ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፸፱


ክፍል ፸፱

በመጋቢት ፲፪፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) በሀይረም ኦሀዮ ውስጥ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ።

፩–፬፣ ጄርድ ካርተር በአፅናኙ ወንጌልን እንዲሰብክ ተጠርቷል።

፩ በእውነት እልሀለሁ፣ አገልጋዬ ጄሪድ ካርተር ዳግም ወደ ምስራቅ አገሮች፣ ከስፍራ ወደ ስፍራ፣ እናም ከከተማ ወደ ከተማ፣ በተሾመበት ሹመት ሀይል ውስጥ ታላቅ ደስታ የምስራች፣ እንዲሁም ዘለአለማዊ ወንጌልን፣ እየሰበከ እንዲሄድ ፍቃዴ ነው።

፪ እናም እውነትን እና የሚሄድበትን መንገድ የሚያስተምረውን አፅናኝንም እልክለታለሁ፤

፫ እናም የታመነ ቢሆን፣ ደግሞም በነዶም አነግሰዋለሁ።

፬ ስለዚህ፣ ልብህ ይደሰት፣ አገልጋዬ ጄርድ ካርተር፣ እናም አትፍራ፣ ይላል ጌታህ፣ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ። አሜን።