በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ቅዱሣን ለሙታን ስለሚደረግ ጥምቀት ተማሩ


“ቅዱሣን ለሙታን ስለሚደረግ ጥምቀት ተማሩ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች (2024 [እ.አ.አ])

“ቅዱሣን ለሙታን ስለሚደረግ ጥምቀት ተማሩ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

ነሐሴ–ጥቅምት 1840 (እ.አ.አ)

ቅዱሣን ለሙታን ስለሚደረግ ጥምቀት ተማሩ

ላልተጠመቁ የቤተሰብ አባላት ያለ ተስፋ

ጄን ኔይማን ጆሴፍ ስሚዝ ንግግር በሚያደርግበት የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ።

ጄን ኔይማን በናቩ ትኖር ነበር። ጆሴፍ ስሚዝ ንግግር ወደሚያደርግበት የቀብር ሥነ ሥርዓት ሄደች። የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ጄን ስለ ልጇ ሳይረስ እንድታስብ አደረጋት። እርሱም ሞቶ ነበር እንዲሁም አልተጠመቀም። ጄን ስለ ሳይረስ በሀሳብ ጨንቋት ነበር። ከሰማይ አባት ጋር ለመኖር መጠመቅ እንዳለብን ታውቅ ነበር።

ቅዱሳን1፥421

ጆሴፍ በአልቪን ስሚዝ መቃብር ፊት ተንበርክኮ።

ጆሴፍ ምን እንደሚሰማት ያውቅ ነበር። ሳይጠመቅ ስለሞተው ወንድሙ አልቪን ተመሳሳይ ነገር ያስጨንቀው ነበር።

ቅዱሳን1፥421

ጆሴፍ ስለሙታን የሚደረገውን የጥምቀት ትምህርት አስተዋወቀ።

በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ፣ ጆሴፍ እግዚአብሔር ያስተማረውን ነገር አካፈለ። አንድ ሰው ሳይጠመቅ ከሞተ እኛ ለዚያ ሰው መጠመቅ እንችላለን አለ።

ቅዱሳን1፥421

ጄን ለወንድ ልጇ ስትጠመቅ።

ጄን ይህን ስትሰማ በጣም ተደሰተች! ከቀብር ሥነ ሥርዓቱ በኋላ፣ ወዲያው ከቤተክርስቲያኗ ሽማግሌ ጋር ወደ ወንዝ ሄደች። እርሱም ለሳይረስ አጠመቃት።

ቅዱሳን1፥421

ጆሴፍ ለሙታን ስለመጠመቅ ተጨማሪ ቅዱሳንን እያስተማረ።

ከጥቂት ሳምንታት በኋላ፣ ጆሴፍ ለሙታን ስለመጠመቅ ለቅዱሳን የበለጠ አስተማራቸው። ብዙ የሞቱ ሰዎች መጠመቅ እንደሚፈልጉ ተናገረ። እነርሱ ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል ይፈልጋሉ። በሕይወት ያሉ የቤተሰብ አባላት ለእነርሱ እንዲጠመቁ እየጠብቁ እና ተስፋ እያደረጉ ነበር።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 128፥15–19ቅዱሳን1፥423

ቅዱሳን ለሙታን እየተጠመቁ።

ቅዱሳኑ ወዲያውኑ ወደ ወንዙ ሮጡ። ለሚወዷቸው ሰዎችም ተጠመቁ። ሃይረም ስሚዝ ለአልቪን ተጠመቀ። በኋላም፣ ጌታ የሙታን ጥምቀት በቤተመቅደስ ውስጥ እንዲደረግ፣ አንድ ሰው የእያንዳንዱን ጥምቀት መዝገብ መያዝ እንዳለበት እና ወንዶች ለወንዶች፣ ሴቶች ደግሞ ለሴቶች እመጠመቅ እንደሚገባቸው አስተማረ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥29–32127፥5–12128፥1–9ቅዱሳን1፥424