“ሀይረም ፔጅ እና ራዕይ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“ሀይረም ፔጅ እና ራዕይ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
መስከረም 1830 (እ.አ.አ)
ሀይረም ፔጅ እና ራዕይ
ቅዱሣን፣ እግዚአብሄር ቤተክርስቲያኑን እንዴት እንደሚመራ ተማሩ።
ሀይረም ፔጅ የጆሴፍ ስሚዝ እና የኦሊቨር ካውድሪ ጓደኛ ነበር። የወርቅ ሰሌዳዎቹ ምስክሮች ከነበሩት ከስምንቱ አንዱ ነበር። ሀይረም ድንጋይ ነበረው፣ እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያኗ የሚሆኑ መልዕክቶችን ወይም ራዕዮችን ለእርሡ ለመስጠት እየተጠቀመበት እንደሆነ ያምን ነበር። ኦሊቨር እና ሌሎች ቅዱሣን የሃይረም ራዕዮች ከእግዚአብሄር እንደመጡ ያምኑ ነበር።
የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28፤ የክፍል መግቢያ፤ ቅዱሳን፣ 1፥97
የሃይረም ራዕዮች ከቅዱሳት መፃሕፍት ጋር ይመሣሠላሉ። ሆኖም መፅሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምረው የተለዩ ነበሩ፡፡ በተጨማሪም፣ ጌታ ለጆሴፍ ስሚዝ ከነገረው የተለዩ ነበሩ፡፡ ጆሴፍ ምን ማድረግ እንደነበረበት እርግጠኛ አልነበረም።
ቅዱሳን፣ 1፥97
ጆሴፍ አብዛኛውን ምሽት እግዚአብሔርን እርዳታ ሲጠይቅ ሳይተኛ ያድር ነበር። የተሳሳተ ነገር በማድረግ የጓደኞቹን ስሜት እንዳይጎዳ ተጨንቆ ነበር።
ቅዱሳን፣ 1፥97
ሰዎች ለራሣቸው ሕይወት የሚሆን ራዕይ እንዲሹ ይፈልግ ነበር። ሆኖም ሁሉም ሠው ለመላው ቤተክርስቲያኗ የሚሆን ራዕይን ለማግኘት ቢሞክር ግራ የሚያጋባ ይሆናል።
ቅዱሳን፣ 1፥97
በመጨረሻም፣ ጆሴፍ ለኦሊቨር የሚያካፍለውን ራዕይ ጌታ ሰጠው። ጌታ ራዕይን እና ትዕዛዛትን ለመላው ቤተክርስቲያኗ የሚቀበለው ነቢዩ ብቻ እንደሆነ ተናገረ። ኦሊቨር ይህንን ለሃይረም እንዲያስተምረው ነገረው።
ጌታ፣ ሃይረም ለራሱ ህይወት ራዕይ መቀበል እንደሚችል እንዲያውቅ ፈልገ። ሆኖም ለቤተክርስቲያኗ የሚሆን ራዕይ የሚመጣው ለጌታ ነቢይ ነው። ሃይረም ኦሊቨርን አደመጠ እንዲሁም ንሥሃ ገባ። አሁን፣ ቅዱሣን፣ እግዚአብሄር ቤተክርስቲያኑን እንዴት እንደሚመራ ተገነዘቡ።
ቅዱሳን፣ 1፥98