ክፍል ፴፫
ጥቅምት ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.)፣ በፈየት፣ ኒው ዮርክ በነቢዩ በጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት ለእዝራ ታይር እና ኖርዝሮፕ ስዊት የተሰጠ ራዕይ። ይህንን ራዕይ በማስተዋወቅ፣ የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ እንደሚያረጋግጠው፣ “በእምነት ተግተው ለሚሹት ጌታ ሊያስተምራቸው ዘወትር ዝግጁ ነው።”
፩–፬፣ ሰራተኞች በአስራ አንደኛው ሰዓት ወንጌልን እንዲያውጁ ተጠርተዋል፤ ፭–፮፣ ቤተክርስቲያኗ ተመስርታለች፤ እና የተመረጡትም ይሰበሰባሉ፤ ፯–፲፣ ንሰሀ ግቡ፣ መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና፤ ፲፩–፲፭፣ ቤተክርስቲያኗ በወንጌል አለት ላይ ተመስርታለች፤ ፲፮–፲፰፣ ለሙሽራው ምጽአት ተዘጋጁ።
፩ እነሆ፣ እንዲህ እልሀችኋለሁ፣ አገልጋዮቼ እዝራ እና ኖርዝሮፕ፣ ጆሮቻችሁን ክፈቱ እናም ፈጣን እና ሀያል፣ ሀቃሉ ሁለት አንደበት ካለው ሰይፍ ይልቅ የተሳለ፣ ነፍስንና መንፈስን፣ መገጣጠሚያን እና መቅኔን እስኪለይ ድረስ የሚሰራውን የጌታን ድምፅ አድምጡ፣ እናም የልብን ሐሳቦችና ለምኞቶች የሚያውቅ ነው።
፪ እውነት፣ እውነት፣ እላችኋለሁ፣ ድምጻችሁን እንደ መለከት ሀድምጽ ከፍ እንድታደርጉ እና ወንጌሌን በጠማማና በክፉ ትውልድ መካከል እንድታውጁ ተጠርታችኋልና።
፫ እነሆም፣ ሀየእርሻው ስፍራ ነጭ ሆኖ አዝመራው ዝግጁ ነው፤ እናም ለአስራ አደኛው ሰዓት፣ እና ሐለመጨረሻ ጊዜ ወደ እኔ የወይን ስፍራ አገልጋዮቼን የምጠራበት ጊዜ ነው።
፬ እናም አንዳች ፍሬ እንኳን ሳይቀር ሀየወይን ስፍራዬም ለተበላሽቷል፤ እናም ከጥቂቶቹ በስተቀር ሐመልካምን የሚያደርጉ የሉም፤ እናም ሁሉም ብልሹ አእምሮ መበካህን ተንኮል ምክንያት በብዙ መንገዶች ሠጥፋት ላይ ወድቀዋል።
፭ እናም እውነት፣ እውነት፣ እላችኋለሁ፣ ይህችን ሀቤተክርስቲያን ለመስርቻታለሁ እናም ከምድረበዳ እንድትወጣ ጠርቻታለሁ።
፮ እናም ምርጦቼን፣ እንዲሁም በእኔ የሚያምኑትን፣ እና ድምጼን የሚያዳምጡትን ሁሉ፣ ሀከአራቱም የምድር ማዕዘናት ቢሆንም ለእሰበስባለሁ።
፯ አዎን፣ እውነት፣ እውነት፣ እላችኋለሁ፣ የእርሻው ስፍራ ነጭ ሆኖ አዝመራው ዝግጁ ነው፤ ስለዚህ፣ በማጭዶቻችሁ እጨዱ፣ እናም በሙሉ ኃይላችሁ፣ አዕምሮአችሁ፣ እናም ጉልበታችሁ ሰብስቡ።
፰ አንደበታችሁን ሀክፈቱ እንዲሁም ይሞላሉ፣ ከኢየሩሳሌም በምድረበዳ እንደተጓዘው፣ እንደጥንቱ ለኔፊም ትሆናላችሁ።
፱ አዎን፣ አንደበታችሁን ከፍታችሁ ከመናገር አትቆጠቡ፣ እናም ሀነዶንም በጀርባችሁ የተጫናችሁ ትሆናላችሁ፣ እኔም ከናንተ ጋር ነኝና።
፲ አዎን፣ አንደበታችሁን ክፈቱ እናም ይሞላሉ፣ እንዲህ በማለትም ተናገሩ፥ ሀንሰሀ ግቡ፣ ንሰሀ ግቡ፣ እናም የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ ጎዳናውንም አስተካክሉ፤ መንገሥተ ሰማይ ተቃርባለችና፤
፲፩ አዎን፣ ለኃጢአታችሁም ስርየት፣ እያንዳንዳችሁም ንሰሀ ግቡ እና ሀተጠመቁ፤ አዎን፣ በውሀም ተጠመቁ፣ እናም በመቀጠልም የእሳት እና የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ይመጣል።
፲፪ እነሆ፣ እውነት፣ እውነት፣ እላችኋለሁ፣ ይህ ሀወንጌሌ ነው፤ እናም በእኔ እምነት ከሌላቸው በስተቀር በምንም መንገድ ሊድኑ አይችሉም፤
፲፫ እናም በዚህ ሀአለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እገነባለሁ፣ አዎን፣ በዚህም አለት ላይ ተገንብታችኋል፣ እናም የምትቀጥሉም ከሆነ፣ ለየሲዖል ደጆችም አያሸንፏችሁም።
፲፬ እናም የቤተክርስቲያኗን ሀመመሪያዎች እና የተስፋ ቃላትን መጠበቅ ታስታውሳላቸሁ።
፲፭ እናም እምነት ያላቸውን ሁሉ በቤተክርስቲያኔ ውስጥ ሀእጆቻችሁን በመጫን ለታጸኗቸዋላችሁ፣ እናም እኔም የመንፈስ ቅዱስን ሐስጦታን እሰጣቸዋለሁ።
፲፮ እናም መፅሐፈ ሞርሞን እናም ሀቅዱሳን መጻህፍት ለእናንተ ለመማሪያነት ከእኔ ለእናንተ ተሰጥተዋል፤ እናም የመንፈሴም ኃይል ነገሮችን ሁሉ ሐህይወት ይሰጣል።
፲፯ ሰለዚህ፤ ሀሙሽራው በሚመጣበት ጊዜ ዝግጁ መሆን እንድትችሉ፣ መብራታችሁን አስተካክላችሁ በመለኮስ እና ዘይታችሁን በመያዝ፣ ታማኝ ሁኑ፣ ዘውትርም ጸልዩ—
፲፰ እነሆም፣ እውነት፣ እውነት፣ እላችኋለሁ፣ በቶሎም ሀእመጣለሁ። እንዲህም ይሁን። አሜን።