድሞቻችሁ ወደ ውርስ ሀመሬታቸው እንዲመለሱ፣ እና የፈረሱትን የፅዮን ስፍራዎችንም እንዲገነቡ አውጃለሁ።
፲፪ ሀከብዙ ስቃይ በኋላ፣ አስቀድሜ እንዳዘዝኳችሁ፣ በረከት ይመጣል።
፲፫ እነሆ፣ ይህም ከስቃያችሁ እና ከወንድሞቻችሁ ስቃይ በኋላ በተስፋ ቃል የሰጠኋችሁ በረከት ነው—ቤዛነታችሁ፣ እና የወንድሞቻችሁ ቤዛነት፣ እንዲሁም የፅዮን ምድር እንደገና እንዳትሸነፍ እንድትመሰረት ዳግም መመለሷ።
፲፬ ይህም ቢሆን፣ ውርሶቻቸውን ካረከሱ ይሸነፋሉ፤ ውርሶቻቸውን የሚያረክሱ ቢሆን አላድናቸውምና።
፲፭ እነሆ እላችኋለሁ፣ የፅዮን ቤዛነት በሀይል ይመጣ ዘንድ ይገባል፤
፲፮ ስለዚህ፣ ሀሙሴ የእስራኤልን ልጆች እንደመራው፣ የሚመራቸው ሰው ለህዝቤ አስነሳለሁ።
፲፯ እናንት የእስራኤል ልጆች፣ ሀየአብርሐም ዘር ናችሁና፣ እና በሀይሌና በተዘረጋው ክንዴ ከባርነታችሁ ተመርታችሁ መውጣት ያስፈልጋችኋልና።
፲፰ እና አባቶቻችሁ በመጀመሪያ እንደተመሩት፣ የፅዮን ቤዛነትም እንዲሁ ይሆናል።
፲፱ ስለዚህ፣ ልባችሁ አይታወክ፣ ለአባቶቻችሁ እንዳልኳቸው ለእናንተም እላችኋለሁና፥ በፊታችሁ ሀመልአኬን እልካለሁ፣ ነገር ግን ለእኔ በመካከላችሁ አልገለጥም።
፳ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በፊታችሁ ሀመላዕክቴን እልካለሁ፣ እና በመካከላችሁም እገኛለሁ፣ እና በጊዜም መልካሙን ምድር ለየራሳችሁ ታደርጋላችሁ።
፳፩ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በሰጠኋችሁ ምሳሌ ውስጥ ሀየወይን ስፍራው ጌታ የሆነው አገልጋይ የተናገረውን የሚመስለው ለሰው አጋልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ ነው።
፳፪ ስለዚህ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ ለቤቴ ሀጥንካሬ፣ ለወጣቶቼና ለጎልማሳዎቼ እንዲህ ይበል—በፅዮን ምድር፣ ለእኔ በተቀደሰው ገንዘብ በገዛሁት ምድር ላይ በአንድነት ተሰብሰቡ።
፳፫ እና ቤተክርስቲያኖቹ ሁሉ ብልህ ሰዎቻቸውን ከገንዘቦቻቸው ጋር ይላኩ፣ እና እንዳዘዝኩትም መሬቶችን ሀግዙ።
፳፬ እና የፅዮን ምድር እንዲሆን ከቀደስኩት ሀምድር፣ ከመልካሙ መሬቴ፣ እንዲሁም በእነርሱ ላይ በፊቴ ካመጣችሁት ከእነዚህ ምስክሮች በኋላ ከመሬታችሁ ሊያሰድዳችሁ ጠላቶቼ ከመጡባችሁ፣ እርገሟቸው፤
፳፭ እና ማንኛውም የምትረግሟቸውን፣ እረግማቸዋለሁ፣ እና ጠላቶቼንም ትበቅላላችሁ።
፳፮ እና በጠላቶቼ፣ በሚጠሉኝ ሶስተኛ እና አራተኛ ትውልድ ላይ ሀስትፈርዱም ከእናንተ ጋር እገኛለሁ።
፳፯ ለእኔ ህይወቱን ለመስጠት ማንም ሰው አይፍራ፤ ማንም ለእኔ ህይወቱን ሀአሳልፎ የሚሰጥ ዳግም ያገኘዋልና።
፳፰ እና ለእኔ ህይወቱን ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆነውም ደቀመዝሙሬ አይደለም።
፳፱ አገልጋዬ ሀስድኒ ሪግደን፣ ቤተክርስቲያኖችን ስለፅዮን ዳግም መመለስ እና ቤዛነት የሰጠኋቸውን ትእዛዛት እንዲጠብቁ ለማዘጋጀት፣ ለምስራቅ ሀገሮች ተሰብሳቢዎች ድምጹን ከፍ ማድረጉ ፍቃዴ ነው።
፴ አገልጋዬ ሀፓርሊ ፒ ፕራትና አገልጋዬ ላይመን ዋይት፣ ወደፅዮን ምድር የሚሄዱ ሰዎችን በአስሮች ወይም በሀያዎች ወይም በሀምሳዎች ወይም በመቶዎች እስኪያደራጁ ድረስ፣ ለቤቴ ለጥንካሬ አምስት መቶዎችን እስኪያገኙ ድረስ፣ ወደወንድሞቻቸው መሬት እንዳይመለሱ ፍቃዴ ነው።
፴፩ እነሆ ይህም ፍቃዴ ነው፤ ጠይቁ፣ ይሰጣችኋል፤ ነገር ግን ሰዎች ፈቃዴዬን ሁልጊዜም ሀአያደርጉም።
፴፪ ስለዚህ፣ አምስት መቶ የማታገኙ ቢሆን፣ ምናልባት ሶስት መቶ ታገኙ ዘንድ በቅንነት ፈልጉ።
፴፫ እና ሶስት መቶ ለማግኘት ባትችሉም፣ ምናልባት አንድ መቶ ታገኙ ዘንድ በቅንነት ፈልጉ።
፴፬ ነገር ግን እውነት እላችኋለሁ፣ ወደ ፅዮን ምድር አብሮአችሁ እንዲሄዱ ከቤቴ ጥንካሬ መቶ እስክታገኙ ድረስ ወደፅዮን ምድር እንዳትሄዱ ትእዛዝን እሰጣችኋለሁ።
፴፭ ስለዚህ፣ እንዳልኳችሁ ጠይቁ፣ ይሰጣችኋል፤ አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ ምናልባት ከእናንተ ጋር እንዲሄድ፣ እና በህዝቤ መካከል እንዲመራ፣ እና ሀበተቀደሰው ምድርም መንግስቴን ያደራጅ፣ እና የፅዮን ልጆችን በተሰጡት እና ወደፊት በሚሰጣችሁ ህግጋት እና ትእዛዛት መሰረት ይመሠርት ዘንድ በቅንነት ጸልዩ።
፴፮ ድልና ክብር ሁሉ የሚመጣላችሁ ሀበቅንነታችሁ፣ በታማኝነታችሁ፣ እና ለበእምነት ጸሎታችሁ ነው።
፴፯ አገልጋዬ ፓርሊ ፒ ፕራት ከአገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ ጋር ይጓዝ።
፴፰ አገልጋዬ ላይመን ዋይት ከአገልጋዬ ስድኒ ሪግደን ጋር ይጓዝ።
፴፱ አገልጋዬ ሀይረም ስሚዝ ከአገልጋዬ ፍሬድሪክ ጂ ዊሊያምስ ጋር ይጓዝ።
፵ አገልጋዬ ኦርሰን ሀይድ ከአገልጋዬ ኦርሰን ፕራት ጋር፣ አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ በሚመክራቸው በማንኛውም፣ የሰጠኋቸውን የእነዚህን ትእዛዛት ፍጻሜ ያገኙ፣ ይጓዙ፣ እና የሚቀረውንም በእጆቼ ይተዉት። እንዲህም ይሁን። አሜን።