በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ሊብረቲ እስር ቤት


“ሊብረቲ እስር ቤት፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“ሊብረቲ እስር ቤት ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

ጥቅምት 1838—መጋቢት 1839 (እ.አ.አ)

ሊብረቲ እስር ቤት

በአስቸጋሪ ጊዜያት ጌታን ማግኘት

ወታደሮች በሚዙሪ ቅዱሳንን ከየቤታቸው ሲያባርሯቸው።

በሚዙሪ ይኖሩ የነበሩ ብዙ ሰዎች ቅዱሳንን አይወዷቸውም ነበር። የአገር ገዢም እነርሱን ለማስወጣት ወታደሮችን ላከ። ወታደሮቹ ቅዱሳንን ከየቤታቸው አባረዋቸው፣ ከቤታቸው ውስጥ አንዳንድ ነገሮችን ሰርቀው፣ እና ብዙዎችን ጎድተዋቸው ነበር።

ቅዱሳን1፥355–56362364

ወታደሮች ጆሴፍ ስሚዝን እና ሌሎች የቤተክርስቲያን መሪዎችን ሲያስሩ።

ወታደሮች ጆሴፍ ስሚዝን እና ሌሎች የቤተክርስቲያን መሪዎችን አሰሩ።

ቅዱሳን1፥357–58

ጆሴፍ እንደ እስረኛ ሆኖ ሲወሰድ የጆሴፍ ስሚዝ ልጅ እያለቀሰ።

ጆሴፍ ምናልባት ከቤተሰቡ ጋር ብቻውን መሆን ይችል እንደሆነ ጠየቀ። ወታደሮቹ አይቻልም አሉ። ጆሴፍን እና ሌሎች እስረኞችን ይዘዋቸው ሄዱ።

ቅዱሳን1፥366

ጆሴፍ ጠባቂዎችን መናገር እንዲያቆሙ ሲነግራቸው።

በአንድ ሌሊት ላይ፣ ጆሴፍ እና ሌሎች እስረኞች ጠባቂዎቹ በቅዱሳን ላይ ስላደረጓቸው መጥፎ ነገሮች እያወሩ ሲስቁ ሰሙ። ጆሴፍ ይህን ከዚህ በላይ ለመስማት ከበደው። ቆመ እናም በቁጣ፣ ‘’ዝምታ!’’ አለ። እርሱ ይናገር የነበረው በእግዚአብሔር ሃይል ነበር። ጠባቂዎቹ ፈሩ። ይቅርታ በማለት ንግግራቸውን አቆሙ።

ቅዱሳን1፥367–68

ጆሴፍ እና ጓደኞቹ በሊብረቲ እስር ቤት።

በኋላም፣ ጆሰፍ እና ጓደኞቹ ሊብረቲ በሚባል ከተማ ወደነበረው አንድ እስር ቤት ተወሰዱ። እስር ቤቱ ቀዝቃዛ፣ ትንሽ እና ጨለማ ነበር። የሚተኙበት የቆሸሸ የሳር ፍራሽ ብቻ ነበር የነበራቸው። የነበረው ትንሽ ምግብ ብቻ ነበር፣ እርሱንም ለበሽታ ዳርጓቸዋል።

ቅዱሳን1፥369–70374384–85

ጆሴፍ ስለቅዱሳኑ ተጨነቀ።

ጆሴፍ ስለ ቅዱሳን አብዝቶ ተጨነቀ። ወደዳቸው። ስለ እነርሱም ይጨነቅ ነበር። ነገር ግን እነርሱን ለመርዳት ሊያደርግ የሚችለው ነገር አልነበረም።

ቅዱሳን1፥385–86

ጆሴፍ በሊብረቲ እስር ቤት ሲሰልይ።

ጆሴፍ አብዝቶ ፀለየ። እግዚአብሔር ለምን ቅዱሳንን እንደማይረዳ እና የት እንደነበርም ጠየቀ። እግዚአብሔር እርሱን እና ቤተክርስቲያኗን ረስቶ ይሆንን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥1–6

ጆሴፍ ለጸሎቱ መልስን ሲቀበል።

እግዚአብሔር ለጆሴፍ ጸሎት ምላሽ ሰጠ። እንዲህም አለ፣ ‘’ልጄ ሆይ፣ ለነፍስህ ሰላም ይኑርህ።’’ እርሱም ፈተናዎቹ ለዘለዓለም የሚቆዩ እንዳልሆኑ እና ለመልካም እንደሚሆኑለት ለጆሴፍ ነገረው። እግዚአብሔር ለጆሴፍ ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳ ከዚህ በከፉ ነገሮች ውስጥ እንዳለፈ እንዲያስታውስ አደረገው። ‘’ለዓለም እና ለዘለዓለም’’ ከጆሴፍ ጋር እንደሚሆን ቃል ገባለት።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥7122፥5–9