በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ጆሴፍ እና ኦሊቨር የክህነት ቁልፎችን ተቀበሉ


“ጆሴፍ እና ኦሊቨር የክህነት ቁልፎችን ተቀበሉ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“ጆሴፍ እና ኦሊቨር የክህነት ቁልፎችን ተቀበሉ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

ሚያዝያ 1836 (እ.አ.አ)

ጆሴፍ እና ኦሊቨር የክህነት ቁልፎችን ተቀበሉ

ኢየሱስ ክርስቶስ እና መላእክት የከርትላንድ ቤተመቅደስን ጎበኙ

ጆሴፍ ስሚዝ በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ለነበሩት ቅዱሳን ቅዱስ ቁርባንን እያሳለፈ።

የከርትላንድ ቤተመቅደስ ከተመረቀ ከአንድ ሳምንት በኋላ፣ በሺህ የሚቆጠሩ ቅዱሳን አዳኙን ለማምለክ በቤተመቅደስ ተሰበሰቡ። እለቱም የፋሲካ እሁድ ነበር። ጆሴፍ ስሚዝ፣ ኦሊቨር ካውድሪ፣ እና አስራ ሁለቱ ሃዋርያት ቅዱስ ቁርባንን ለቅዱሳን ሰጡ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፤ የክፍል መግቢያ፤ ቅዱሳን1፥239

ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውድሪ በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ሲጸልዩ።

ከቅዱስ ቁርባን በኋላ፣ ጆሴፍ እና ኦሊቨር በቤተመቅደሱ ውስጥ፣ ከመጋረጃው በስተጀርባ ለመጸለይ ጸጥ ያለ ስፍራን አገኙ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፤ የክፍል መግቢያ፤ ቅዱሳን1፥239

ኢየሱስ ክርስቶስ ለጆሴፍ እና ለኦሊቨር ሲገለጥ።

ጸሎታቸውን እንደጨረሱ፣ ወደላይ ተመለከቱ። ኢየሱስ ክርስቶስ በፊታቸው ቆሞ ነበር። ቅዱሳን ቤተመቅደስን ለመስራት ጠንክረው እንደሰሩ አውቋል። ‘’ይህን ቤት ተቀብዬዋለሁ’’ በማለት ተናገረ። ኢየሱስ ለጆሴፍ እና ለኦሊቨር የቤተመቅደሱ በረከቶች ለብዙ ህዝብ ታላቅ ሃሴትን እንደሚያመጣ ተናገረ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥1–10

ሙሴ ለጆሴፍ እና ለኦሊቨር ሲገለጥ።

ኢየሱስ ከተሰወረ በኋላ፣ የብሉይ ኪዳን ነቢይ የነበረው ሙሴ ለጆሴፍ እና ለኦሊቨር ተገለጠ። እርሱም የእስራኤልን መሰባሰብ የክህነት ቁልፍ ስጣቸው። ይህም ማለት የወንጌል ማካፈልን ስራ መምራት ይችላሉ ማለት ነው። ሰዎችን ወደ አዳኙ ቤተክርስቲያን ለማምጣት ወደ ዓለም ሁሉ ሚሲዮናውያንን መላክ ይችላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥11

ኤልያ ለጆሴፍ እና ለኦሊቨር ሲገለጥ።

ቀጥሎም፣ ነቢዩ ኤልያ ተገለጠ። እርሱ ለጆሴፍ እና ለኦሊቨር የአብርሐም ቃል ኪዳንን ለመመለስ ቁልፎችን ሰጣቸው። ይህ ማለት አብርሃም የተቀበለውን ያንኑ ቃል ኪዳን ቅዱሳን መቀበል ይችላሉ ማለት ነው። እነርሱም ወንጌልን እና የእግዚአብሔርን በረከቶች ለሚመጡት አያሌ ዓመታት በየስፍራው ላሉ ሰዎች ለመስጠት ሃይል ይኖራቸዋል ማለት ነው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥12

ኤሊያስ ለጆሴፍ እና ለኦሊቨር ሲገለጥ።

በመጨረሻም፣ ነቢዩ ኤሊያስ ተገልጧል። እርሱ ለጆሴፍ እና ለኦሊቨር ቤተሰቦችን ለማተም፣ ወይም ለማጣመር የክህነት ቁልፎችን ሰጣቸው። ቅዱሳን በቤተመቅደሶች ውስጥ የሚያከናውኗቸው ስራዎች በሰማይ ተቀባይነትን ያገኛሉ። አሁን ቤተክርስቲያኗ የአዳኙን ስራ ለመስራት እና እርሱ ዳግም ወደ ምድር ለሚመጣበት ለመዘጋጀት ሃይል አላት።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥13–16