ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፵


ክፍል ፵

ጥር ፮፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) በፈየት፣ ኒው ዮርክ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ለሲድኒ ሪግደን የተሰጠ ራዕይ። ይህ እራይ ከመመዝገቡ ቀደም ብሎ፣ የነቢዩ ታሪክ እንደሚገልጸው፣ “ጄምስ [ኮቪል] የጌታን ቃል ስላልተቀበለ እና ወደ ቀድሞው መሰረታዊ መርሆችና ሰዎች ስለተመለሰ፣ ጌታ ለእኔ እና ለስድኒ ሪግደን ተከታዩን ራዕይ ሰጠን” (ክፍል ፴፱ን ተመልከቱ)።

፩–፫፣ የስደት ፍራቻ እና ለአለም መጨነቅ ወንጌልን አለመቀበልን ያመጣል።

፩ እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ቃሌን ለመታዘዝ ቃል ኪዳንን ስለገባ፣ የአገልጋዬ የጄምስ ኮቪል ልብ በፊቴ መልካም ነበር።

፪ እናም ቃሉን በደስታ ተቀበለ፣ ነገር ግን ወዲያውኑ ሰይጣን ፈተነው፤ እናም የስደት ፍራቻና ለአለም መጨነቅ ቃሉን እንዳይቀበል አደረገው።

፫ ስለዚህም ቃል ኪዳኔን አፈረሰ፣ እናም መልካም የመሰለኝን በእርሱ ላይ አደርግ ዘንድ ፍቃዴ ነው። አሜን።