“የጥበብ ቃል፣” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“የጥበብ ቃል፣” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
የካቲት 1833 (እ.አ.አ)
የጥበብ ቃል
የጌታ የጤና ህግ
በኑወል እና በአን ውትኒ መጋዘን የላይኛው ወለል ላይ ከእርሱ ጋር እንዲገናኙ ጆሴፍ ስሚዝ ከቤተክርስቲያን ጥቂት ሰዎችን ጋበዘ። በዚያም ወንጌልን እና ሌሎች ጉዳዮችን ተማሩ፣ እንዲሁም በቡድን ሆነው ጸለዩ። ይህንንም ስብሰባ የነቢያት ትምህርት ቤት በማለት ሰየሙት።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥117–137፣ Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥166
አብዛኞቹ ሰዎች ትምህርቱ በሚሰጥበት ጊዜ ፒፓ ያጨሱ ነበር እና የትምባሆ ቅጠልም ያኝኩ ነበር። ጭሱ አየሩን ደመናማ ያደርገው ነበር፣ እና ትንባሆውም ወለሉን ያቆሽሸው ነበር። ከስብሰባው በኋላ፣ ኤማ ስሚዝ ክፍሉን ለማጽዳት ወደ ፎቁ ወጣች። በጣም ቆሻሻ ነበር።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥167
ኤማ ወለሎቹን ደጋግማ ፈተገቻቸው፣ ነገር ግን የትምባሆው ምልክት ሊለቅ አልቻለም። ስለተዝረከረከው ነገር ከጆሴፍ ጋር አወራች።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥167
ጆሴፍ ኤማን አዳመጠ። እርሷን መስማቱ እግዚአብሔር ስለ ትምባሆው ምን እንደሚሰማው እንዲያስብ አደረገው።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥167
በመሆኑም ጆሴፍ ጌታን ስለትምባሆው ጠየቀ። ጌታም ለቅዱሳን የጥበብ ቃል እንዳለው ለጆሴፍ ስሚዝ ነገረው።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89፥1–9፣ Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥167
ጌታም ቅዱሳን ማጨስ እንደሌለባቸው፣ ትንባሆ መጠቀም፣ ወይም አልኮል ወይም ‘’ትኩስ መጠጦችን’ ማለትም ቡና እና ሻይ መጠጣት እንደሌለባቸው ተናገረ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89፥1–9፣ Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥167
ጌታም ለቅዱሳን ጥራጥሬ እና ፍራፍሬ መልካም ምግቦች እንደሆኑ እንዲሁ አስተማረ። እርሱም በተጨማሪ አንዳንድ ጌዜ ስጋን መብላት እንደሚችሉ ነገራቸው።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89፥10–17፣ Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥168
ጌታም ለጆሴፍ የጥበብ ቃልን ለመታዘዝ የሚመርጡ ቅዱሳን ጥበቃን እንደሚያገኙ ነገረው። ጌታም በጤና፣ በእውቀት፣ እና በብርታት እንደሚባርካቸው ቃል ገባ። ጆሴፍ በነቢያት ትምህርት ቤት ለነበሩት ሰዎች ስለ ጥበብ ቃል ነገራቸው።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89፥18–21፣ Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥168
በክፍሉ ውስጥ የነበሩት ሰዎች ትምባሆአቸውን እና ፒፓዎቻቸውን ወደ እሳት ውስጥ ወረወሩ ይህንንም ያደረጉት የጥበብ ቃልን እንደሚያከብሩ ለጌታ ለማሳየት ነበር።
Saints [ቅዱሳን]፣ 1፥168