በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ናቩን መገንባት


“ናቩን መገንባት፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች (2024 [እ.አ.አ])

“ናቩን መገንባት፣’’ የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

1840–1842 (እ.አ.አ)

ናቩን መገንባት

ጌታ ለውቧ ከተማ ያለው እቅድ

ቅዱሳኖች በሚሲሲፒ ወንዝ አቅራቢያ በድንኳን ውስጥ እየኖሩ።

ጌታ ቅዱሳን በአዲስ ቦታ እንዲሰበሰቡ ነገራቸው። ይህም ሚሲሲፒ በተባለ ትልቅ ወንዝ አጠገብ ነበር። መሬቱ እርጥብ እና ጭቃማ ነበር። ለአንዳንድ ሰዎች ይህ ቦታ ከተማን ለመገንባት ጥሩ ቦታ አይመስልም ነበር። ነገር ግን ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በጌታ እርዳታ ውብ ሊያደርጉት እንደሚችሉ ያውቅ ነበር።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥25ቅዱሳን1፥417

ቅዱሳን ናቩን እየገነቡ።

ቅዱሳኑ ጥሩ የመኖሪያ ቦታ ለማድረግ ጠንክረው መሥራት ጀመሩ። ነቢዩ ጆሴፍ ከተማዋን ናቩ ብሎ ጠራት፣ ትርጉሙም “ውብ ቦታ” ማለት ነው።

ቅዱሳን1፥417

ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎች ቤት እየሰሩ።

ጌታ መንገደኞች መጥተው የሚያርፉበትን ቤት በናቩ እንዲሰሩ ለቅዱሳ ነገራቸው። እርሱ ናቩ ሁሉም ሰው ጥሩ አቀባበል የሚደረግለት ቦታ እንዲሆን ፈለገ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥22–24፣ 60ቅዱሳን1፥426

ጆሴፍ ወደፊት ቤተመቅደስ የሚገነባበትን ቦታ እየጠቆመ።

ጌታ ለናቩ ታላቅ እቅድ እንዳለው ለነቢዩ ጆሴፍ ነገረው። ቅዱሳኑ ቤተመቅደስ ይገነቡ ዘንድ እዚህ እንዲሰበሰቡ ፈለገ። የእርሱን ቤት ለመገንባት የቻሉትን ያህል እንዲሠሩ ጠየቃቸው። ቅዱሳኑም በፍጥነት መሥራት ጀመሩ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥25–28፣ 44፣ 55ቅዱሳን1፥420–21425–27

ጆሴፍ ስለ ቤተመቅደስ እያስተማረ።

ጌታ ለቅዱሳን የሚሰጣቸው ታላቅ በረከቶች ስለነበሩት ቤተመቅደስ እንዲሰሩ ፈለገ። በቤተመቅደስ ውስጥ፣ ከጌታ ጋር ቃል ኪዳኖችን ወይም ልዩ ተስፋዎችን ይገባሉ። እንዲሁም የሰማይ አባት ለሁሉም ልጆቹ ስላለው የደስታ እቅድ ይማራሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥29–41ቅዱሣን1፥453–55

የተጠናቀቀው ቤተመቅደስ።

ልክ ጌታ እንዳዘዘው ቅዱሳን ቤተመቅደሱን ለመስራት ጠንክረው ሰሩ። ብዙ ጊዜ ወሰደባቸው፣ ነገር ግን እያንዳንዳቸው በቤተመቅደሱ ውስጥ ጌታ ስለሚሰጣቸው ልዩ ተስፋዎች ለሚማሩበት ቀን ጓጉተው ነበር።

ቅዱሳን1፥453–55