በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
የእስራኤል ሰፈር


“የእስራኤል ሰፈር፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“የእስራኤል ሰፈር፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

ህዳር 1833–የካቲት 1835 (እ.አ.አ)

የእስራኤል ሰፈር

በጌታ መታመንን መማር

በሚዙሪ ያሉ ቅዱሳን በድንኳን እየኖሩ።

በኢንዲፔንደንስ፣ ሚዙሪ ይኖሩ የነበሩ ቅዱሳን እርዳታ አስፈልጓቸው ነበር። እግዚአብሔር እንደጠየቀው ፅዮንን ለመገንባት ጠንክረው ሰርተዋል። ነገር ግን በከተማው የነበሩ ሌሎች ሰዎች በዚያ እንዲሆኑ አልፈለጉም ነበር። ቅዱሳን ቤቶቻቸውን ትተው እንዲሄዱ አደረጓቸው።

ቅዱሳን1፥195

ጆሴፍ ስሚዝ በሚዙሪ የነበሩ ቅዱሳን ስለነበረባቸው ትግል ተረድቷል።

ጆሴፍ ስሚዝ በከርትላንድ ይኖር ነበር። በሚዙሪ በነበሩ ቅዱሳን ላይ የተከሰተውን በመስማቱ አዝኗል። ምን መደረግ እንደሚገባ ለማወቅ ጸለየ። ጌታ ወደ ሚዙሪ አብረውት የሚሄዱ ስዎችን እንዲፈልግ ለጆሴፍ ነገረው። መንግስት የቅዱሳንን ቤቶች ለማስመለስ እንደሚረዳቸው ተስፋ አድርገው ነበር።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 103፥1–2፣ 11–20፣ 30–34ቅዱሳን1፥195–96

የእስራዔል ሰፈር በሚዙሪ የነበሩ ቅዱሳንን ለመርዳት በመዘጋጀት ላይ።

ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎች ከእርሱ ጋር ለመቀላቀል ፈቃደኛ ሆነው ነበር። ነቢዩ ይህንን ስብስብ የእስራኤል ሰፈር በማለት ጠራው። በሚዙሪ የነበሩ ቅዱሳንን ለመርዳት በመሄዳቸው ተደስተው ነበር።።

ቅዱሳን1፥197–99

ጆሴፍ ለብሪገም ያንግን፣ ለሂበር ኪምቦል፣ እና ለዊልፈርድ ውድረፍ ሰላምታ ሲያቀርብ።

ብሪገም ያንግ እና ጓደኛው ሂበር ኪምቦል የቡድኑ አካል ነበሩ። ዊልፈርድ ውድረፍ የተባለ አንድ ወጣት ከኒውዮርክ ድረስ ሊረዳቸው መጥቶ ነበር።

ቅዱሳን1፥197–98

የእስራኤል ሰፈር አባላት እረፍት ሲያደርጉ።

ብዙ ሰዎች ሰፈሩን ተቀላቀሉ። አንድ ወር ሙሉ የእግር ጉዞ አድርገዋል እና ወደ ሚዙሪ ለመሻገር ሰፊ ወንዝ ተሻገሩ። ደክሟቸው እና ዝለው ነበር። ረዥሙ የእግር መንገድ አንዳንድ ሰዎችን ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓቸው ነበር። ወደ ኢንዲፔንደንስ ከተማ ለመሄድ አሁንም ብዙ ርቀት ይቀራቸው ነበር።

ቅዱሳን1፥200–201

አንዲት ሴት የወንዶች ቡድን የእስራዔልን ሰፈርን እየፈለጉ እንደሆነ ነገረችው።

እየተጓዙ እያለ፣ አንዲት ሴት ወደ እነርሱ ተጣራች። እርሷም አንዳንድ ሰዎች ሊገሏቸው እየመጡ እንደሆነ ተናገረች።

ቅዱሳን1፥203

በፈረስ ላይ የነበሩ አምስት ሰዎች ጆሴፍን እና በእስራኤል ሰፈር የነበሩትን አስፈራሯቸው።

የእስራኤል ሰፈር ከወንዙ በላይ በነበረ አንድ ኮረብታ ላይ ቆመ። ሰፈሩንም ሲያደራጁ፣ አምስት ሰዎች በፈረስ ወደ እነርሱ መጋለብ ጀመሩ። 300 ተጨማሪ ሰዎች ሊያጠቋቸው በመንገድ ላይ እንደሆኑ በትእቢት መናገር ጀመሩ። ብዙዎቹ የእስራኤል ሰፈር አባላት ተጨንቀው ነበር። ጆሴፍም በእግዚአብሔር ላይ እምነት እንዲኖራቸው እርሱም እንደሚረዳቸው ነገራቸው።

ቅዱሳን1፥203

ጆሴፍ እና ሌሎች በአንድ ቤተክርስቲያን መጠለያን ሲፈልጉ።

ወዲያውኑም ሰማዩ በግራጫ ደመና ተሞላ። ከባድ ዝናብ መጣል ጀመረ። ወንዙ ጥልቅ እየሆነ መጣ። ነፋስም ዛፎችን ማስጎንበስ ጀመረ። መብረቅ በሰማዩ ዙሪያ ያንጸባርቅ ጀመረ። ጆሴፍ እና ሌሎች ደህንነት ሊሰማቸው የሚችልበትን አንዲት ትንሽ ቤተክርስቲያንን አገኙ። ሌሊቱን በሙሉ መዝሙር ሲዘምሩ አደሩ። ‘’እግዚአብሔር በዚህ ማእበል ውስጥ ነበር!” በማለት ጆሴፍ ተናገረ።

ቅዱሳን1፥203–4

ጆሴፍም ለእስራኤል ሰፈር አባላት ወደ ቤታቸው መሄድ እንደሚችሉ ሲነግራቸው።

ማእበሉ ሊያጠቋቸው የመጡ ሰዎችን አስቆማቸው። ሰፈሩ ደህና ሆነ። ነገር ግን መንግስት ቅዱሳንን አልረዳም አለ። የእስራኤል ሰፈር ሰዎች ወደየቤታቸው መሄድ እንደሚችሉ ጌታ ለጆሴፍ ነገረው። ቅዱሳኑ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት በመጠበቅ ፅዮንን መገንባት አለባቸው። እርሱ ‘’የጽዮንን ጦርነት እንደሚዋጋ’’ ቃል ገባላቸው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 105፥1–19ቅዱሣን1፥204–5

የእስራኤል ሰፈር አባላት እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ።

አንዳንድ የሰፈሩ አባላት ይህንን ሲሰሙ ተበሳጭተው ነበር። ለፅዮን ባለመዋጋታቸው አዝነዋል። አንዳንድ ሰዎች የእስራዔል ሰፈር ያልተሳካ መሰላቸው። ነገር ግን፣ እንደ ብሪገም ያንግ፣ ሂበር፣ እና ዊልፈርድ ያሉ ሌሎች ከነቢዩ ጆሴፍ ጋር በመሆናቸው እና ከእርሱም በመማራቸው አመስጋኞች ሆነዋል።

ቅዱሳን1፥205–6

ብሪገም ያንግ የኢየሱስ ክርስቶስ ሃዋርያ በመሆን ተሾመ።

በኋላም፣ ጌታ ለጆሴፍ ስሚዝ ቤተክርስቲያንን ለመምራት እንዲረዱ አስራ ሁለት ሃዋርያትን እንዲጠራ ነገረው። ሃዋርያቱ በዓለም ሁሉ የኢየሱስ ክርስቶስ ልዩ ምስክር እንዲሆኑ ተጠርተዋል። ከአስራ ሁለቱ ሃዋርያት ስምንቱ በእስራኤል ሰፈር አብረው ተጉዘው ነበር። ከጆሰፍ ጋር ማገልገል ለዚህ አስፈላጊ ጥሪ እንዲዘጋጁ ረድቷቸዋል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥ 26–27107፥23ቅዱሣን1፥214–17