በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
የናይት ቤተሰቦች እና ሌሎች ወደ ፅዮን ተሰበሰቡ


“የናይት ቤተሰቦች እና ሌሎች ወደ ጽዮን ተሰበሰቡ፣” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች (2024 [እ.አ.አ])

‘’የናይት ቤተሰቦች እና ሌሎች ወደ ፅዮን ተሰበሰቡ፣’’ የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

ታህሳስ 1830–ነሐሴ1831 (እ.አ.አ)

የናይት ቤተሰቦች እና ሌሎች ወደ ፅዮን ተሰበሰቡ

ለጌታ ጥሪ መታዘዝ

ፖሊ እና ጆሴፍ ናይት ከሌሎች ቅዱሳን ጋር ወደ ኦሀዮ ተዛወሩ።

ፖሊ እና ጆሴፍ ናይት በኒው ዮርክ ውስጥ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ኖሩ። ነቢዩ ጆሴፍን በደንብ ያውቁት ነበር። ወንጌልን ከተማሩ በኋላ፣ ቤተክርስቲያኗን ለመቀላቀል መረጡ። ጌታ ቅዱሳንን ወደ ኦሀዮ እንዲሄዱ በጠየቀ ጊዜ፣ የናይት ቤተሰቦችም ትዕዛዙን ተቀበሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 37Saints [ቅዱሳን]1፥3394109–110

ሊመን ኮፕሊ በኦሀዮ ያሉ ቅዱሳን ሰላምታ ሲያቀርብላቸው።

የናይት ቤተሰቦች ኦሀዮ በደረሱ ጊዜ ተደሰቱ። የቤተክርስቲያኗ አባል የነበረው ሊመን ኮፕሊ፣ የተወሰኑ ቅዱሳን በእርሱ መሬት ላይ መኖር ይችላሉ አለ። በዚያ እህል ለመዝራት እና ቤቶችን ለመገንባት በቂ ስፍራ ነበር። ጆሴፍ ናይት እና ልጆቹ ማሳዎቹ እህል ለመዝራት አመቺ እንዲሆኑ ለማድረግ በሀይል ሰሩ።

Saints [ቅዱሳን]1፥126–27

ቅዱሳን የሊመን ኮፕሊን መሬት ለቀው ሲሄዱ።

ነገር ግን አንድ ቀን፣ ሊመን ስለመሬቱ ያለውን ሀሳብ ቀየረ። ቅዱሳኑ ከዚህ በኋላ በዚያ እንዲኖሩ አልፈለገም። የናይት ቤተሰቦችን እና እያንዳንዱን ሰው ወጥተው እንዲሄዱ ነገራቸው።

Saints [ቅዱሳን]1፥127

ቅዱሳን ምን ማድረግ እንዳለባቸው ጆሴፍን ሲጠይቁ።

ቅዱሳኑ ተጨንቀው ነበር። አሁን የትም የሚኖሩበት አልነበራቸውም። ነቢዩ ጆሴፍን ምን ማድረግ እንዳለባቸው ጠየቁት።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 54Saints [ቅዱሳን]1–127

ጆሴፍም ለቅዱሳን ወደ ምዙሪ እንዲሄዱ እና በዚያም ጽዮንን እንዲገነቡ ሲነግራቸው።

ጌታም እነዚህ ቅዱሳን ወደ ምዙሪ ይሄዱ እና ጽዮንን ይገንቡ አለ። ጽዮን የጌታ ህዝቦች ሊሰበሰቡበት የሚችሉበት ከተማ ይሆናል። በጽዮን፣ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን የሚገቡበትን ቤተመቅደስ ይገነባሉ። እነዚህን ቃል ኪዳኖች የሚጠብቁ ከሆነ እርሱ ይባርካቸዋል። የናይት ቤተሰቦችም ለመሄድ ተደሰቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥1–842፥30–3645፥59–6654፥6–957፥1–2Saints [ቅዱሳን]1፥128

ወደ ምዙሪ በሚሄዱበት ወቅት የፖሊ ቤተሰቦች እርስዋን ሲንከባከቧት።

የናይት ቤተሰቦች ወደ ምዙሪ በተጓዙበት ወቅት፣ ፖሊ በጣም ታመመች። ባለቤቷ፣ ጆሴፍ፣ እና ወንዶች ልጆቿ ከዚህ በኋላ ብዙ ጊዜ ልትኖር አትችልም በማለት ተጨንቀው ነበር። ነገር ግን ፖሊ ከመሞቷ በፊት ጽዮን ውስጥ መሆን እንደምትፈልግ ለቤተሰቦቿ ተናገረች። እርሷ ከምንም ነገር በላይ ይህን ትመኝ ነበር!

Saints [ቅዱሳን]1፥128

የናይት ቤተሰቦች በምዙሪ ሲደርሱ።

ከረዥም ጉዞ በኋላ፣ የናይት ቤተሰቦች በምዙሪ ደረሱ። ፖሊ ይህን ለማየት በመኖሯ ጌታን በጣም አመሰገነች። የናይት ቤተሰቦች መሬቱ ያማረ እንደሆነ አሰቡ። በዚያም ጽዮንን ለመገንባት የጌታን ትእዛዛት መጠበቅ እንደሚችሉ እምነት ነበራቸው።

Saints [ቅዱሳን]1፥132

ቅዱሳን አዲሱ ቤተመቅደስ በሚገነባበት ስፍራ ላይ በምልክት ድንጋይ ሲያስቀምጡ።

ቅዱሳኑም ልዩ የሆነ ጸሎትን በዚያ አደረጉ እና መሬቱንም የጌታ ህዝቦች የሚመጡበት ስፍራ እንዲሆን ጽዮን ብለው ሰየሙት። ነቢዩ ጆሴፍ የቤተመቅደሱ ማእዘን የሚቀመጥበትን ቦታ ለማመልከት ድንጋይን አስቀመጠ። ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ፖሊ ሞተች። ጌታም ወደ ጽዮን የሚመጡ እና በዚያም የሚሞቱ ቅዱሳን በሰማይ እረፍት እንደሚያገኙ ቃል ገባላቸው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥1–2Saints [ቅዱሣን]1፥132–33